Get Mystery Box with random crypto!

ውብ ታሪኮች®

የቴሌግራም ቻናል አርማ wub_tarikoch — ውብ ታሪኮች®
የቴሌግራም ቻናል አርማ wub_tarikoch — ውብ ታሪኮች®
የሰርጥ አድራሻ: @wub_tarikoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.42K
የሰርጥ መግለጫ

“ማወቅ መልካም ነው ያወቁት ማሳወቅ ይበልጥ መልካምነት ነው።”
ውብ ታሪኮች 𝐎𝐅𝐅𝐈𝐂𝐈𝐀𝐋 𝐏𝐀𝐆𝐄®
ለሃሳብ አስተያየታችሁ👉 @Jemseidbot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-19 22:22:38
አንድ ባሪያ ጌታው ፊት ሁለት ጊዜ ይቆማል። ቀዳሚው
ሶላት ላይ ሲሆን ተከታዩ የፍርድ ቀን ነው። የመጀመሪያው
አቋቋሙን ያስተካከለ ሁለተኛው አቋቋሙንም በእርግጥ
አስተካከለ» [ኢማም ኢብኑል ቀይዩም]

#ለሌሎችም_ሼር_ማድረግ_እንዳይረሱ

@wub_Tarikoch
@wub_Tarikoch
933 views19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:05:47 ለሰው ልጅ ትልቁ ምግብ ተስፋ ነው።....
ከተስፋዎች ሁሉ በላጩ የአላህን የተስፋ ቃል መመገብ ነው።
በብሩህ ተስፋ ጉዞን መቀጠል...
አላህ ተስፋን ይረዝቀን እውንም ያድርግልን።

Ibnu Muhammed

@wub_Tarikoch
@wub_Tarikoch
851 views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:05:11 ፈዳኢል...
(በTeam Huda)
(ክፍል ሀያ ሰባት)
.
መናልን የፈለገችውን ገዝቼላት ወደ ቤቷ ከመለስኳት በኋላ ከጋሼ ጋር ወደ ኢብኑ ዐባስ መስጂድ አመራን። የዐስር ጀመዐ ሰላት ካለፈን ቆይቷል፤ ገብተን በግላችን ሰገድን። ዛሬ የያዝኩት ቁርዐን አልነበረም... ወደ ሆቴልም ተመልሼ መሰናዳት ስለፈለኩ ነገ በጠዋት ቁርዐኖቹን ገዝቼ እንደምንመለስ አቅጄ በጊዜ የመልስ መንገዳችንን ጀመርን።
*
የአንዋር አጎት ደውለውልኝ፤ ገንዘቡን ሰርቆ እንዳላመጣው እየመሰከርኩለት ነበር ወደ ሆቴሉ የደረስነው። አጎቱ ቁምነገረኛ ናቸው፤ በስርዐቱ ከተወያየንና ከተማመንን በኋላ ለሚጠቅመው ነገር እንዲያውለው እንደሚያግዙት ቃል ገብተውልኝ ስልኩ ተዘጋ። ከቃላቸው እንደማይወጡ ተስፋ አደርጋለሁ። ወደ ክፍሌ ገብቼ ልብሶቼንና እቃዎቼን ወደ ሻንጣዬ አስተካክዬ መመለስ ቀጠልኩ፤ ስለጓጓሁ እንጂ ከነገ ወዲያ ለሚደረግ በረራ ነገ ብሰናዳ ይበቃኝ ነበር። አስተካክዬ ስጨርስ እንደሁሌው ለራቢ የውሎዬን ዘገባ አቅርቤ ወደ መኝታዬ አመራሁ።
