Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 20/12/2014 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የትምህ | Addis Ababa Education Bureau

ቀን 20/12/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም እና በ2015 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ጋር ለሶስት ቀን ቆይታ ሲያካሂደው የቆየው ግምገማ እና ውይይት የማጠቃለያ መርሃ ግብር መካሄድ ጀምራል።

በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ዋና እና ምክትል ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በውይይቱ የተሳተፉ ሲሆኑ ተሳታፊዎች ለግምገማዉ እና ውይይቱ በተዘጋጁ የመወያያ ሰነዶች ዙሪያ በቡድንና በጋራ በመሆን ሰፊ ውይይት በማድረግ የማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ላይ መሳተፍ ጀምረዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ማርቺንግ ባንድ ጥሁመ ዜማዎችን በማቅብ ለመድረኩ ድምቀት ከመሆኑም ባሻገር የኢትዩጵያን ብሄራዊ ህዝብ መዝሙርን በማቀረብ መርሀ ግብሩን ለማስጀመር ችለዋል፡፡

ደራሲ ገጣሚ እና ተመራማሪ አበራ ለማ ተገኝተዉ የብዕር ቱሩፋታቸዉን ለመድረኩ አቅርበዋል፡፡

በግምገማ እና ውይይት መርሃ ግብሩም የጋራ የፊርማ መርሃ ግብር የሚከናወን መሆኑን ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችላል፡፡


ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!