Get Mystery Box with random crypto!

የንፅፅር ኮርሶች #1 ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ባለፉት አምስት አመታት 10 በሚጠጉ የንጽጽራዊ ርዕ | የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

የንፅፅር ኮርሶች #1

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ባለፉት አምስት አመታት 10 በሚጠጉ የንጽጽራዊ ርዕሶች ዙሪያ ከ2,000 በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የንጽጽር ኮርስ በነጻ ሰጥቷል። አብዛኛዎቹ የንጽጽር ኮርሶች አጫጭር ጊዜን ያማከሉ ሲሆን በተለየ ሁኔታ ደግሞ ረጃጅም ኮርሶችንም ስርአተ ትምህርት በመቅረጽ አስተምሯል። ከነዚህ ውስጥ አብዛኛው በኢንተርኔት አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም ለዩንቨርሲቲ ተማሪዎች፣ የአክፍሮተ ሀይላት ስጋት ላለባቸው አካባቢዎችና ፍላጎቱ ላላቸው ሁሉ በተቻለ መጠን ለመስጠት ተሞክሯል።

ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ቦታዎች በአካል በመሄድ ስልጠና የሚያስፈልጋቸው ሁነው ሲገኙ ቦታው ድረስ በመገኘት አጫጭር ስልጠናዎችንና የማጥኛ ማቴሪያሎችን በነጻ አበርክተናል። በቀጣይም ይህንን ስራ በሰፊው ለመስራት የታቀደ ሲሆን በተለይም በገጠሩ አካባቢ የሚሽነሪ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች አጠናክሮ የመስራት እቅድን አንግበን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን።

ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ ወንድምና እህቶች በቀጥታ የተቋሙ አካውንት ቁጥር ገቢ አድርጋችሁ ደረሰኝ ከዚህ በታች ባለው ግሩፕ ሼር ልታደርጉን ትችላላችሁ።
..
1000499318212
Hidaya Islamic Center
አጭር ቁጥር - 8212
..
ወደ ግሩፑ ለመቀላቀል፦
https://t.me/+Dy1d7s3_31s4NmQ0