Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 1/13/2014 ዓ.ም ' ጳጉሜን በመደመር' በሚል መሪ ቃል የበጎ ፍቃድ ቀን በአዲስ አበባ | Addis Ababa Education Bureau

ቀን 1/13/2014 ዓ.ም

" ጳጉሜን በመደመር" በሚል መሪ ቃል የበጎ ፍቃድ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ መከበር ጀመረ።

በእለቱ በማለዳ በሁሉም ክፍለከተሞች አካባቢን ማጽዳት፤ ችግኝ ተከላና የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎችን ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጁ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችንም ጨምሮ በጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ተገኝተው የበጎ ፍቃድ ቀንን የትምህርት ተቋሙን አካባቢን በማጽዳት አስጀምረዋል፡፡

ዛሬ አመቱን ሙሉ በበጎነት ስናከናውን የቆየነውን ተግባር የምናጠናቅቅበት ዕለት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዕለቱ ከሁሉም በላይ አሸባሪውን ህወሃት በከፈተብን ጦርነት ለኛ መኖር፤ ለኛ ሰላም እና ለሉአላዊነት ሕይወትቱ በመስጠት መስዋዕት እየከፈለ ያለን መከላከያ ሰራዊታችን እንዲሁም ጥምር ጦሩ እየሰጡት ላለዉ በጎነት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ፡፡