*
በነጋታው ከጋሼ ጋር ረፈድ አድርገን ነበር የወጣነው፤ የሰሞኑን ድካም ስለተጫጫነኝና የመጣሁለትን ጉዳይ በማገባደዴ ሃሳቤ ቀለል ስላለኝ ከሱብሂ በኋላ ተኝቼ ነው ያረፈድኩት። ጋሼ ደስ ባይላቸውም በኔ ሙግት አርፍደን 4 ሰዐት ከሆቴል ተነሳን።
"ግን አስቀየምኩህ እንዴ ልጄ?" መንገድ ላይ ስንደርስ ጋሼ ጠየቁኝ።
"እንዴ ምን አርገው?" በጥያቄያቸው ግራ እየተጋባሁ።
"ድንገት ለመሄድ የወሰንከው አስቀይሜህ መናገር ከብዶህ ከሆነ ብዬ ነው። ይኸው ጠዋትም ለመውጣት እንደሌላው ቀን አልጓጓህም። ወላሂ ሲጋራውን ትናንት ማታ መልሼ ላልነካው ትቼዋለሁ ሙስዐቤ.... አንተንም ራቢንም የሚያስከፋ ምንም ነገር ማድረግ አልፈልግም።" ድምፃቸው ቀዝቀዝ እንዳለ መለሱልኝ። የገመቱት ነገር ልክ ባይሆንም በሰበቡ ስለተሳካልኝ ደስ አለኝ፤ አልሃምዱሊላህ።
"ኧረ ወላሂ ምንም ያስቀየሙን ነገር የለም። አባቴ አይደሉ እንዴ ጋሼ? ግን ደስ ብሎኛል በወሰኑት ነገር ማሻአላህ።"
"ካልክ እሺ.... ግን ምንም ነገር ቅር ካለህ እንዳትፈራ...እ?"
"ኧረ አብሽሩ....ምንም የለም" ፈገግ አልኩላቸው። ፈገግታቸው በመጠኑ ሲመለስ በመስታወቱ ተመለከትኩት። እንዲ እየተወያየን በቅድሚያ ወደ ኢብኑ ዐባስ ነበር ያመራነው። ቁርዐኖቹን ገዝተን አስረክበን ዱዐ እንዲያደርጉልን ከጠየኳቸው በኋላ ተሰናብተናቸው ወደ ቀጣዩ አድራሻ አመራን፤ ጎሮ።
*
አድራሻውን ለማግኘት አልተቸገርንም፤ ጋሼን መኪናው ውስጥ ትቻቸው በቀጥታ አንዱ ፎቅ ላይ ወዳለው ስቱድዮ ቤት አመሁ።
"ማነው?" ሳንኳኳ ከውስጥ የወጣት ሴት ድምፅ መለሰልኝ።
"አሰላሙ ዐለይኪ የሳራ ቤት ነው?" ከበሩ በመጠኑ ራቅ ብዬ መለስኩላት። ትንሽ ቆይታ በሩን ከፈተችልኝ።
"አቤት ነኝ አዎ፤ ማን ልበል?" በሩን በመጠኑ ገርበብ አድርጋ እንደቆመች መለሰችለኝ።
"ራቢያን ታውቂያታለሽ?"
"ራቢያ... አርክቴክት ተመራቂዋ ናታ? ከሆነች አዎ አውቃታለሁ፤ ጊቢ አብረን ተምረናል። ምነው?"
"ናት አዎ.... ይሄን መልዕክት ልካልሽ ነው።" አውጥቼ ፖስታውን ሰጠኋት። ከፍታ ተመለከተችው....
"ግን..... በሰላም ነዋ? ማለት.... ብሩ.." የምትመልስልኝ ግራ የገባት ይመስላል።
"አዎ በሰላም ነው። ውስጡ የፅሁፍ መልዕክት አስቀምጣልሻለች..." ወደ ካርዱ ጠቆምኳት። ሌላ ጥያቄ ሳትጨምር አውጥታ በዝምታ ማንበብ ጀመረች....
"ሳምሪ.... ኧረ በማሪያም ነይ ቶሎ በይ ላሳይሽ፤ ሃሃሃ.... የሚገርም ፖስት" የምታሽካካ ሴት ድምፅ ከውስጥ ይሰማል። ሳምሪ ነው ያለችው?
