Get Mystery Box with random crypto!

ኢት-ዮጵ

የቴሌግራም ቻናል አርማ xobya — ኢት-ዮጵ
የቴሌግራም ቻናል አርማ xobya — ኢት-ዮጵ
የሰርጥ አድራሻ: @xobya
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.80K
የሰርጥ መግለጫ

ኢት-ዮጵ
ይህ ቻናል ያየሁትን የሰማሁትን እና ያነበብኩትን ሼር የ ማደርግበት ነው ይህ ቻናል እንዲያድግ ሼር በማድረግ ተባበሩን✌✌✌✌
አስተያየት ካላችሁ
@Hiloga_bot ላይ ያድርሱን
መጸሀፍ ከፈለጉ @telemondo
ግሩፕ ለመቀላቀል @etyolis


@ኢት-ዮጵ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-23 11:47:49 እስቲ አፍቅሩ !

አሌክስ አብርሃም

በምድር ላይ ያልባከነ ምርጥ ጊዜ ማለት በፍቅር ያሳለፋችኋቸው ደይቃዎች ናቸው … እስቲ አፍቅሩ …መልካችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ …እድሚያችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ … ኑሮ ቢከብዳችሁ ራሱ ኑሮ ከከበደው ጋር ተፋቀሩ …ፍቅር ተያይዞ ማደግ ብቻ አይደለም ተያይዞ መውደቅም ነው ! በጥላቻና በድርቅና ከመቆም ለፍቅር መውደቅ ተለማመዱ !

``አገር፣ህዝብ ፣ፖለቲካ በሚል ግዙፍ ነገር ውስጥ እየዳከራችሁ የጤፍ ቅንጣት አክላችሁ አትሙቱ … ፍቅር የሚባል እጅግ ረቂቅ አየር ወደውስጥ ሳቡና አገር አክሉ ! የማታፈቅሩበት አገር ምን ያደርግላችኋል? ገብስ ልታመርቱበት ነው? …የማታፈቀሩበት ህዝብ ምን ያደርግላችኋል ቀብራችሁን እንዲያደምቅ ነው …?የማታፈቅሩበት ፖለቲካ ምን ያደርግላችኋል? ፓርላማ ልተሰየሙበት ነው? …የማታፈቅሩበት ህገ መንግስት ምን ያደርግላችኋል ሲጀመር ይልተጣመራችሁትን መገንጠል እንዲፈቅድላችሁ ነው? …

ተያዩ ተነጋገሩ ትዝብት ጥርጣሬ ፍርሃትን ወደዛ ጣሉና በፈገግታ በተሞላ ፊታችሁ የወደዳችኋትን ወደእናተ ሳቡ የወደድሽውን ወደራስሽ ጋብዥ ! ተቃቀፉ …አብራችሁ ቡና ጠጡ … ተደዋወሉ ‹ቴክስት› ተላላኩ ! በሚወዷችሁ ሰዎች እቅፍ ውስጥ ስጋችሁ ይድላው !ነፍሳችሁም ደስ ይበለው !ተሳሳሙ …ለመጨረሻ ጊዜ በፍቅር ከተሳማችሁ ስንት ቀን ስንት ወር ስንት ዓመት ሆናችሁ … ኪሳራ !

ህግ ስርዓትና አሉባልታ አትፍሩ …ደግሞ አትንቀዠቀዡ! ብቻ ማፍቀርም መፈቀርም ፈልጉ ..ራሳችሁን ብቻ ቀለል አድርጉት አየሩ ራሱ ወደየት እንደሚወስዳችሁ ያውቃል !…ለምርጫችሁ ብዙ መስፈርት አታስቀምጡለት ….ፈልጉ ተፈላለጉ ያለምንም ወሰን በነፍስም በስጋም ወደፍቅር ድንበር ቅረቡ ….ፀብ አትፍሩ መለያየት አያስጨንቃችሁ …ዘላለማዊ ጥላቻም ሆነ ጊዚያዊ ፍቅር ብሎ ነገር የለም ! አልፎ ሂያጅ ፍቅር የሚባል ነገር የለም ፍቅር ወደየትም አያልፍም …ፍቅር ራሱ መንገዱ ነው ! ተራመዱበት ፍጠኑበት …ብቻ አትቁሙ ! መንገድ ላይ በቆማችሁ ቁጥር ለሌላው እንቅፋት ትሆናላችሁ !

