Get Mystery Box with random crypto!

Yeka Abado Full Gospel Belivers'church

የቴሌግራም ቻናል አርማ yafgbchurch — Yeka Abado Full Gospel Belivers'church Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ yafgbchurch — Yeka Abado Full Gospel Belivers'church
የሰርጥ አድራሻ: @yafgbchurch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 208
የሰርጥ መግለጫ

Channal

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 17:06:24

22 views14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 16:40:48 “አቤቱ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞው አድስ፡፡” ሰቆ ኤር 5፡21

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የአባዶ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ

ከነሐሴ 30 - ጳግሜ 5/201 የጾምና የጸሎት ጊዜ

1ኛ) የምስጋና ጸሎት መዝ 136፡1-26

 እንደዚህ በአንድነት እንድንጸልይ እድልን ስለተሰጠን ማመስገን

አንደ ግልም ሆነ ፤ እንደ ቤተክርስቲያን ፤ ስለሃገርም ጸልየን፤ ለምነን ፤ማልደን ፤ የሆነልንን ሁሉ እያሰብ ማመስገን

2ኛ) እውነተኛ ንስሃ ማድረግ መዝ 55፡ 7

 ራሳችንን እየመረመርን ፤ስለቤተሰቦቻችን

 ስለ ሃገር መሪዎች ፤ ፓለቲከኞች ምህረትን እንጠይቃለን
ስለ ባለስልጣናት፤

3ኛ) ምልጃ ከልመና ጋር መጸለይ 1ጢሞ 2፡1-2

 ሰዎች እንዲድኑ፤ እግዚአብሔርን መፍራት በምድሪቱ እንዲሆን

 የይቅርታ ህይወት እና እውነተኛ ፍቅርን መለማመድ እንድንችል፡፡

 ለቃሉ ትኩረት የሚሰጥ ህይወት እንዲኖረን

 ስለ ሃገራችን የሰላም ሁኔታ ስለ ምድሪቱ ኢኮኖሚ፤ ማህበራዊ ግንኙነት ፤ የሰዎችን መጥፎ የሆኑ አመለካከቶችን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲቀይር

 የታመሙ እንዲፈወሱ ፤ የተለያየ ችግር ስላለባቸው

 በሱዳን፤ በግብጽ፤ በጎረቤት አገሮች ላይ እና በእነ አሜሪካ አውሮፓ መጸለይ

 በቤተክርስቲያናችን የእግዚአብሔር
ሃይል እንዲገለጥ : ስለ ሪቫይቫል፤

 ስለሃገራችን ሰላም ግጭትና ጦርነቱ ፤ ስደት እንዲቆም

 ልጆችን አዳጊዎችን እና ወጣቶችን በእግዚአብሔር ፊት ይዞ መቅረብ

 ስለ ተሰጠን ቦታ መጸለይ

4ኛ) እየተቃወምን መጸለይ ያዕ 4፡7
 በግለሰብ ፤ በቤተክርስቲያንና በሃገር ላይ የታሰበ የታቀደ የጠላት ስራ እንዲፈርስ

 ርኩሰትን የሚያስፋፋውን፤ግልሙትና፤ ግብረሰዶም

 በቦታችን ላይ የተነሳውን ተግዳሮት በመቃወም እንጸልይ !
28 viewsedited  13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:14:16 ምዕራፍ 2

በክርስቶስ ያለ ምክርን እንፈጽም

ወደ ፊሊጲስዮስ 2: 1-4

1 በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤

2 በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤

3 ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤

4 እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።
I. በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ ምን አይነት ምክር ነው? ጳውሎስ ደስታዬን ፈጽሙልኝ ያሰኘው-

