Get Mystery Box with random crypto!

የዓለም አካባቢ ቀንን አስመልክቶ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የእግር ጉዞ ተካሄደ:: (ግንቦት | Addis Ababa Education Bureau

የዓለም አካባቢ ቀንን አስመልክቶ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የእግር ጉዞ ተካሄደ::

(ግንቦት 27/2016 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንና በአደስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲሁም ቁም ለኢትዮጵያ የሚባል የአካባቢ ተቆርቋሪ ማህበር በጋራ በመሆን በአለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ግንቦት 28 ቀን የሚከበረውን የአለም የአካባቢ ቀንን አስመልክቶ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የእግር ጉዞ እንዲካሄድ አድርገዋል፡፡

የዓለም አካባቢ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ51ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ31ኛ ጊዜ “የመሬት ማገገምን፣በረሀማነትንና ድርቅን መቋቋም (Land Restoration, Desertification and Drought Resilience)“ በሚል መሪ የከበራል፡፡

የእግር ጉዞው መዳረሻ በሆነው የደቡብ በር አካባቢ ባለፈው ዓመት የተተከሉ ችግኞችን ውሀ በማጠጣት ዝግጅቱ የተጠናቀቀ ሲሆን በፕሮግረሙ ላይ የጀነራል ታደሰ ብሩና የበላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