ማህበረሰቡ የሰከነ... ረጋ ያለ... ቁም ነገር …ሁነኛ ሰው… የማይሆን ሰው…የሚሆን ሰው… እያለ ከጫነባችሁ የጉልት ሂሳብ ውጡና እብደታችሁ በሰፈረላችሁ ልክ ከዚህ ነዝናዛ አዕምሮ ተላቃችሁ በልባችሁ ደስታ ኑሩ ! ካለፈ ታሪካችሁ ውጡ …ካለፈ ህመማችሁ አገግሙ … በዘፈን ስም ሙሾ ከሚያስወርዱ ሙዚቃዎች ራቁ ….እንዴ…! …እንዳሰባችሁና እንደተመኛችሁ እስከመቸ ትኖራላችሁ ?! ባለፈ ጥላቻችሁ ከሬዲዮና ከምናምን በተለቃቀመ የመካካድና ተጎዳሁ ተሰበርኩ ታሪክ (ያውም እንደዛም ብለው ማፍቀር ላያቆሙ) በፍርሃት ተሸማቃችሀ ትኖራላችሁ እንዴ ?!

አንዳንዴማ ልብሳችሁን ጣሉ …እራቁታችሁን መኖር ተለማመዱ …እራቁታችሁን ከሆናችሁ ልብስ አይኖራችሁም… ልብስ ከሌላችሁ ኪስ አይኖራችሁም ….ኪስ ከሌላችሁ በኪስ ከሚያዙ ነገሮች ሁሉ ነፃ ናችሁ … ምንም ነገር ልትይዙ የምትችሉት ብቸኛ ነገር ልባችሁ ብቻ ይሆናል … እንደልባችሁ ኑሩ ! የነፍሶቻችሁ ባሉን ላይ የተቋጠሩ ክሮችን ከራሳችሁ የፍርሃት እጅም ይሁን ከሌሎች ሰዎች የቁጥጥር እጅ ላይ አላቁና ወደሰፊው ህዋ ልቀቋቸው በአየሩ ላይ ይንሳፈፉ !

ሸጋ ውሎ ተመኘን


አሌክስ አብርሃም

@telemondo
@telemondo
1.7K viewsFix K, 08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 08:50:51
የስኬታማ አጋርነት ምስጢር
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

በማንኛውም መስክ ውስጥ ከአንድ ሰው ጋርም ሆነ ከአንድ ማህበረሰብ ጋርም ከአንድ ሕብረተሰብ ጋር ስኬታማ፣ የጠለቀና ዘላቂ የሆነ አጋርነት ከፈለጋችሁ ምስጢሩ ሁለት ነው።

1). በጋራ የምትወዷቸውና አጥብቃችሁ የምትከተሏቸው ነገሮች ሲኖሩ
2). በጋራ የምትጸየፏቸውና አጥብቃችሁ የምትርቋቸው ነገሮች ሲኖሩ

እንደ ንግድ አጋሮች አብረን የምንበለጽገው፣ አንደ ባለትዳኖች አብረን ውብ የሆነ ቤተሰብ የምንመሰርተው፣ አንደ አንድ ሀገር ዜጎች አብረን የምንቀጥለውና የምናድገው፣ በጋራ የምንወዳቸውና በጋራ የምንጠሊቸው ሁኔታዎች ሲበዙ ነው።

አስብት እስቲ መሪዎቻችን በሙሉ በጋራ የሰለጠነ ሕብረተሰብ መስራትን ቢወዱና ያንንም ቢከታተሉ! መሪዎቻችን በሙሉ በጋራ አንድነትና እኩልነትን ቢወዱና ያንን ቢከታተሉ...አስቡት

አስቡት እስቲ:- መሪዎቻችን በሙሉ በጉቦ(ሙስና) ላይ የጋራ ጥላቻ ቢኖራቸውና ያንን ቢርቁ...አስቡት! የዚህ እውነት ተግባራዊነት በትዳር፣ በንግድና በራዕይ አጋርነት ውስጥም ቢሆን ያው ነው። አይለወጥም!