1. የፍቅር መጽናናት
2. የመንፈስ ኅብረት
3. ምሕረትና ርኅራኄ

እነዚህ ፍቅር፤ ኅብረት፤ ምህረትና ርህራሄ በክርስቶስ ውስጥ ያየናቸው ባህሪያት ናቸው ስለዚህ እነዚህ ባህርያት በመንፈስ ቅዱስ በኩል ዛሬ በእኛ ይገለጣሉ:: በፍቅር ተመላለሰ ደግሞም ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም የተባለለትን ትልቅ መስዋዕትነት ከፈል:: ከአባቱም ጋር ህብረት ነበረው ለሊቱን ሁሉ ሲጸልይ ያድራል:: ምህረትና ርኅራሄውም በደንብ ታይቷል:- ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? እኔም አልፈርድብሽም ሂጂ ሲል በሌላ ቦታ ደግሞ እረኛ እንደሌላቸው ተበትነው ሲያይ አዝኖ:: ለታመሙት ራርቶ የሚፈውስ ከሚያለቅሱት ጋር የሚያለቅስ ሩህሩህ ጌታ:: ብዙ ማለት ይቻላል ስለ እየሱስ ይህ በርሱ የተጀመረው ህይወት አሁንም በእኛ ይቀጥል::

II. በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ ምን ብናደርግ ነው በአንድ ሀሳብ ልንስማማ የምችለው?

1. አንድ ፍቅር – ክርስቶስን ብቻ ማየት እንዴት እንደወደደን

2. አንድም ልብ – ክርስቶስ እንዲከብር ብቻ ማሰብ
3. አንድም አሳብ – እርሱን በሀሳባችን ሁሉ መቀደስ ያኔ እርሱን ብቻ ለማክበር እንስማማለን

4. በትሕትና – ሰውን ሁሉ በክርስቶስ ውስጥ ማወቅና ከኔ ይሻላል ማለት

5. ለሌላው በማሰብ – በሌላው ውስጥም ጌታ ይሰራል ብሎ መቀበልና መርዳት ወደ ተጠሩበት ነገር እንዲደርሱ
በዚህ ሁሉ ውስጥ ዝቅ ማለትና በትህትና መመላለስ አለብን እኔ አውቃለሁን ትተን ከኔ ይሻላል ወገኔ እንበል:: ያለ ሌላው አገልግሎት እኔ የምሮጠው ሙሉ እንድማይሆን ማወቅ:: እግዚአብሔር ለትሁታን ጸጋን ይሰጣልና::
48 views04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:04:33 ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ

ወደ ፊልጵስዩስ 1: 22-30

22 ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም።

23 በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ 24 ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው።

25 -26 ይህንንም ተረድቼ፥ በእናንተ ዘንድ እንደ ገና ስለ መሆኔ፥ በእኔ መመካታችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ይበዛ ዘንድ፥ በእምነት ታድጉና ደስ ይላችሁ ዘንድ እንድኖር ከሁላችሁም ጋር እንድቈይ አውቃለሁ።

27 ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ።

28 በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤ 29 ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤

30 በእኔ ያያችሁት አሁንም በእኔ እንዳለ የምትሰሙት፥ ያው መጋደል ደርሶባችኋልና።

አሁን እንደው ጳውሎስ ልኑር ወይስ ልሙት የቱን ልምረጥ እያለ ሲቸገር ይገርማል:: ማንም በዚህ ጥያቄ ሲፈተን አይቼ አላውቅም ልኑር ህይወቴን አቅና የሚል እንጂ እኔንም ጨምሮ ያውም ከአንዱ የድብደባ መድረክ ወደሌላው የሚሄደው ጳውሎስ የቱን መምረጥ እንዳለበት ሲቸገር ይደንቃል:: ልክ እንደው ሁለት የሚያጉዋጉዋ ነገር በፊቱ ያለ ይመስላል:: አንድም እየተደበደቡ መኖር አልያም መሞት እና ወደ ጌታ መሄድ:: እሱ እንዳስቀመጠው ግን ለኔ መሞቱና ወደ እረፍት መግባቱ ይሻላል ደግሞም በጣም እናፍቃለሁና ከጌታዬ ጋር መኖርን ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ብቆይ ደግሞ በእኔ መመካታችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ይበዛ ዘንድ፥ በእምነት ታድጉና ደስ ይላችሁ ዘንድ እንድኖር ከሁላችሁም ጋር እንድቈይ አውቃለሁ ብሎ መቆየቱን መርጧል::

ከራሱ ይልቅ ለሌላ ለመኖር ወሰነ እኛስ ምን እንወስን ይሆን? እራሳችንን ስናይ ግን አንዳች ጎደለን ብለን ወይም ይህ ነገር አልተሳካም ብለን ወደ ጌታ በሄድን ወይም እርሱ በመጣ እምንል ነን:: ምን አይነት የወንጌል መልእክት እንደያዝን አይገባኝም ጌታ ይርዳን ለክርስቶስ አካል እንኑር ብለን ለመኖር ከየት እንደምንጀምርም ግራ ይገባል:: ወንጌል ግን ለጌታ መኖር ነው::

ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ ብሎ ይላል እንዴት ነው እንደሚገባ የምንኖረው?

1. በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ – የያዝነው የወንጌል ስራ እንደ አካል በህብረት የሚሰራ ነውና በመዋደድና በመደጋገፍ ልንሰራ ይገባል:: ዮሐንስ 13:35. እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።

2. በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ – 1ኛ ቆሮንቶስ 12
13፤ አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል። እናስታውስ ያው አንዱ መንፈስ በሁላችን አለልዩነት አለ::
እንደዚህ ስንመላለስ የጠላት ፉከራና ቀረርቶ አያስፈራንም ምክንያቱም የመዳን ምልክት እንጂ ለእኛ የጥፋት አይደለም::

ክርስቶስን ስንከተል ከወንጌል የተንሳ መከራ ይመጣል ግን አያጠፋንም እናሸንፋለን::
81 viewsedited  04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:01:39 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው

ወደ ፊልጵስዩስ 1:21

21፤ ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።

ዘራፍ!! እያለ ድፍረት ለማግኘት እራሱን እያነቃቃ አይደለም ጳውሎስ ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነው ሲለን ውስጡ የሞላውን እውነት ነው የሚነግረን ያለው:: ያስጨነቀው መሞቱ አይደለም ለኔ መሞት ጥቅም ነው ነው ያለው ብኖር እጠቅማችኃለሁ ስለዚህ ስጋዬ በግርፋትና በመከራ ይለፍ እንጂ ነፍሴን መንካት ማንም አይችልም በሚል ልበ ሙሉነት ነው እየተናገረ ያለው:: ለሌላው አካል ወይም እስር ቤት ላስገቡት ቦታም አልሰጣቸው ከእስርም ያስመልጣል ከሞትም ያስነሳል የኔ ጌታ ሁሉ በእጁ ነው እያለ ነው:: ከዚህ በፊት ደብድበው ሞቷል ብለው ጥለውት አልሄዱም? እርሱ ግን ተነስቶ መስበኩን ቀጠለ አይደል? ጌታውን ጠንቅቆ ያውቃል እኛም እንወቀው:: የሚያኖረን ከክርስቶስ የተቀበልነው ጸጋ እንጂ የሰው ቸርነት ወይም የስጋችን ብርታት አይደለም::


ህይወታችን እራሱ ክርስቶስ ነው በእርሱ ውስጥ ነን ካልን እዚህ እንሁን ወይም በሰማይ ምንድነው ለውጡ? በመጀመርያ ግን በእርሱ ውስጥ ነኝ የሚለው ሀሳብ በውስጣችን ሊዘልቅና አይምሯችን በዚህ እውነት ሊሞላ ይገባዋል:: ሞት እኮ መውጊያውን ተነጥቋል ዛሬ መጣሁ እያለ አያስፈራራንም ከሞትም ጋር ህብረትም ወዳጅነትም የለንም:: ለእኛ ሞት ማለት በር ብቻ ነው ወደ ዘለዓለሙ መዝለቂያ እንዲያውም ሊያስፈራን ሳይሆን ስራችንን ስንጨርስ በል አሰናብተኝና ወደቤት ልምጣ የምንልበት ማለፊያ በር ብቻ ነው:: የመጨረሻ የተባለውን ትንፋሽ በዚች ምድር ላይ ስንወስድ ወድያው የመጀመሪያውን በሰማይ እንጀምርና ጌታንም በክብሩ እናየዋለን:: ግን ዛሬ ነፍስና ስጋችንን የሚያላቅቀው ነገር ሞት አይደል?! ዛሬም ጠላት መጣሁብህ እያለ ባዶ እጁን የቀረበትን የሽንፈት መሳሪያውን እንደድል ሲጠቀምበት ዝም አልነው::

ይብቃ እኛ የክርስቶስ ነን!! ማንም ከቶ አያስፈራራንም ብንኖር ለጌታ ብንሞት ለጌታ!