"መጣሁ..." መልስ ሰታት ማንበቧን ቀጠለች። "በጣም በጣም አመሰግናለሁ ወንድሜ.... የምር ከጭንቅላቴ በላይ ነው የሆነችው እቼ እብድ። አላህ ይስጥልኝ.... እየበረታሁ ነው፤ እነ ሃዩም እየረዱኝ ነው አልተሰላቸሁም በላት። ኦ ፈጣሪዬ... እኔንጃ ቃላት የሉኝም!" ደስታዋ ከጠበኩት በላይ ነበር።
"መርሃባ.... እላታለሁ እሺ"
"አንቺ ሳምራዊት! ሊያልፍሽ ነው ባክሽ..." ከውስጥ ያለችው ሴት ድጋሚ መጣራት ጀመረች።
"አንዴ....ደርሰሽ እስክትመጪ ባነበው ቅር ይልሻል?" በድፍረት ጠየኳት።
"አይ.... አይለኝም። ሁሉም የሚያውቀው ነው የኔ ጉዳይ... ዘና በል" ሰታኝ ወደ ውስጥ ገባች። የስሟ ነገር ግራ እንደገባኝ ማንበቤን ቀጠልኩ።
.
<<አሰላሙ ዐለይኪ ሳሪ.... ራቢ ነኝ የኔ ቀውስ። ከተመረቅን በኋላ ረሳሽኝ ብለሽ ተነጫነጪ ደግሞ እንደለመድሽው። ኢስላም እንዴት ይዞሻል? እየለመድሽው ነው? ሀያትና መዱን በደንብ ጨቅጭቂያቸው፤ ግራ የገባሽን ሁሉ ያስረዱሻል... እንዳትፋቻቸው። ይገባኛል ሂጃቡ፣ ሰላቱ.... ሁሉም ከባድ እየሆኑብሽ እንደሚመጡ፤ ራስሽን መቀየር ስምሽን የመቀየሩን ያህል ቀላል አይደለም ግን ሁሉም ፈተና ለጊዜው ነው። አሁን ደግሞ ከፊታችን የ2ኛ የፆም ወርሽ እየተጠጋ ነው፤ ተዘጋጅተሽ ጠብቂው። የባለፈውን ከግማሽ በኋማ ስለጀመርሽው ከባድ አልሆነብሽ ይሆናል፤ ግን ከቤተሰብ ርቀሽ የእህትሽንም ሃላፊነት ጨምረሽ ሙሉ ወሩን መፆም ትንሽ ሊያዳክምሽ ይችላል። ግን ተስፋ እንዳትቆርጪ.... ውትወታዎች መቼም ከጀመርሽው የሀቅ መንገድ ወደኋላ እንዳይመልሱሽ። የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ}:- <አምስት ወቅት ሶላቶች፣ ከጁምዐ እስከ ጁምዐና ከረመዷን እስከ ረመዷን በመካከላቸው የሚፈፀሙ ወንጀሎችን የሚያስምሩ ናቸው። ይህም የሚሆነው ከታላላቅ ወንጀሎች ከታቀቡ ነው።> ብለውን ነበር። አደራሽን ሰላትሽንም ፆምሽንም ዲንሽንም አጥብቀሽ ያዢ። ላለፈው ሁሉ እንዲምርሽ ጠይቂው፤ የወደፊቱንም እንዲያቀልልሽ ለምኚው። የመጪውን ወር እንድትጠቀሚው ቢያንስ የቤት ኪራይሽን እኔ ልቻል... ግን ከመስራት ቦዝኚ አሉሽ ደግሞ ሰነፎ። እህትሽንም ጊቢ ሄዳ ሳትርቅሽ ካሁኑ በትንሹ ስለ ኢስላም አስተምሪያት። በቅርቡ መጥቼ በአካል እስክንገናኝ ለኔም ለሙስዐብም (ይሄን የሰጠሽ ሰው፤ ባለቤቴ...ሃሃሃ) ዱዐ አድርጊልን። ወሰላሙ ዐለይኪ ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።>>...የመልዕክቱ ማብቂያ ነበር። ኢስላም ላይ ተፈጥሬ በማደጌ ከሷ አንፃር የቀለልኝን ፈተናና ረዥም ጉዞ ሳስበው የመታደል ስሜት ወረረኝ።
.
