Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 24/12/2014 ዓ.ም የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባና የትምህርት ተቋ | Addis Ababa Education Bureau

ቀን 24/12/2014 ዓ.ም

የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባና የትምህርት ተቋማት ቅድመ ዝግጅት በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን አስመልክቶ በዛሬው እለት በአንዶዴ ሁለተኛ ደረጃ ፣ በበሻሌ እና በጎሮ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት የተማሪዎች ምዝገባና የትምህርት ተቋማት ቅድመ ዝግጅት ያሉበት ደረጃ ምን እንደሚመስል ምልከታ አድርጓል።

በዚህም ምልከታ ተማሪዎች ምዝገባ እያደሩ ለመሆኑ ለመመልከት የተቻለ ሲሆን በመጪው የትምህርት ዘመን ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች እየተሰሩ ለመሆኑ በበሻሌ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማየት ተችላል።

በቅድመ ዝግጅቱም ትምህርት ተቋማትን ለተማሪዎች ሳቢ እና ማራኪ እንዲሆኑ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ ለማድረግ ክፍሎችን የማስዋብ ፣ አጥርና ግቢዎችን የማሳመር ፣ ለተማሪዎች ምቹ ያልሆኑ መቀመጫዎችን የመጠገን እና በተቋማቱ ዙሪያ ያሉ አዋኪ ተግባራትን ለማስወገድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን ሲደረጉ እንደቆዩ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በምልከታውም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ጥሩ ጅማሮ ላይ እንዳሉ ለመመልከት መቻሉን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባዩም ወርቁ ገልጸዋል፡፡