Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 2/13/2014 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ጳጉሜ 2 የአም | Addis Ababa Education Bureau

ቀን 2/13/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ጳጉሜ 2 የአምራችነት ቀንን በተለያዩ መርሀ ግብሮች አከበሩ፡፡

በእለቱ የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላትና ሁሉም ሰራተኞች በተገኙበት በቢሮው ቅጥር ግቢ የተመረቱ የጉዋሮ አትክልቶችን ለሰራተኞች በመስጠት እና የተለያዩ ችግኞችን በመትከል ጳጉሜ 2 የአምራችነት ቀን ተከብራል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እለቱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክክት ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአምራችነት ቀን በተለያዩ መርሀግብሮች በመከበር ላይ እንደሚገኝና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮም ቀኑን በማስመልከት በመስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ያመረታቸውን የጉዋሮ አትክልቶች ለሰራተኞቹ በስጦታ መልዕክ ማከፋፈሉን ገልጸው መጪው የ2015 ዓ.ም አዲስ አመት ለሁሉም የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች የሰላም እንዲሁም በስራቸው ውጤታማ የሚሆኑበት እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የእቴጌ መነን የአካባቢ ፖሊስ አባላትም ተሳተፊ ሆነዋል፡፡