ውስጥ ከገባች በኋላ ከእህቷ ጋር ውይይት የጀመሩ ይመስላል፤ ትንሽ ከጠበኳት በኋላ አንኳኳሁላት። ከሷ ቀደም ብላ ቅድም ስትጣራ የነበረችው ሴት መጣች፤ ሂጃብ አለበሰችም... ስገምት እህቷ ናት።
"አንተ ነህ ሙስአብ? ውይ እግዜር ያክብርልን የምር በጣም መልካም ሰው ነህ። ፆማቹን የተባረከ ያርግላቹ..." ተፍለቀለቀች፤ እድሜዋ ገና ትንሽ ናት። ውስጥ የቆየችው እያስረዳቻት እንደነበር ተረዳሁ።
"ቤዛ አንቺ... ቀውስ! ሂጂ ግቢ።" እንደመደንገጥ እያለች፤ ሳራ። "ይቅርታ ወንድሜ..."
"ኧረ ችግር የለውም፤ በቃ ልሄድ ነው... የባንክ ሂሳብ ካለሽ ብታስገቢው..."
"እሺ አያሳስብም። እምም.... ካላስቸገርኩህ ስትመለስ ራቢን እቅፍ አርገህ ሳምልኝ... ማነው ሰላም በልልኝ ለማለት ነው።" የተናገረችው ልክ ይሁን አይሁን ከማብሰልሰል ጋር ነበር የምታወራው።
"ሃሃህ... መርሃባ፤ አደርሳለሁ። ሰላም ዋሉ" ተሰናብቻት ደረጃዎቹን መውረድ ጀመርኩ፤ ወደ ጋሼ መኪና።
.
.
ይቀጥላል...

@wub_Tarikoch
@wub_Tarikoch
711 views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:04:00 ፈዳኢል...
(በTeam Huda)
(ክፍል ሀያ ስድስት)
.
ዙህርን አልፋሩቅ መስጂድ ከሰገድን በኋላ ወጥተን ቁርዐኖቹን ገዝተን ተመለስን። ለአስተባባሪዎቹ ሰጥተናቸው ዱዐ እንዲያደርጉልን ከጠየኳቸው በኋላ ከመስጂዱ ወጥተን ወደ ምሳ አመራን። ራቢ የላኩላትን መልዕክት አንብባ በጣም ተደስታለች.... መደሰቷ የኔን ደስታ እጥፍ አድርጎታል። ምሳ ከበላን በኋላ ከ2 ቀን በኋላ ትኬት የማገኝበትን ሁኔታ በስልኬ ማፈላለግ ጀመርኩ።
"እሺ.... እና ቀጣይስ ወዴት ነው?" ጋሼ ነበሩ።
"ምኑ?"
"ሃሃህ ዛሬ ቀልብህ የለም.... ጉዞአችን ነዋ።"
"እእእ... ወደ ገርጂ እንሂድ። እዛ አንድ የምንሰጠው ሰው አለ.... በዛውም በጊዜ ወደ ሆቴል ልመለስና እቃዎቼን ላዘገጃጅ፤ ለዛሬ 2 ቀን የአየር ቲኬት አግኝቻለሁ።"
"ላንተ? ቀንህ ደረሰ እንዴ?.... 10 ቀን መች ሞላን?" በእጃቸው ያሳለፍነውን ቀን መቁጠር ጀመሩ።
"አይ ሳይሆን እኔ ስለቸኮልኩ ነው ጋሼ.."
