Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ለ | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ለሁለት ቀን የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

(ግንቦት 23/2016 ዓ.ም) ስልጠናው በዋናነት ቢሮው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በቀዳማይ ልጅነት ፐሮግራም እያከናወነ በሚገኛቸው የተለያዩ ተግባራትና በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚገኙ የመማሪያ ክፍሎች የኮርነር አደረጃጀትና አጠቃቀም እንዴት መሆን እንደሚገባው ግንዛቤ ለመፍጠር ለክላስተር ሱፐርቫይዘሮች ፤ለክፍለከተማ የዘርፈ ብዙ ቡድን መሪዎች እንዲሁም ለአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ የቀዳማይ ልጅነት ባለሙያዎች መዘጋጀቱን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የስልጠናው ተሳታፊዎች በቀጣይ የቅድመ ዝግጅት ምእራፍ በየአከባቢያቸው በሚገኙ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቀዳማይ ልጅነት ፐሮግራም በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆንም ሆነ የመማሪያ ክፍሎቻቸው የኮሪደር አደረጃጀት ለህጻናቱ ተገቢውን እውቀት የሚያስጨብጡ ሆነው እንዲዘጋጁ ለማድረግ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩዋ አክለውም የስልጠናው ተሳታፊዎች በየትምህርት ቤቱ ለድጋፍና ክትትል ስራ በሚሄዱበት ወቅት ከቀዳማይ ልጅነት ፐሮግራም አተገባበር ጋር በተገናኘ ለሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ ለመመለስ የሚያግዝ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል ስልጠና መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