ሃሌሉያ!!!
108 viewsedited  17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 06:39:29 በሁሉ ምክንያት ክርስቶስ ይሰበክ

ወደ ፊልጵስዩስ 1:12-20

12፤ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህ የደረሰብኝ በእውነት ወንጌልን ለማስፋት እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።

13፤ ስለዚህም እስራቴ ስለ ክርስቶስ እንዲሆን በንጉሥ ዘበኞች ሁሉና በሌሎች ሁሉ ዘንድ ተገልጦአል፥

14፤ በጌታም ካሉት ወንድሞች የሚበዙት ስለ እስራቴ ታምነው የእግዚአብሔርን ቃል እንዲነግሩ ያለ ፍርሃት ከፊት ይልቅ ይደፍራሉ።

15፤ አንዳንዶች ከቅንአትና ከክርክር እንኳ ሌሎች ግን ከበጎ ፈቃድ የተነሣ ክርስቶስን ይሰብኩታል፤

16፤ እነዚህ ወንጌልን መመከቻ ለማድረግ እንደ ተሾምሁ አውቀው በፍቅር ይሰብካሉ፥

17፤ እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ መከራን ሊያመጡብኝ መስሎአቸው፥ ለወገናቸው የሚጠቅም ፈልገው በቅን አሳብ ሳይሆኑ ስለ ክርስቶስ ያወራሉ::

18፤ ምን አለ? ቢሆንም በሁሉ ጎዳና፥ በማመካኘት ቢሆን ወይም በቅንነት ቢሆን፥ ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል።

19፤ ወደ ፊትም ደግሞ ደስ ይለኛል፤ ይህ በጸሎታችሁና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ መሰጠት ለመዳኔ እንዲሆንልኝ አውቃለሁና፥

20፤ ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በአንድ ነገር እንኳ አላፍርም ነገር ግን በህይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ በግልጥነት ሁሉ እንደ ወትሮው አሁን ደግሞ በስጋዬ ይከብራል።

ወንድማችን ጳውሎስ ወንጌልን ሲሰብክ የደረሰበት ብዙ ድብደባ ብሎም እስራት ነው:: መታሰሩም ወንጀል ሰርቶ ሳይሆን በእምነቱ እንደሆነ ታውቋል:: ይህም ወሬ አሳሪዎቹም ሳይቀሩ አውቀዋል ምናልባትም ወንጌልን ሰምተዋል:: በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን በእኔ ላይ የመጣውን መከራ እዩ ሳይሆን እያለ ያለው አይዟችሁ መታሰሬ አያሳዝናችሁ በርቱ ወንጌልን ስበኩ እያለ ነው:: እንዲያውም አንዳንድ ወንድሞች እስራትን ንቀው ከፊት ይልቅ ወንጌልን እየሰሩ ነው ይላል ምክንያቱም እርሱ ስለ እስራቱ ሳይሆን የሚያወራው ስለወንጌል መሰበክ ስለሆነ በወገኖች ላይ ያሳደረው ነገር ወንጌል መሮጥ አለበት የሚልና ብያዝ እንኳን ግፋ ቢል መታሰር ነው እንደእርሱ ሳልያዝ ልስራ የሚል መንፈስ ነው:: ሌሎች ደግሞ በማሾፍ የሞተ ተነሳ ይላል ብለው አንዳንዶችም መከራውን ሊያበዙና ወደፊት ስለዚህ ጌታ ሁለተኛ እንዳይናገር ተስፋ ለማስቆረጥ ስለ ኢየሱስ ይናገራሉ::

በዚህ ሁሉ ግን ይላል ኢየሱስ ብቻ ይሰበክ በዚህ ደስ ብሎኛል ይላል::

በህይወት ይሁን በሞት በስጋዬ ጌታ ይክበር ባይ ነው ምክንያቱም አላፍርም በጸሎታችሁና በመንፈሱ ተረድቼ እቆማለሁ ይህ ተስፋዬ ናፍቆቴም ነውና ብሎ ስለ ዘላለም ህይወቱ እንጂ ከስር ስለመፈታቱ አያወራም ሁልጊዜ ወደጌታ ያሳያል ያበረታል:: እኛም ዛሬ አይናችንን በርሱ ላይ አድርገን ወንጌልን እንስበክና እንኑረው::
128 views03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 23:27:09 ፍቅራችን በእውቀትና በማተዋል ይብዛ