አብረን በጋራ የምንወዳቸውና የምንከተላቸው፣ እንዲሁም አብረን በጋራ የምንጸየፋቸውና የምንሸሻቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር እድገታችኔ ፈጣን ይሆናል። እነዚህ ሁለት ነገሮች ሲዥጎረጎሩና ሲበዙ፣ የሕብረተሰብ እድገትም ከዚያው ጋር አብሮ ይዛባል፣ ይጎተታል።
ሀገር አማን ቅጽ ሃያኛ ላይ
https://t.me/hageraman
1.7K viewsSamuel Belete(bama), 05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-11 19:08:49
ለተመራቂ ተማሪዎች
የመመረቂያ መጽሐፍት ሕትመት(Yearbook)
የፕሮግራም የዝግጂታችሁን ቪዲዮ ቀረጻና ቅንብር በጥራትና በተመጠጣኝ ዋጋ
ይደውሉ:-0911871767
1.3K viewsSamuel Belete(bama), 16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-01 10:31:00 #ሀገር አማን መጽሔት
#አስራ-ዘጠነኛ ቅጽ
https://t.me/hageraman
1.5K viewsSamuel Belete(bama), 07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-26 16:44:51 ተራራ ሐውልት ፥ ያቆምኩ በሀገሬ
ነጻነቴን ሰንደቄን ያቆምኩ ፥ ሮም ላይ ተሸግሬ
ያውም እንደፈጠረኝ ፥ በባዶ እግሬ
ኢትዮጲያዊ ነኝ፤

እንደየሱስ እንጂ ፥ በፍቅር
ለመረዘኝ የተንኮል ፥ ስፍር

የማልመች አታጥሉልኝ ባይ
ክታብ ያብሮነት ፥ ሲሳይ ፤

በጅምላ ፥ የማልቀመስ
በችርቻሮ ፥ የማረክስ
ኢትዮጲያዊ ነኝ፤

ጃዋሌ የደንጊያ እጣን ፥ ከርቤ ከጊንር ቋጥሬ
አቦዳይ ጫት ተዘይሬ

ጅማ ካባጁፋር መንደር ፥ ከአዎል በረካ ጀባ
ሶዶ ዋዳ ተዘፍኖልኝ ጎዴ ላይ ፥ ቃጢራ አድሬ

አፋር ላይ በግመል እንገር ምርቃናዬን የሰበርኩ
የሀገሬን ባንዲራ ለአፋር ግመል ማተብ ያሰርኩ

ወሰን የለሽ እግረ ፌንጣ
ሞተ ሲሉኝ ብን ትር የምል፥ ሄደ ሲሉኝ የምምጣ
የቅዠት ምች ህልም ፈቺ ፥ ዳነ ሲሉኝ የማገረሽ
ወሰን ዐልባ እግረ ሞረሽ

ጎጥ አይበቃኝ የሀገር ስፍር
ጎሳ አይገልጠኝ ፥ የሰው ሥዕል
ኢትዮጲያዊ ነኝ።

አመሠግናለሁ ( )
1.9K viewsSamuel Belete(bama), 13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-26 16:44:51 ሀገርን መተንተን
ሙዚቃው:-ምን ቢያዩብሽ
ሳሙኤል በለጠ(ባማ)

ሀገር ገጿ ደም ሲለብስ ፣ ሀገር ኀልውናዋ ሲናጥና ሲደፈርስ ፣ እውነቷ ሲዘለስ ፤ የሀገር ፍቅራችን እልም-እልም ብሎ እንዳይዳፈን ብዙ ገጣሚያን ፣ ሠዓሊያን ፣ ሙዚቀኞች ሀገርን ከነክብሯ ውስጣችን ቀርጸዋል ።

ሁለመናችን(በነፍስም ጭምር) ሀገራችንን 'ምናስበው ኀልው የሆነች ሀገር ስላለን ነው ። ሀገር ለሕዝብ ሐሳብ ናት ፣ ለሯሷ እውነት ናት በሐሳብም በእውንም የሚኖር ኅላዌ በእሳቦትነት ብቻ ከሚኖር ኅላዌ ይበልጣል መቼም ፤ የሀገር ኅልውና ለሕዝብ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው። ካልን ሀገር በእሳቦትም በእውንም አለች ማለት ነው።

ገጣሚና ተርጓሚ ነብይ መኮንን "አገርህ ናት በቃ !" ብሎ በግጥም እስትንፈስ በሰመመን ውስጥ ላለች ለሀገር ሥጋ ኅልውና አብጅቶላታል። "ይቺዉ ናት ዓለምህ፤ ብቻዋን የተኛች ከዓለም ተደብቃ / ልቧን አታዉልቃት አትጨቅጭቃት በቃ / አብረህ አንቀላፋ ወይ አብረህ ንቃ / ወሰብሰብ ይላል ። ግን የአገርን ኀልውና ያረጋግጣል ። ያንተ ናት ፣ አንተም የርሷ ነህ ። ሰው ለሀገር የማይዳሰስ ረቂቅ ነው። ሀገር ለሰው 'ምትታይ መንፈስ ናት ። ግን ሰው ሀገሩን ሲያይ ማንን ነው የሚያየው ?