"ጥሩ እሺ ካልክ.... በቃ እንሂድ በጊዜ" ወደ መኪናው ቀደሙኝ።
*
ዐስር ከመድረሱ በፊት ወደ ገርጂ ደረስን፤ ያሰብኩትን ያህል ቅርብ አልነበረም። ወደ አድራሻው ደርሰን ከመኪናው ወረድኩ፤ ጋሼ እዛው እንደሚጠብቁን ነገሩኝ። ቤቷ ትንሽዬ የቀበሌ የመሰለች ቤት ናት።
"ማኑ?" ከቤቱ ውስጥ የሰማነው የትንሽ ልጅ ድምፅ ነበር።
"አሰላሙ ዐለይኩም... ወ/ሮ ኸዲጃን ፈልገን ነበር" መልስኩላቸው። ለዲቃዎች ምንም ድምፅ ሳንሰማ ከቆምን በኋላ አንዲት ትንሽዬ ልጅ በሩን ከፈተችልን። ለንፃት የረበ ቅላትና ፀጉሯ ለስላሳ ከመሆኑ ኢትዮዺያዊ አትመስልም።
"ኡሚ አሊች.... ምን ፈልገህ ኑ?" በሚኮላተፍ አፏ ጠየቀችኝ።
"ጥሪያት አንዴ.... መልዕክት ሊሰጥሽ ነው በያት"
"ምድኑ ምልክት?.... ኡሚ ሰገደች ኑ ዐስር። ለኔ በል..." ባለችነት ቆመች። ምን ብዬ እንደማስረዳት ግራ ገባኝ። እዛው እንደቆምኩ እናቷ ሰግዳ ጨርሳ አንድ አነስ ያለ ፀጉሩ ግምባሩ ላይ የተደፋ ወንድ ልጅ አቅፋ መጣች። ፊቷ በኒቃብ ተሸፍኗል... ቢሆንም የሌላ ሃገር ዜጎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ በቂ ነበር።
"አፍወን.... ኸዲጃ ነሽ? ራቢያ ሱልጣን ልካኝ ነበር የመጣሁት..." ትረዳኝ አትረዳኝ ባላውቅም ዝም ብዬ ነገርኳት። ወደ ልጇ ጎምበስ አለች.... በአረብኛ ታዋራት ጀመር፤ ሲመስለኝ እየተረጎመችላት ነው። ሃዲሶችና ቁርዐንን ለመረዳትና መፅሃፎችን ለማንበብ የሚያበቃ የአረብኛ እውቀት ቢኖረኝም የነሱን ፈጣን ንግግር መልቀም ግን ከባድ ነበር።
" 'ማኑ ራቢያ?' አለችህ ኡሚ" ልጅቷ መለሰችለኝ። በዚህ አይነት እንዴት እንደምንግባባ ግራ ስለገባኝ ለራቢ ደወልኩላት። ኢሞ እንድገባ ነገረችኝና በቪድዮ ኮል አገናኘኋቸው። ራቢ ስታዋራት የኸዲጃ ድምድ የለቅሶ ሲቃ ይዞ ሲቀየር ይደመጥ ነበር። ምን እየተባባሉ እንደሆነ ለማወቅ ብችል ተመኘሁ። ራቢ አዋርታት ስትጨርስ ፖስታውን እንድሰጣት አዘዘችኝ፤ ስልኩን ወደ ኪሴ ከመለስኩ በኋላ አውጥቼ ሰጠኋት። ከኒቃቧ ስር እንባዋን እየጠረገች ተቀበለችኝ። ቀጥላም እየመረቀችን ልጇን ወደኔ ስትጠቁማት አየኋት።
" 'ጀዛከላህ በሊው' አለች ኻሎ.... 'ምንም አልንብረም... ብዙ ማታ አልቅስኩ... አንተ መጣህ... አልሃምዱሊላህ' ትላሊች" ልጅቷ በሚሰባበር አማርኛ የእናቷን ንግግር ልታስረዳኝ እየጣረች። " 'አላህ ሀብታም አያርግህ... ደሞ በኋላ ምንም የሌለው አያርግህ...' " መተርጎሟን ቀጠለች።
"ከየት ሀገር ናቹ?" ስትጨርስ ጠብቄ ጠየኳት።
"ሱሪያ.... ባለፈው ለት 2 አመት መጣን እዚ። ባባ አላይርሃሙ ቀረ ሱሪያ" ክፍት ሲላት ተመለከትኳት፤ አሳዘነችኝ። የተቀረውን ታሪክ ሳልጠይቃት በራሴ ግምት ሞላሁት።
"ደብዳቤ ታውቂያለሽ?.... ወረቀት? ኦ ሪሳላ! ብሩ ጋር ሪሳላ አለው በያት..." ንግግሬን እንደሰማች ነገረቻት። ፖስታውን ከፍታ መመልከት ስትጀምር እንደተረዳችኝ ገባኝ። ከፍታው አውጥታ ማንበብ ጀመረች.... በድጋሚ አስለቀሳት። በድጋሚ ለልጇ ወደኔ ጠቆመቻት...
