Get Mystery Box with random crypto!

#ልረሳሽ_እልና ልረሳሽ እልና የትዝታን መዝገብ ዳግም እከፍታለሁው የደረቀን ቁስል አመረቅ | የፍቅር ጥቅሶች

#ልረሳሽ_እልና

ልረሳሽ እልና የትዝታን መዝገብ
ዳግም እከፍታለሁው
የደረቀን ቁስል አመረቅዛለው
ከሞት ለደረሰ ነፍስሽ መዳን እሆናለው።

ልረሳሽ እልና መርሳት #ይሳነኛል
ከልቤ ኪዳን ላይ #መፋቅ ይከብደኛል
አንቺን መተው ሳስብ #ትውስታሽ ያመኛል
እንደው ምን ላርግሽ ምን ባረግ ይሻለኛል።

ሀቂቃ ነው ምልሽ ልረሳሽ እልና
አስታውስሻለው ዛሬም እንደገና
ትዝታሽ ይጠላል አንደ ሰማይ ዳመና
አስታውስሻለው ልረሳሽ እልና።

አቅም ይከዳኛል ሳስብ ልረሳሽ
ያዝለፈልፈኛል ሀያሉ የፍቅርሽ
መቶ ይወጋኛል ፀዳል ፈገግታሽ።

ልረሳሽ ልፍቅሽ እልና ከሂወቴ መዝገብ ላይ
መቶ ይደቀናል መልክሽ ከፊቴ ላይ
ይከለክለኛል ዙሬ #ሌላ እንዳላይ።

በቃ ይሄ ነው ያለው ሌላ ምንም የለም
አንቺን መርሳት ሳስብ አንቺን ነውየማልም
አንቺን #ማሰብ እንጂ መዘንጋት #አይቻልም
ምንም እንኳ ባልም ለመርሳት እንደገና
አስታውስሻለው #ልረሳሽ እልና

Join & Share

@yabutiiiiiiiiiiiii
@yabutiiiiiiiiiiiii