ሰሞኑን ብዙ ሀገራዊ ስሜት ያላቸው ሙዚቃዎች እየወጡ ነው ። ስለ ሀገር መጻፍና መዝፈን የአገር ወዳድን ጥፍር የማንዘር ጉዳይ እንጂ ተራ ስሜትን መግለጫ ዐይደለም ፤ በዚህ ሚዛን የወንደሰን መኮንን(ወንዲ ማክ) "ምን ቢያዩብሽ" ከብዙ አቅጣጫ ሳጤነው ገዘፍ ያለ ነው። ታሪክ ያወሳል ፣ የተኛን ይቀሰቅሳል ፣ እንደዋዛ የተውነውን እንድናይ ዐይናችንን ይገልጣል ። መቼም ኢትዮጵያ ስልጡን እንደነበረች ለማንም ግልጥ ነው ። አከራካሪም አይደል ። የታሪክ ተማራማሪ ፣ የሥነ-ሰብ አጥኚ ፣ ጸሀፌ ተውኔት እንዲሁም ባለቅኔ ፣ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን በአንድ ግጥማቸው "አስቀድሞ ሰው ሲፈጠር በዘፍጥረት በአፍሪካ አገር፣// እዚህ አሁን ባለንበት፣ በኖርንበት ክልል ነበር፡፡/ቀጥሎም ቋንቋና ፊደል፣ ልሳንም የፈለቀበት፣ / የዓለም የሥልጣኔ እንብርት ይህችው የኛው ጦቢያ ናት፡፡" (ጦቢያ መጽሔት አምስተኛ ዓመት ቁ.3፣ መጋቢት 1989) ብለዋል ።

"...ቃል ኖሮሽ ላትወድቂ ቢሽር እንጂ ኮሶሽ
የዘመናት ትብትብ ቢቆጣጥሩብሽ
አንድ ዐይን ገልጦ እንቅልፍ ምን ያህል ቢፈሩሽ
እነሱ ገብቷቸው ያልገባን ልጆችሽ
ቆጥረን ያልጨረስነው ስንትነው አቅምሽ?"
[ወንደሰን መኮንን(ወንዲ ማክ)]

