Get Mystery Box with random crypto!

'ጽዱና ውብ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች!' በሚል መሪ ቃል በሀምሌ 19/67 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህር | Addis Ababa Education Bureau

"ጽዱና ውብ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች!" በሚል መሪ ቃል በሀምሌ 19/67 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የጽዳት ንቅናቄ ፕሮግራም ተከናወነ፡፡


(አዲስ አበባ ታህሳስ 12/2016 ዓ.ም) በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ስር በሚገኘው ሀምሌ 19/67 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት "ጽዱና ውብ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች!" በሚል መሪ ቃል የጽዳት ንቅናቄ ፕሮግራም ተከናውናል፡፡


በንቅናቄዉ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ይከበር ስማቸው ፣ የጽዳት አስተዳደር ሀላፊ ወ/ሮ ሽቱ ሀይሉ፣ የጽዳት አምባሳደር እማማ ፊሽካ፣ የወረዳው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሀላፊ ወ/ሮ እመቤት ፍቃዱ፣ የወረዳ አመራሮች፣ የትምህርት ቤቱ መምህራንና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ይከበር ስማቸው ትምህርትቤቶችን ለተማሪዎች ምቹና ውብ በማድረግ የመማር ማስተማር ሄደቱ ስኬታማ እንዲሆን መስራት ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው ከጽዳት ስራው ባሻገር መልሶ በመጠቀም የቆሻሻን ሀብትነት ለሌሎች ማሳየት ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


የጉለሌ ክፍለ ከተማ የጽዳት አምባሳደር የሆኑት እማማ ፊሽካ ጤናችን በእጃችን ነው ሲሉ የጽዳትን ወሳኝነት ገልጸው በትምህርት ቤቱ የጽዳት ስራውን የሚያስተባብሩ ሶስት ተማሪዎችን የጽዳት አምባሳደር አድርገው መርጠዋል፡፡


በእለቱ ከተጣሉ ቆሻሻዎች የተሰሩ ጌጣጌጦችና የተለያዩ ቁሳቁሶች ኤግዚሽን መቅረቡን ከጉለሌ ወረዳ ሰባት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