Get Mystery Box with random crypto!

ወዴት..! ከሰዓታት በፊት አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትቤት እቃ ለማየት ሄጄ ነበር። የረፍት | ውብ ታሪኮች ®

ወዴት..!

ከሰዓታት በፊት አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትቤት እቃ ለማየት ሄጄ ነበር። የረፍት ሰዓት ስለነበር ተማሪዎች በየቦታው ተበታትነው በራሳቸው መንገድ የረፍት ሰዓታቸውን ያሳልፋሉ። ካየኋቸው ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ወንድ እና ሴት ሆነው ጥንድ ጥንድ ሆነው ነበር።

በሀሳብ ወደኋላ ተጉዤ ስለኛ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ማሰብ ጀመርኩኝ እንኳን እንደዚህ ተቀራርበን ልናወራ ልንተሻሽ ስንረብሽ መምህሮቻችን ከቱለት ሴቶች መሃል ያስቀምጡን ነበር ክፈለጊዜው እስከሚያልቅም ጭንቀታችን አይጣል ነበር ።

አሁን ግን የሴት እና የወንድ ቅርርባቸውን ሳይ የሆነ ልክ ያልሆነ ነገርማ አለ አልኩኝ። ገና የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተናን ሳይፈተኑ ፍቅር ውስጥ ገባን ብለው ድርጊታቸው ሁሉ የሚያስጠላ ልጅ ልጅ የማይሸት የድሮውን ልጅነት የሚያስናፍቅ የሆነ ነገር አለው። ልጆቻችንን ለማሳደግ ፈተና ከሚሆኑብን ነገሮች አንዱ የትምህርት ቤት ውሏቸው ይመስለኛል ።

የሃይደር | @WubTarikoch