Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 1/13/2014 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ተቋማትን ፅዱና ውብ የማድረግ መርሃ | Addis Ababa Education Bureau

ቀን 1/13/2014 ዓ.ም

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ተቋማትን ፅዱና ውብ የማድረግ መርሃ ግብር መካሄድ ጀመረ፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን በማስመልከት የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች ምቹ ፣ ፅዱ ፣ ውብና ማራኪ እንዲሁም ሳቢ እንዲሆኑ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል መርሀ ግብር በዛሬው እለት በወረዳ 13 መሪ ህዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አስጀምራል።

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የለሚ ኩራ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን ሮባ፣የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ፍቅሬ ግዛው፣የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና በየደረጃው ያሉ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን በመርሀ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ትምህርት ቤቶች ፅዱና ውብ እንዲሆኑ የሚያደርገው ይህ መርሀ ግብር የተማሪዎችን የመማር ፍላጎታቸው እንዲጨምር ያደርጋል ሲሉ በቀጣይም የማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ የጳጉሜ ቀናትን ጨምሮ ትምህርት ተጀምሮ ተማሪዎች ወደ ተቋማቱ መጥተው መማር እስኪ ጀምሮ ድረስ በክፍለ ከተማው ባሉ ሀያ ሁለት የመንግስት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባሩ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።