በመንፈስ ወለምታ(እብደት) ሰበብ ሀገርን አለመተንተን ኗሪ ላይ በቅጽበት ካጋጠመ ሀገርን ከሀገራዊነት ምንጭ ለማፍለቅ ዳገት ይሆንናል ። ሀገርም ለራስ ቅኔ ትሆናለች ገጣሚ አበባው መላኩ "መተንተን" በተሰኘው ግጥሙ ለዚህ ውትብትበት ቅኔ ተቀኝቷል ። "...ራሱ በካበው ወኅኒ - በገዛ ሠምና ወርቁ/ ይቺ ናት...! ሥልጣኔም ያልቻላት / ያበሻ የቅኔ ምትሃት ፤ / ለሌላው እሰወር ብሎ - ለራስ አለመፈታት (እኔ ነኝ ገጽ -73 ) የሕዝብ ሰመመን የሀገርን የተስፋ ጨው ያሟሟል ። ለጋ ቅስምን ይቀነጥሳል ። ነገር ግን ሀገር ቋሚ ቅኔ ናት ለመሆኑ ኢትዮጵያ ምን ሀብት አላት ? ሥልጣኔዋስ ምን ነበር ? ዶ/ር ኃይሌ ወልደሚካኤል በመጽሐፋቸው እንዲህ ይላሉ "የአባይ ሸለቆ የአባይ ወንዝ ውጤት ነው፡፡ የአባይ ወንዝ ደግሞ የኢትዮጵያ ሥጦታ ነው፡፡ የአባይ ሸለቆም የመጀመሪያው ጉልህ ማኅበራዊ ሕይወት የተደራጀበት፣ የተፈጥሮ ክስተቶች ግንዛቤ ያገኙበትና የሰው ልጅ ጉልህ የሃይማኖት፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የሥነ ምግባርና የሣይንስ ሥርዓትና ምሥጢር የለየበትና በየፈርጁ ያደራጀበት ነው፡፡ መደበኛ ግብርና ማለትም ከብት ማርባት፣ አዕዝርት መዝራት፣ የመገልገያና የማምረቻ መሣሪያዎችን  ማምረት፣ አልባሳት መሥራት፣ ከብቶችን በወተት፣ በሥጋ፣ በትራንስፖርትና በእርሻ ምንጭነት መጠቀም፣ በመስኖ እርሻ መገልገል፣ በውሃ መጓዝ፣ በአንድ አምላክ ማምለክ፣ የጽሁፍ ባህል ማመንጨት፣ የሃይማኖት ካህን ማፍራት፣ አስከሬን ማቆየት፣ የጂኦሜትሪን ሳይንስ ማዳበር ወዘተ የመሳሰሉ ሁሉ ብልጭታዎች መጀመሪያ የታዩት በአባይ ሸለቆ ውስጥ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ለመጀመሪያ የሠው ልጅ በተናጠል ሳይሆን በተደራጀ መልክ በተፈጥሮ ጋር በውል የታገለበትና በኋላም የሰው ልጅ ከራሱ ጋር መታገል የጀመረው በአባይ ሸለቆ አካባቢ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡"(እብሮነት በኢትዮጵያ ገጽ 4-5 )
"...ጠላትሽ ሆነና የተፈጥሮ ሀብትሽ
እነሱ ረስርሰው በጥም ቢያቃጥሉሽ
ንስር ሆነሽ ውጪ ታድሷል ጉልበትሽ
[ወንደሰን መኮንን(ወንዲ ማክ)] ይህንን አለመረዳትና ለዓለም አለመተንተንና አለመጠቀም መቼም የዋህነት ነው።

"...ሞሰብሽ ካረጀ ሰበዙ ተስቦ
እንጀራሽ ከማነው 'ሚኖር ተደራርቦ
ሁሉም የኔ ከኔ ለኔ እለብሽ
ከራስ ፍቅር ወድቆ ምጥ ቢያበዛብሽ
መውለጃሽ ተቃርቦ ማርያምም ቀርባሽ
ልናይ ነው ኢትዮጵያዬ ደርሷል ትንሳኤሽ
[ወንደሰን መኮንን (ወንዲ ማክ)] የዑቡምቱ ፍልስፍና እንዲህ ይላል "Umuntu ngumuntu ngabantu" ወደ አማርኛ ስንመልሰው (እኔ እኔ የሆንኩት እኛ እኛ በመሆናችን ነው።) የሚል ትርጉም ይይዛል። ፍልስፍናው ልክ ነው ። ይህንን ዘፋኙ ስላልተረዱለት በጅጉ ተቆጨ ፣ ሀገሩን እንደ ቅርጫ ሥጋ ሲቆራርጧት ባይነዋር ቢሆን ፣ መስቀሏን ተሸከመላት ፣ ሀገሩን በትንሳኤ ጨርቅ ጠቀለላት ትንሳኤዋን ናፈቀ:-

"ነጭ ሽብር ቀይ ሽብር ሁሉንም አየነው
እናቸንፋለን እናሸንፋለን
የቃላት ልውውጥ ስንቱን አጋደለው
የነሱን አሲዘው የኛን እያስጣሉ
ስንቶች ከራስ ንቀው ባዕድ ኮበለሉ
ሶሻሊስት ኮሚኒስት ሁሉንም ቃኘነው
አብዮት ዲምክራሲን ጨፍነን ሞከርነው
ትምርቱን ቁሱንም ሁሉንም ቃረምነው
መዘመን መዋስ ነው ብለን ደመደምነው"
[ወንደሰን መኮንን(ወንዲ ማክ)]

ይህ ትክክለኛ ሂስ ነው ። ያ ትውልድ በደንብ ባደናገረው ፍልስፍና አቅሉን ስቶ ነበር ይህ እውነት ነው። ርዕዮተ ዓለሙም ስንት ለዓይን የሚያሳሱ ወጣቶቻችን ደም-አንጠባጥቦ እንደቀረ የ ያ ትውልድ አባላት ግለታሪካቸው ሲጽፉ ነግረውናል ። ጸጸት የማያውቀው ከትናንት ያደረው ዐቢዮት ለዛሬ አልተረፈም ወይ ? ይህ ስንኝ በጥልቅ መረዳት የተደረደረ ነው ።

