Get Mystery Box with random crypto!

የድሀ ፍቅር              ክፍል 25 ሜላት የቅዱስን መኝታ ክፍል መግባት ተከትላ .ከእና | ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤

የድሀ ፍቅር

             ክፍል 25

ሜላት የቅዱስን መኝታ ክፍል መግባት ተከትላ .ከእናትህ ቤትና ከእዚህ ቤት አንዱን ምረጥ ብላ ስትጮህብኝ ቅዱሴ የመኝታ ቤት በር ላይ ቆሞ ይሰማ ነበረ ...ሳየው ደነገጥኩ ...ሜላትም አየችው .ቅዱሴ ወደ መኝታ ክፍል ገብቶ ቁጭ አለ ተከትዬው ገባሁ .ሊያናግረኝ አልፈለገም... ሜላትም መጣች .እሷንም መልስ ሊሰጣት አልፈለገም....
ቅዱስ አኩርፏል ስንጨቃጨቅ አይቶን አያውቅም ሜላትም ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት ስለነበር በደንብ ተቆጥታ ነበር የተናገረችኝ...መቼም የእናቴን ቤት መተው አልችልም እናቴ ናትና ...የሚስቴንም ቤት አልችልም ሚስቴ የልጄ እናት ናትና ከዛም በላይ አሁን ላለሁበት ትልቅ መሰዋአትነት ከፍላለችና ብቻ ግራ ገብቶኛል ምን እንደማደረግ አላውቅም....
እኔና ሜላት ከቀን ወደ ቀን ጭቅጭቃችን እየባሰ ቅዱስም እናቴጋ መዋል ማደረን ከመረጠ ሰነባበትን .. ቅዱስ ወደ ቤት እንሂድ ሲባል እናቴ እግር ላይ ተጠምጥሞ አልሄድም ይላል..ግራ ገብቶኛል ፍቅራችን እየተናደ እየተሸረሸረ ከመጣ ቀናቶች አለፉ...የተፈጠረውን እየተፈጠረ ያለውን ለእናቴ እነግራታለው....
ሜላት ሁሉን ነገር እርስት አድርጋው ጠጥታ አምሽታ ትመጣለች በጣም ሰለቸኝ በቃ ከአቅሜ በላይ ሆነችብኝ ምን ላድርጋት... ብመክራት ባስመክራትa ምንም ልትስተካከል አልቻለችም ...አንድ ቀን አምሽታ በጣም ሰክራ መጣች ያን ቀን ግን በጣም በሽቄ ስለነበር በቃ እኔ ከዚህ በኃላ እኔና አንቺ አብረን መሆን አንችልም እናቴ ጋ እሄዳለው አልኳትና እናቴ ክፍል አድሬ ጠዋት ሻንጣዬን አዘጋጅቼ ወደ እናቴ ቤት ሄድኩ.....
የእኔና የሜላትን እንደዚህ መሆን ሰው ሲሰማው እጅግ ልገረምበት ይችላል እንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ሲበረክት ፍቅር ይጨምራል ይላሉ ግን ውሽት ነው ገንዘብ ሲበረክት ፍቅር ይጠፋል....እኔና ሜላት በድህነቴ የነበረን ፍቅር እጅ በጣም ደስ ይል ነበር ገንዘብ ስናፈራ ብር ወደኛ ሲመጣ ግን ፍቅራችን ተሸረሸረ ...ልጃችንን እንኳን በፍቅር ማሳደግ አቅቶን ሁለታችንም በተለያየ መንገድ መጎዝ ጀመርን....
ብዙውን ጊዜ ቅዱስ እናቴ ጋ ነው የሚውለው ሜላትም ስትፈልግ ትወስደውና አሷ ጋ አድሮ ውሎ ይመጣል ... እኔና ሜላት አንድ ነገር ተነጋግረናል ከቤት ሰወጣ ...መጠጧን ትታ ወደራሷ ተመልሳ ...ትዳራችንን ለመቀጠልም ሆነ ለመፋታት እንደምንወስን ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ምንም ነገር መወሰን እንደማልችል ነግሪያት ነበር ...
ሜላት ሁሉንም ነገር አየችው ለሳምንታት ያክል እኔ እየተደበቅሁ እያየኃት እሷ እንዳታየኝ እየተጠነቀቅሁ ስከታተላት ከረምክ ..በጣም ተጎሳቁላለች የሚገርመው የያዘቻቸው ጏደኞች እልም ያሉ ጠጪዎች ናቸው አብዛኞቹ እንደ ሹገር ማሚ ነገር ይሰራሉ ..የተረፍት ደግሞ አግብተው የፈቱ ናቸው...ከእነሱ ጋር ሆና ነው እንደዚህ ቅይርይር ያለችብኝ ...
አንድ ቀን ማታ ከሰራ ስትወጣ ተከትያት ሄድኩኝ ሆቴል ውስጥ ስትገባ አብሪያት ገባሁ ...በጣም በብዛት ተሰብስበው ወደ ሚጠጡ ሴቶች ተደባልቃ ቁጭ አለች ...ብርጮቆ አምጥተው ቀዱላት ..በአንድ ትንፋሽ ጭልጥ አድርጋ ጠጣችው አጠጣጧ ያስፈራል ...ሳትሰክር ማናገር ስለነበረብኝ ...ተጠጋኃቸው ስታየኝ ደነገጠች ሁሉንም ሰላም አመሻችሁ አልኳቸው ...እዚህ ምን ትሰራለህ ብላ አፈጠጠችብኝ...ምንም አልሰራም መቼም መጠጥ እንደማልጠጣ ታውቂያለሽ ግን አንዳንድ ነገሮችን አንቺ ያላወቅሻቸውን ላሳውቅሽ ብዬ ነው አልኳት....ሴቶቹ ግራ ተጋቡ እሷም አይኗን አፈጠጠችብኝ.....

ይቀጥላል ......

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @z_zou
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