Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 1/13/2014 ዓ.ም 'ጳጉሜን በመደመር' ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በአራዳ ክፍለ ከተ | Addis Ababa Education Bureau

ቀን 1/13/2014 ዓ.ም

"ጳጉሜን በመደመር" ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በአራዳ ክፍለ ከተማ በሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ተቋማትን ፅዱና ውብ የማድረግ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች ምቹ ፣ ፅዱ ፣ ውብና ማራኪ እንዲሁም ሳቢ እንዲሆኑ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል መርሀ ግብር በሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መካሄድ ጀምራል።

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ደ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ፣ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደስ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ በጎነት የሁልጊዜ ተግባር መሆን እንደሚገባዉ እና ትምህርት ቤቶች ፅዱና ውብ እንዲሆኑ ለማድረግ የጽዳት ዘመቻዉ እገዛ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ገልጸዋል።

የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባስተላለፉት መልዕክት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለራሳችን ስንል የምንሰራውና ከሌሎች ጋር አብሮ ለመኖር የሚያስችለን ነው ብለዋል። የበጎ ፈቃድ ተግባር ባንድ ጊዜ ብቻ የሚሰራ ተግባር ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባር ሊሆን እንደሚገባው ነው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የገለፁት።

የጤና ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው የበጎ ፈቃድ ሌሎችን የምንደግፍበት ብቻ ሳይሆን ለራሳችንም ትልቅ ጠቀሜታ የምናገኝበት ነው ብለዋል ።