Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የትም | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የትምህር ጥራትን ለማረጋገጥ በጋራ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡


(አዲስ አበባ ታህሳስ 11/2016 ዓ.ም) በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎች ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛዉ ገብሩ ፣ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የተቋሙ ማኔጅመንት አባላት ፣ የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ጽፈት ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡



በውይይቱ ላይ በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በእውቅና ፍቃድ እድሳት ዳይሬክተር በአቶ ያሬድ ካሳ አማካኝነት ለ564 የመንግስት ትምህርት ቤቶች እውቅና ፍቃድ ለመስጠት በ379 የመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ የተደረገ ምዘና ሪፖርትና የመምህራንንና የትምህርት ቤት አመራሮችን በመመዘን ብቃታቸዉን ለማረጋገጥ የሚያስችል እቅድ ቀርባል፡፡ በተጨማሪም በባለስልጣኑ የኢንስፔክሽን ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ አንዋር ሙላቱ የ2016 ዓ.ም መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች የድንገተኛ ሱፐርቪዥን ግኝትና የ2015 ዓ.ም የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች የክፍል ፈተና ሂደት አተገባበር ዳሰሳ ጥናት በቅደም ተከተል ቀርቦ ውይይት ተካሄዳል፡፡



ሁለቱ ተቋማት በከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ የሚሰሩ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተመላክቷል፡፡