Get Mystery Box with random crypto!

ህልም እንደ ፈቺው ነው..! ሰውዬው በህልሙ የከተማውን ከንቲባ በአለንጋ ሲገርፈው ተመለከተ። ሲነ | ውብ ታሪኮች ®

ህልም እንደ ፈቺው ነው..!

ሰውዬው በህልሙ የከተማውን ከንቲባ በአለንጋ ሲገርፈው ተመለከተ። ሲነጋ ክስተቱን ለሚስቱ ነገራት። እሷም «አለሚቱ» ለተባለች ጎረቤቷ አጫወተቻት። ወሬው እየተራባ በንፋስ ፍጥነት የደህንነትና ጸጥታ አካላት ጆሮ ደረሰ። ሰውዬውን ምሽት ላይ አፍነው ከቤቱ ወሰዱት። አጓጉል አድርገው ከሰባበሩት በኋላ ማለዳ ላይ ከቤቱ ደጃፍ ፊት ለፊት ጣሉት። እንደ «ጀሶ እንጀራ» ልንኮታኮትለትና «አከመሌ» አደረጉት::

ስቃዩ ብርቱ ስለነበር ቀኑን ሙሉ ሲጮህ ዋለ። የጸጥታ አካላቱ ምሽት ላይ በድጋሜ በሩን አንኳኩ። ሲመለከታቸው «ኧረ ባካችሁ ወላሂ ተጸጽቻለሁ፤ እንዲህ አይነት ህልም ዳግም አልመለከትም» | አላቸው። «አይ አሁን እንኳ የመጣነው በህልምህ ከንቲባውን ስትገርፍ እጆቹን ጠፍሮ የያዘልህ ማን እንደሆነ እንድትነገረን ነው» አሉት። ምን ቢል ጥሩ ነው ... «ሚስቴ እና ጎረቤቴ አለሚቱ ናቸው»

ለማን ምን እንደሚነገር እና እንደማይነገር መለዬት ተስኖህ እንደሚያፈስ ስልቻ ምስጢርህን ሁሉ በየቦታው የምትዘራ ከሆነ በጀመዓ ትሞታለህ። ፌስቡክ ከግቢህ ውስጥ የተወጠረ የልብስ ገመድ ይመስል ሁሉንም የምታሰጣበት ከሆነ አላፊ አግዳሚው ነውርህን እየቆጠረ ቀን ጠብቆ ይሰብርሃል።

@WubTarikoch