" 'አላህ ሀገራቹ ያቁያቹ.... ሰላም ያርጋቹ። ኢንሻአላህ ለይል ቁሚ ዱዐ አረጋሉ... እምም... ረመዳንም ሸዋልም ሶም አላ-ይባሪክፊህ አሊች' "
"ሃሃህ አሚን። ኡሚን አንዴ ስጪኝ በያት..."
"ሪሳላ?"
"አዎ...ሃሃህ" ወደ እናቷ መለስ ብላ ከጇ ተቀበልላ ሰጠችኝ። በአረብኛ ነበር የተፃፈው.... በአማርኛ እንደተረዳሁት ከሆነ እንዲህ ይላል...
.
<<አሰላሙ ዐለይኪ እህቴ ኸዲጃ.... መናልና ዐምር እንዴት ናቸው? ወላህ ናፍቀቹኛል። አይዞሽ ሶብሪ የአላህ ፈረጃ ቅርብ ነው.... ወደ ሃገራቹ በሰላም የምትመለሱበት ያድርግላቹ። ረመዳን በሰው ሃገር የራስን ሃገር ያህል እንደማይሞላ ይገባኛል፤ ቢሆንም ከዒባዳ ሳትዘናጊ ታትረሽ ጨርሺው። ከቻልሽ የሸዋልንም 6 ቀናት ጨምረሽ ፁሚው። የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ} እንዲህ ብለዋል:- <ረመዷንን የፆመና እርሱን አስከትሎም ከሸዋል ወር ውስጥ ስድስት ቀናትን ያከለ ዓመቱን ሙሉ እንደ ፆመ ይቆጠርለታል>። አቡ ዐምር በጀነት እንዲጠብቅሽ ዱዐ አደርጊለት፤ አላህ ከሷሊህና ዐቢድ ባሪያዎቹ ይሰማል። በቻልሽው መጠን ቋንቋ ለመልመድ ሞክሪ፤ እነመናልም እንዲለምዱ አድርጊያቸው። በዚህ ረመዳን ከሙስሊሞች ጋር ይበልጥ ተቀላቀይ፤ ሙስሊም የሙስሊም ወንድሙ አይደል? ከየትም ሃገር ቢሆን አይተዉሽም። በማብሰል ሙያሽ ስራ የምታገኚበት እንዲሆን ዱዐ አድርጊ፤ ሰበቡን አድርሺ። ልመናሽን ወደ አላህ ብቻ መልሺው.... ምላሹ ቅርብ ይሆናል ኢንሻአላህ። መጥቼ እስካያቹ ድረስ ለኔም ለሙስዐብም ዱዐ አድርጊልን። ወሰላሙ ዐለይኪ ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።>> የመልክቱ ማብቂያ ነበር። ወረቀቱን መለስኩላት፤ በድጋሚ ከመረቀችን በኋላ ወንዱን ልጇን እንዳቀፈች ወደ ውስጥ ገባች። ልንሄድ ስንል መናል ከኋላዬ ተከትላኝ ስትጠራኝ ሰማኋት፤ ተመልሼ በሷ ቁመት በርከክ ብዬ አዳምጣት ጀመር።