ወደ ፊልጵስዩስ 1: 9-11

9-11፤ ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ።

1. ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሆን ዘንድ ከክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶብን መገኘት አለብን:: እናስተውል ከእኛ አይደለም የጽድቁ ፍሬ የሚመጣው ከጠራን ከራሱ ነው:: ነገር ግን ገና የራሳችንን ጽድቅ ለማቆም የምንነሳ ከሆነ አስቸጋሪ ነው ወደ እረፍቱ መግባታችን ታድያ ምኑ ላይ ነው? ውላችን እኛ ልንሞት እርሱ በእኛ ሊኖርም አይደል? እንደዛ ካላሰብን የምንፈልገውን መለወጥ አናየውም ጥረት ግረት ሆኖ ይቀራል:: ክርስትና ግን እረፍት ነው ደግሞም ክብርና ምስጋናን ከእኛ ህይወት የተነሳ የምናመጣ ነን:: ደስ አይልም? በተቃራኒውም እንዳለ ልብ እንበል::

2. ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ እኛ የመድኃኒታችንን ከሰማይ መገለጥ የምንጠባበቅ ነን:: ስንጠባበቅ ግን ኑሮ እናቆማለን ማለት አይደለም ነገርን ፈትነን የሚሻለውን ማለትም:- እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ይለናል ቃሉ:: ይህንንም የምናደርገው ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅተን ቅኖችና እለነውር ሆነን እንጠብቅ::

3. ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ። ፍቅር በእውቀት እየጨመረ የሚመጣ ነው:: ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ ጌታ ይፈልጋል:: ይህ እንዲበዛ ነው ጳውሎስ እጸልያለሁኝ ያለን እኛም እንጸልይ ይህ ከመታወቅ የሚያልፍ ፍቅር በህይወታችን ውስጥ ይገኝ ዘንድና ማስተዋልም እንዲሆንልን::
125 viewsedited  20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:06:24 የተወደዳችሁ የቤተክርስቲያናችን አባላት እና ከእኛ ጋር የምታመልኩ ወገኖች ሁሉ

እንደ ጌታ ፍቃድ ከነሐሴ 30 እስከ 3 /2014 ዓም ማለት ከሰኞ እስከ ሐሙስ በአጥቢያችን የጾምና ጸሎት ይደረጋል። አርብ በጋራ ከአብያተ ክርስቲያን መገኖች ጋር ከ3-7:30 በሲኤምሲ ሙሉወንጌል እንዲሁም ቅዳሜ ጳግሜ 5 በአጥቢያችን እንፀልያለን ።

ጌታ ይባርካችሁ።
129 viewsedited  06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 07:49:58 መልካሙን ስራ ክርስቶስ ይፈጽመዋል

ወደ ፊልጵስዩስ 1: 3-8

3-5፤ ሁልጊዜ በጸሎቴ ሁሉ ስለ እናንተ ሁሉ በደስታ እየጸለይሁ፥ ከፊተኛው ቀን እስከ ዛሬ ድረስ ወንጌልን በመስበክ አብራችሁ ስለ ሠራችሁ፥ ባሰብኋችሁ ጊዜ ሁሉ አምላኬን አመሰግናለሁ።

6፤ በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፤

7፤ በእስራቴም ወንጌልንም መመከቻና መጽኛ በማድረግ ሁላችሁ ከእኔ ጋር በጸጋ ተካፋዮች ስለ ሆናችሁ፥ በልቤ ትኖራላችሁና ስለ ሁላችሁ ይህን ላስብ ይገባኛል።

8፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ሁላችሁን እንዴት እንድናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና።

የዝች ቤተክርስቲያን ሰዎች ከጳውሎስ ጋር ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ነው አብረውት የወንጌል ሰራተኛ የሆኑት እርሱም በጣም ነው የሚወዳቸውና ስለእነሱ ሲጸልይም በደስታ አምላኩን ያመሰግናል::

