Get Mystery Box with random crypto!

ለማሳወቅ ያህል ፦ ****** ከኦሮሞ አክቲቪስቶች መሀከል ለኦሮሞ ብልጽግና ያደሩ ብዙዎች በተለይ | Yalelet Wondye

ለማሳወቅ ያህል ፦
******
ከኦሮሞ አክቲቪስቶች መሀከል ለኦሮሞ ብልጽግና ያደሩ ብዙዎች በተለይም ለአቶ ሽመልስ አስተዳደር ቅርብ የሆኑት፣
በወለጋ ጉዳይ ታክቲካሊ የሚሰሩት ፕሮፓጋንዳ ዋነኛ መገለጫ ፦

1) Cover-up,
[ አንድም ግድያዎቹን እንዳይነገሩ ማፈን፣ አለያም
መካድ፣ ]

2) Chery-picking,
[ በጥቅል ሁነቱ ውስጥ መሠረታዊ ዋጋ የሌላቸው
አለያም ገዢ ማሳያ ያልሆኑ ጥቃቅን አለያም
ጠርዘኛ (Fringe/peripheral) ጉዳዮችን አጋኖ
እና ዋነኛ አድርጎ ማቅረብ፣ ]

3) blame shifting- victimization of the criminal,
[ ተጠያቂነትን ከወንጀሉ ፈጻሚ(ዎች) እና ተባባሪዎች በማንሳት በጉዳዩ ውስጥ እጁ ለሌለበት ምናባዊ ቡድን፣ አለያም የተጠላ እና እንዲጠላ የተፈለገ ሌላ አካል እንዲሁም የጥቃቱ ሰለባ የሆነን አካል መወንጀል እና ተጠያቂ ማድረግ፤ በዚህም አጥቂውን ሰለባ አድርጎ ማቅረብ ]

4) subversion of a reality,
[ በገሀድ የታወቀውን፣ ታውቆ በተደጋጋሚ የተነገረውን እና ብዙ ምስክሮች ያሉትን እውነታ መልክ ማሳጣት፤ ማለትም የታሪኩን የአፈጻጸም ሂደት መደበቅ- ዋና እና ጠርዘኛ ጉዳይ ማቀዳደም እና በማዛባት እንዲሁም ውሸቶችን መጨመር፣ ብዙ አላስፈላጊ ጉዳዮችን በማንሳት እና አማራጭ አተረጎጓሞችን በማቅረብ የጋራ ስምምነት እንዳይኖር ማወዛገብ እንዲሁም በጥንቃቄ የተፈበረኩ የግለሰብ(ቦች) ተረክ እና ለዚህ ተረክ በሚገጥም መልኩ የተቀናብሩ የምስል ማስረጃዎች በማቅረብ እውነታን ቀይሮ ማቅረብ ]

5) producing alternative story,
[ ከላይ የተጠቀሱትን ታክቲኮች ተጠቅመው በየጊዜው እውነታን የሚቃረኑ አለያም የሚተኩ የተለያዬ ተለዋጭ ትርክቶችን አቅርበዋል። ]

6) Making a hero out of Villains.
[ በዚህ ሂደት ውስጥ አንድም በቀጥታ በተሳታፊነት፣ አንድም በቸልተኝነት አለያም ችግሩን እንደ ዕድል በማየት ሀላፊነትን ባለመወጣት፣ በወንጀል ተጠያቂ ሊሆኑ የሚገባቸውን አካላት እንደ ጀግና እና ዋና የመፍትሔ ሰጪ አድርጎ ማቅረብ። ከላይ የተጠቀሱት ታክቲኮች በተደጋጋሚ የተደረጉ ሲሆን ይኼኛው ግን አሁን የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ከላይ ባሉት ላይ በተጨማሪነት የተደረገ እና እየተደረገ ያለ ነው። ]

7) Creating a story of triumph to outweigh a leadership failure and grand criminal scheme which resulted The Fst and foremost horrible humanitarian disastor in the country that continued for the last 5 years, Or More.
[ ይህ እስካሁን ያልተደረገ ሲሆን ታክቲኩ ስትራቴጂካዊ ግብን ያዘለ እና የጌም ፕላኑ የፍጻሜ መሳሪያ ሊሆን የሚችል ነው። የወለጋው ኦፕሬሽን አፈጻጸምን ተከትሎ የዚህ ታክቲክ ትገበራው ሊለያይ ይችላል። የታክቲኩ አላማ ለ5 እና ከዛ ያለፉ አመታት የዘለቀውን የወለጋን አስፈሪ ሰብአዊ ውድመት እንዲሁም ለዚህ መግፎኤ የሆነውን ከአመራር ክሽፈት ጋር የተዳበለ ግዙፍ የወንጀል ሴራ የሚሸፍን የድል አድራጊዎች ታሪክ መጻፍ ነው። ]

__

እነዚህን ተግባራት እያደረጉ ያሉት አካላት የትልቁ የወንጀል ሴራ አካል አለያም ተባባሪ ናቸው። ሆኖም አካሄዱ አሳች በመሆኑ ተታልተው በዚህ ወጥመድ የገቡም ሊኖሩ ይችላል።
በተረፈ ግን በወለጋ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል የሚቃወሙ አካላት ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች በአንክሮ አጢነው ሊያዩ እና በጥንቃቄ ሊታገሉ ይገባል።

@ ዳዊት መሃሪ