"ኻሎ.... ንዳንተ መሆን ፈልጋሉ.... ባባ ሰደቃት ይሰጣል... አንተም ይሰጣል... ኒም መስጠት ፈልጋሉ ረቡናስ ወ ኡሚ ደስ እንዲሉ" ጥያቄዋ አንጀት የሚበላ ነበር። ምን እንደምላት ግራ ገብቶኝ ጥቂት ካሰብኩ በኋላ ባለፈው ከዳዕዋዎቹ አንዱ ላይ የሰማሁት ሃዲስ ትዝ አለኝ።
"ትቺያለሽ.... ዚክር አድርጊ። ዚክር ታውቂያለሽ?... ተስቢሕ (ሱብሐነላህ)፣ ተሕሚድ (አልሃምዱሊላህ)፣ ተሕሊል (ላ ኢላሀ ኢለ ላህ)ና ተክቢር (አላሁ አክበር).... ሁሉም ሰደቃ ናቸው ብለዋል ነቢና ሙሃመድ {ሰ.ዐ.ወ}። እንደ ኡሚ ሁኚ.... እሷ ተህሚድ ስታደርግ ሰማሻት አይደል? አላህ በጣም ይወዳታል! በጣም ብዙ ብዙ ዚክር ስትዪ ጀነት ውስጥ ብዙ ብዙ ዛፍ ይኖርሻል። ዛፍ ታውቂያለሽ?"
"አዉ.." ጭንቅላቷን ላይና ታች እየነቀነች።
"ማሻአላህ ጀነት ውስጥ ትልቅ ቡስታን ያለሽ ልዕልት ትሆኛለሽ። ጀነት የሚገባው ደግሞ ኡሚን የማያናድድ ነው። ተስማማን?" በድጋሚ ጭቅላቷን ነቀነቀችለኝ። "እምም... አሁን ኡሚን አስፈቅጃትና እሺ ካለች ብስኩት ገዝተን እንመጣለን ጠይብ?" እጄን ዘረጋሁላት።
"ጠይብ" መስማማቷን ለመግለፅ እየሳቀች እጄን መትታኝ ወደ ቤቷ ሮጠች። እስክተመለስ ቦታው ላይ ያሉትን ዛፎች እየተመለከትኩ መጠበቅ ጀመርኩ፤ ሳይታወቀኝ በሰደቀችኝ ፈገግታ እኔም ፈገግ እያልኩ ነበር።
.
.
ይቀጥላል...

@wub_Tarikoch
@wub_Tarikoch
601 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 21:28:07 ፈዳኢል...
(በTeam Huda)
(ክፍል ሀያ አምስት)
.
.
አቶ ሰዒድ ቤት ከተስተናገድን በኋላ እሱን ጦርሃይሎች አካባቢ ወደሚሰራበት የመንግስት መስሪያቤት ሸኝተነው ወደ ሁለተኛው ቤት አቀናን። ሰዐቱ ሳናስበው ነጉዶ 5 ሰዐት እያለፈ ነበር።
"እሺ ጎረምሳው... እና ደስ አለህ..." ጋሼ ነበሩ፤ አቶ ሰዒድ ወርደው መንገዳችንን እንደጀመርን ጠየቁኝ።
"ለምኑ?"