"...ስሞ የሸጠውም አሳልፎ ሀገር
በሰላሳ የገዛው መቃብሩን ነበር
ትሸኛለች እንጂ ልጆቿን መርቃ
እናት አትቀብዘ ዘቅዝቃ
እጅ የሚያስነሳ አልቤን የታጠቀው
ለእናቱ ብሎ ነው አልቤን የታጠቀው
ለሀገሩ ብሎ ነው ቃሉን የጠበቀው
እሳት በሰደዱ ገስግሶ በቶሎ
በላይ በላይ ፈጀው ባንዳውን ነጥሎ"
[ወንደሰን መኮንን(ወንዲ ማክ) ] ሀገርን ቸል ማለት ፤ መሸጥ ከዓይን ቋጥኝ ዕንባ ያስፈነቅላል ። ነፍስን ዘቅዝቆ የአገር ፍቅሩን ያፈሰሰውን መዘንጋት አይሆንም ? ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አድማስ 'ማያግደው ጀግንነት ፣ ሞት ፣ ክብር ፣ ገነት ፣ እኔ እኛነት ፣ እንደሆነ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ 'ንዲህ እያለ ያዋዛዋል።

ኢትዮጵያዊ ነኝ!

ማሳዬ ላይ ገበሬ ፥ ምድር አራሽ
ድንበሬ ላይ ወጥቶ ፥ አደር ጠላት ደምሳሽ፤

ከበሬዬ ቀንበር ፥ ከሞፈር
ከወገቤ ላይ ፥ ዝናር፤

ከጀርባዬ ላይ ፥ ዲሞፍተር የማላጣ
ለወደደኝ እንደወደዱ ፥ ከማሳዬ ፍሬ የማልሰስት
ለጠላኝ እንደድፍረቱ ፥ ከጀርባዬ ባሩድ የምግት
እልኸኛ እንደምስጥ ፥ በቁም የምልጥል
ተበድዬ የማልተኛ...
ለደፈሩኝ አድዋን ያህል፤
1.4K viewsSamuel Belete(bama), 13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-30 23:18:32 #ገንዘብ:- እኔን አግኝና ሁሉንም ተዋቸው ይልሀል!
#ጊዜ:- ሁሉንም ተውና እኔን ተከተለኝ ይልሀል!
#ፍላጎትህ:- ሁሉንም ተውና ለኔ ብቻ ተጋደል ይልሀል!

#ፈጣሪ_ግን:- እኔን አስታውሰኝ ሁሉንም እሰጥሀለው ይልሀል።


ዞር ዞር ስንል ከ ማህበራዊ ሚዲያው ያገኘነው ነው ለምን ለብቻዬ አይቼው ልለፍ ብዬ ለናንተ አቀረብኩ

ሰናይ ምሽት


#share join
@telemondo
@xobya
@kurazs
1.5K viewsFix K, 20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-30 16:56:29 #አንድ ስመጥር የአሜሪካን ፕሬዚዳንት በአንድ ወቅት እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ይባላል፦

"ሃያ ስድስት ሰራዊት ስጡኝ፤ ዓለምን በቁጥጥሬ ስር አደርጋለሁ"። ፕሬዝዳንቱ 26 ወታደር/ሰራዊት ያሏቸው የሰለጠኑ በሚሌተሪ ሳይንስ የተካኑ፣ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁ ሰብዓዊያን ወታደሮች ማለታቸው ሳይሆን፣ 26ቱን የእንግሊዘኛ ሆሄያት ማለታቸው ነው። እውነት ነው ፊደላት ከታጠቀ ስልጡን ወታደር ይልቅ ኀያላን ናቸው። የአሜሪካን ልዕለ ኀያልነት ከማንበብና ያነበበቡትን ከመፃፍ ጋር የተቆራኘ ነው።

("የንባብ ባህላችን በንፅፅር ሲፈተሽ" ከተሰኘ የዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ ፅሑፍ የተቆነጠረ)

ሸጋ ቅዳሜ ተመኘን

#share join
@xobya
@telemondo
@kurazs
1.4K viewsFix K, 13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