Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 14/1/2015 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 29ኛውን ከተማ አቀፍ የት | Addis Ababa Education Bureau

ቀን 14/1/2015 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 29ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ "ትምህርት ለብዘሀ ባህልና ለሀገር ብልጽግና!" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባኤው በጠዋቱ ቆይታ ላይ የአዲስ አበባ ት/ቢሮ የ2014 የትምህርት ዘመን የቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በአቶ ጌታውን ለማ በቢሮው እቅድ በጀት ዝግጅት እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እና የ2014 ዓ/ም የተማሪዎች ውጤት ትንተና ሪፖርት በአቶ ዲናኦል ጫላ በቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አማካኝነት ቀርባል፡፡

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ እና የከተማ አስተዳደሩ ተወማ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጌታቸው ሰጠኝ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ኢንጂነር ጌታቸው ሰጠኝ በመልዕክታቸዉ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ከምን ጊዜውም በላቀ ደረጃ የበኩላቸዉን ሚና እንደሚወጡ እና የትምህርት ልማት ስራዉን ለመደገፍ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጎን የሚቆሙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ማህበራቸው ለከተማ አስተዳደሩ ያቀረባቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ እየተሰጣቸው ያሉ በመሆናቸዉ የከተማ አስተዳደሩን አመስግነው በቀጣይም የከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን ጥያቄዎች የሚሰጣቸዉን ጥያቄዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