Get Mystery Box with random crypto!

የድሀ ፍቅር              ክፍል 24 ከስራ አምሽቼ እናቴ ጋ ሄጄ ማምሸት እያማረኝ ሜላ | ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤

የድሀ ፍቅር

             ክፍል 24


ከስራ አምሽቼ እናቴ ጋ ሄጄ ማምሸት እያማረኝ ሜላቴ ቀድማኝ ከገባች ትናደድብኛለች ብዬ ቅር እያለኝ ወደ ቤት ሄድኩኝ ,...እቤት ስገባ ግን ማንም ሰው የለም ...ቤቱ ጠዋት ትቼው እንደወጣሁት ነው ምንም የተቀየረ ነገር የለውም,...እናቴ ክፍል ስገባ የተኛንበት አልተስተካከለም,..ልብሳችንን አነሳስቼ መኝታውን አነጠፍኩት....
ወደ እኔና ሜላት ክፍልም ስገባ አልተነጠፈም የቀየረችውን ልብስ እንኳን አላነሳችውም... እሱንም አስተካከልኩ ስልኬ ቻርጅ ስላልነበረው እሱን እያደረግሁ ቤቱን ማስተካከል ጀመርኩ.... ማታ እራት የተበላበት ሰአን አልታጠበም,...ብቻ በአጠቃላይ ቤቱ በጣም ያስጠላል ያስፈራል... እሪ ብዬ ብጮህ ደስ ይለኝ ነበር ግን አልችልም.....
ስራውን ሰርቼ ጨረስኩ እራት መስራት ፈለግሁ ግን ቅድሚያ ሜላት ጋ ልደውል ብዬ ስልኬን ከፈትኩት ሜላት ደውላ ነበር ግን ባትሪ ዘግቶብኝ ስለሆነ አላየሁትም ...መልሼ ደወልኩ አታነሳም ትንሽ ልጠብቅ አልኩ ....ግን ማንም የመጣ ሰው አልነበረም ...በጣም ተበሳጨሁ ተናደድኩ ግን በቃ ትዕግስት ይኑርህ እያለች ነው እያቴ ያሳደገችኝ.....
ጠብቄ ጠብቄ ሰው ሳይመጣ የሜላት ስልክ አልነሳ ሲለኝ እናቴ ጋ ደወልኩ ሰላም አልኳት እቤት ማንም እንደሌለ ነገርኳት እራት ቀርቧል ና አለችኝ ...ተነስቼ እናቴ ጋ ሄድኩ .... እናቴ ጋ እራት በልቼ ትንሽ ተጫውቼ ወደ ቤት ተመለስኩ ... እቤት ስመለስ ሜላት ተኝታ አገኝኃት ቅዱስም ተኝቷል .....
ወደ ሜላት ተጠግቼ ሜላት አልኳት ምን ላድርግህ ?አለችኝ በጣም ደነገጥሁ....ስልክ ስደውልልሽ አታነሽም ስጠብቃችሁ ስትቀሩብኝ እናቴ ጋ ሄድኩ አልኳት ...አሪፍ ነው ደክሞኛል ማረፍ እፈልጋለው አለች....ሜላት እየጠየቅሁሽ ነው ስደውልልሽ ስልክ አታነሽም ለምንድነው? አልኳት....
ሜላት በጣም በመቆጣት ከመኝታዋ ተነስታ ቁጭ አለችና በመጀመርያ ስደውል ለምን አላነሳህም አለችኝ.... ስልኬ ባትሪ ዘግቶ ነበር እንደከፈትኩ ስደውልልሽ አታነሺም ሲጨንቀኝ እናቴ ጋር ሄድኩ አልኳት.... አሪፍ ነው እኔም ስልኬን መኪና ውስጥ እርስቼው ስለነበር ነው አሁን ደክሞኛል ደህና እደር ብላኝ ትታኝ ተኛች.....
ነገሩን ላለማክረር ብዬ እኔም ዝም አልኩ ልብሴን ቀይሬ ተኛሁ .....ጠዋት ስነሳ ሜላት ተኝታ ነበር እስከዛሬ እናቴ ነበረች በጠዋት ተነስታ ቁርስ ሰርታ ቅዱስን አልብሳ እኛን የምትቀሰቅሰን አሁን ግን ያ የለም..... እኔም ተነስቼ ቅዱስን ቀስቅሼ ሜላትን ቀሰቀስኳት .... ቅዱስን ልብሱን አልብሼው እኔም ለበስኩ ...ድንገት ቅዱስ አባቢ አባቢ እንደ ትላንትናው እነ እቴቴ ጋ ቁርስ እንበላለን አለኝ?.....
በጣም ደነገጥኩ ሜላት አፈጠጠችብኝ ... አይ ቅዱሴ ዛሬ ማሚ የሰራችውን ቁርስ ነው የምንበላው እሽ አልኩትና ወደ መኝታ ክፍል ገባሁ...ሜላት ተከትላኝ መጣች ...ትላንት በጠዋት ልጄን ይዘህ የሄድከው የት ነው አለችኝ ... እናቴ ጋ.. አልኳት ...በጣም ተበሳጨች ግን እናቴን እንደምወዳት ስለምታውቅ ምንም ማለት አልፈለገችም ነበር.....
ሜላት ቁርስ እስከምትሰራ እኔ መኝታችንን አነጠፍኩ የሚስተካከለእን አስተካከልኩ ...ቁርስ ደርሶ በልተን ቅዱስን ይዜ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ በዛውስራዬ ገባሁ ....ስራ ውዬ ቅዱስን ወንድሜ ከትምህርት ቤት አውጥቶት ስለነበር ቅዱስን ላመጣ ሄድኩ ...በዛውም እራት ሳትበላ አትሄድም በለውኝ እራት በልቼ ወደ ቤት ሄድኩ .... እቤት ስንደርስ ሜላት እራት አዘጋጅታ ጠበቀችን ቅዱስ ጠግቧል እኔም ጠግቤያለው ግን በቃኝ ማለት ስላልፈለግሁ ቁጭ አልኩ..... ቅዱስ ወደ መኝታ ክፍል ሲገባ .. ሜላት በጣም ተቆጥታ ከዚህ በኃላ አንዱን ቤት ምረጥ እሺ ወይ እዚህ ወይ እናትህ ቤት ... ስትል ድንገት ቅዱስ መኝታ ቤት በር ላይ ሆኖ ሲሰማ አየሁት........

ይቀጥላል......

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @z_zou
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