ጳውሎስ ወዳጅነቱን በግልጽ ነው የሚያሳየው ደብዳቤው የግል እንጂ ለቤተክርስቲያን የተጻፈ መልእክት እንኳን አይመስልም:: ባደረጉለት ስጦታ ምክንያት ህይወቱን ይደግፉ ነበርና መቼም ድንኳን በመስፋት ብዙውን ጊዜ ከሚያውል ለማገልገል እንዲችል አስችለውታል ምክንያቱም አብራችሁኝ አገለገላችሁ ብሎ እውቅና እየሰጣቸው ነው:: ጸጋ የተለያየ ነውና በተሰጠን ጸጋ እንገለጥ ያን ጊዜ ወንጌል በኃይል ይሄዳል የግድ ሁሉም ሰው መስበክ የለበትም ልግስናም ጸጋ ነውና ለመንግስቱ ያስፈልጋል:: የተሰጠን ጸጋ ምንድነው? እናገልግልበት::

እግዚአብሔር ታማኝ ነውና በእናንተ የተጀመረው ስራ ይቀጥላል፥ ይሰፋል ምክንያቱም እሱ የታመነ ጌታ ስለሆነ የስራውም ባለቤት እርሱ ስለሆነ ይህ የማይቀር ሀቅ ነው:: በእርግጥ የእኛ መተባበር ያስፈልጋል የእግዚአብሔር ግን መምራትና መርዳት አስፈላጊ ነው እርሱንም ያደርገዋል እያለን ነው ለእኛም።

በእስራቱ ሳያፍሩና ሳይረሱት ስለእርሱ በማሰብ አብረውት ቆመዋል ከዚህ ሁሉ በላይ ግን እንደዚህ ያቆመው ጸጋ እንደሆነ ጳውሎስ ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ነው ለእናንተም ይህ ጸጋ ያቆማችኃል እያላቸው ነው:: ምንም አይነት ነገር ቢመጣ እርሱ በጸጋው ያቆማችኃል እኔ ምስክር ነኝ እያለ ነው::

ዛሬም በምናልፍበት ሁሉ በጸጋው ሊረዳን የታመነ ነው የእኛ ጌታ ከጳውሎስ ጋር እንደነበረ ዛሬም ከእኛ ጋር በስራ ላይ ነው::
ጳውሎስ እነዚህን ሰዎች ከመውደዱ የተነሳ ሁልጊዜ መቼ ነው የማያቸው በሚል ጉጉት ውስጥ ነበር ግን የወንጌል ስራ ስለበለጠበት ሳያያቸው ቆየ:: ሊያያቸው እንዴት እንደሚናፍቅ ግን እግዚአብሔር ነው ምስክሬ ይላቸዋል እንዲህ ያለ መነፋፈቅንና መተሳሰብን ጌታ በዘመናችን ባለችው ቤተክርስቲያን ውስጥም ያድርግ ይህ ፍቅር ይፍሰስልን:: አሜን!
127 views04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 01:07:17 ምዕራፍ 1

የሐዋርያው የጳውሎስ መልዕክት
ወደ ፊልጵስዩስ 1:1-2

1፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤


2፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


ጳውሎስ እራሱንና አብሮት የሚያገለግለውን ጢሞቴዎስን የኢየሱስ ባርያ ብሎ ይጀምራል ጽሁፉን::


ኢየሱስ ጌታዬ ነው በሰራሁት ስራ ሁሉ ጌታዬን ለማስደሰት ነው እያለ ይህንን እንደመረጃ እየሰጠ ያለው::

የተጻፈላቸውም የቤተክርስቲያንዋ አገልጋዮችና እንዲሁም ምዕመኑ በሱ አጠራር ቅዱሳን ብሎ ይጠራቸዋል ዛሬም ለኛ ቢጽፍ እንደዚህ አድርጎ ነው የሚጠርን ደግሞም ቅዱሳን ነን በጌታ ከመዋጀታችን የተነሳ::


የመግቢያው ሰላምታ እንደሰላምታ ብቻ አይደለም ባርኮትም አለበት ከአባታችን እንዲሁም ከኢየሱስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን:: አሜን!

ማንም በክርስቶስ ካልሆነ በስተቀር ይህንን ሰላም መለማመድ አይቻልም።

እርሱ የሚሰጠን ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው አይነት አይደለም ይልቁንም አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ ነው::

ዛሬም ሰላሙና ጸጋው ይብዛልን ይትረፍረፍልን::
135 views22:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