Get Mystery Box with random crypto!

ሀብታምና ድኃ..! ሀብታም መሆን ፈለገ ..እናም ሀብታም ለመሁን የሚጠቅሙ ዘዴውች ተብለው የተፃ | ውብ ታሪኮች ®

ሀብታምና ድኃ..!

ሀብታም መሆን ፈለገ ..እናም ሀብታም ለመሁን የሚጠቅሙ ዘዴውች ተብለው የተፃፉ መፅሐፎች እየሰበሰበ ማንበብ ጀመረ ። ሳይኩሉጂስት ዊሊያም ሂል በ መፅሐፍ ላይ" ድኃ የሆነው ሀብታም የመሆን ፍላጎት ሰለሌለን ነው " የሚለውን አባባል ሲያነብ ተናዶ መፅሐፉን ወረወረው ::

ለብቻው አንድ ክፍሉ ውስጥ " እንደኔ ሀብታም የመሆን ፍላጉት ያለው አለ ። ከጫማ በላይ መፅሀፍ የገዛሁት ዕኮ ይህን ፍላጉቴን ለማሟለት ነበር ። ግን ከመፅሀፎቹ ያገኘሁት አይዞህ ፣ በርታ ብቻ የሚሉኝ. ከዛ ግዜ በኃላ መፅሀፍ ማንበብ አቆመ ። ስራውም ከቀን ስራ የማታ ስራ ይሻላል በሚል የሀብታሞችን አኗኗር በቅርብ ለመከታተል ዘበኛ ሆኖ ተቀጠረ ። ሀብታም መሆን ባይችልም ሀብታሞች እንዴት እንደሚኖሩ ማየቱ ደስ አለው :: ለዚህ ሰው ሀብታሞ ማለት ምን ማለት ነው ብትሉት?

ካየው አንፃር ። ሀብታም ስትሆን እንቅልፍ አትተኛም ፣ ሀብታም ስትሁን ትጨናነቃለህ ሀብታም ስትሁን ትጠራጠራለህ ፣ ጥያቄ ታበዛለህ ? " አንዳንድ ሀብታሞች እኔ ሳልተኛ አንተ እንዴት ትተኛለህ ብለው ይቆጡሃል የሚገረመው ይሄ ሰው አይተኛም :: ከለሊቱ 7 ሰኣት ተነስቶ ግቢው ላይ ይዟዟራል ። አንዳንዴ ሌባ መስልህ ከኃላ በዱላ ልታጣድፍው ትችላለህ ። እና እንደዚ ባለሀብቶች ከሌባ ይልቅ እነሱን የምትጠብቅው ... አንዳንዴ እሱ የማይተኛ ከሆነ ለምን እኔን ቀጠረኝ ግን ? በመጨረሻም ሀብታም መሆን ደስ ይላል እንቅልፍ ባትተኛም ቤትህ ፍቅር ባይኖረውም ..

በመጀመሪያው የዘበኝነት ስራው 3 አመት ቆየና ሌላ ሀብታም ቤት ተቀጠረ ። ይሄ ሀብታም ደግሞ አለመተኛቱ እንዳለ ሆኖ በእሱ እንቅልፍ ይቀናል ። ዘበኛው በሀብታሙ ሀብት ሀብታሙ ደግሞ በዘበኛው እንቀልፍ ይቀናናሉ ።

@WubTarikoch