"የሚስትህን ደብዳቤ ስላነበብክ... ሃሃሃ"
"እንዴ ለኔ ብለው ነው እንዴ የተቀበሉት?" በመገረም ጠየኳቸው።
"እናስ? አላነበብኩትም ባይገርምህ.... ወደ ፖስታው ሲከቱት ፊትህን ጥለኸው ስለነበር እንዲሞላልህ ብዬ ነው...ሃሃህ" መልሳቸውን ስሰማ ሳቅ ብዬ ለጥቂት ደቂቃዎች ዝም አልኩ።
"ጋሼ ግን.... ያን ያህል ያስታውቅብኛል እንዴ?" ልብ ስላሉኝ እንደማፈር ብዬ ጠየኳቸው።
"ሃሃሃህ.... አይ አብሽር። እኔ ስከታተልህ ስለነበር ነው.... ሁሌ ስለሷ ከሰማህ በኋላ ፊትህ በፈገግታ እንደበራ ነው፤ አልፈንበትም የለ?... 'እስኪ ዛሬስ ደፍሮ ይጠይቃል አይጠይቅም' እያልኩ ዝም ስትል አሳዘንከኝ። ደግሞ አብሽር እ?.... ሰዒዴ ሲያስበረግግህ ነው እንጂ ፈታ ያለ ሰው ነው።"
"ሃሃህ እሺ ጋሼ። አላህ ይስጦት ወላህ ትልቅ ነገር ነው ያደረጉልኝ.."
"ኧረ አያስፈልግም.... ብዙ ይገባቿል ለናንተ" ፈገግ እንዳሉ ማሽከርከራቸውን ቀጠሉ።
*
ከጋሼ ጋር እየተጨዋወትን ወደ አድራሻው ደረስን። አድራሻው ግራ ስላጋባን ራቢ ከቀናት በፊት ወደላከችልኝ ስልክ ቁጥሮች ተመልሼ የሪድዋንን ስልክ ቁጥር መፈለግ ጀመርኩ። አግኝቼው እንደደወልኩለት አቅጣጫውን እየመራን ወደ ቤቱ ደረስን።
.
"ተቀመጡ.... ቆይ ሻይ ልጣድላቹ።" ቤቱ እንደገባን እኛን ለማስተናገድ መንጎዳጎድ ጀመረ። ትህትናው መረጋጋቱ.... ደስ የሚል ሰው ነው። ቁመቱና ፊቱን የከበበው ጥቁር ፂም የደስደስ አላብሰውታል። ቤቱ ሁለት ክፍል ናት፤ ከውስጥ ባለቤቱ ፥ ሰሚራ፥ እንደተኛች ነገረን፤ ትናንት ማታ ወልዳ ገና ጠዋት መግባቷ ነው።
"ኧረ አያስልግም በአላህ.... አትቸገር።"
"ኧረ አብሽሩ መቸገር የለውም...ሃሃህ" መልሶልን ወደ ውስጥ ገባ። አንድ እቃ የጠፋው ይመስላል... "አፍወን... ጠዋት ጎረቤታችን ስለነበረች ቁርስ የሰራችላት እቃዎቹ ተዘበራርቃዋል። ሰሙን እንዳልቀሰቅሳት ስለደከማት..."
"ኧረ አያስፈልግም ወላሂ፤ አንቆይም እኮ አብሽር አረፍ በል.... ራቢያ መልዕክት ልካን ለማድረስ ብቻ ነው።"
"ወላሂ? ኸይር እሺ አፉ በሉኝ፤ ሳልዘጋጅ ነው የመጣቹት።" ከፊትለፊታችን ተቀመጠ። ጋሼም የሚያውቁት አይመስለኝመም፤ እንደኔው በዝምታ ተቀምጠዋል። "ራቢያ የአክስቴ ፋጢማ ልጅ ናት አይደል?"
"አዎ እሷ ናት... እኔ ሙስዐብ እባላለሁ ባለቤቷ ነኝ።"
"ኦ ባረከላህ። ድሮ መስጂድ ጀመዐ ላይ አሚር ሆና ነው የማውቃት እሷን፣ ሰሙ ጋር በደምብ የተሻለ ይተዋወቃሉ። አክስቴ ፋጢማ ግን እንደ እናቴ ናቸው.... ጥሩ አማት አግኝተሃል ማሻአላህ።"
"ሃሃህ ተባረከላህ.... ይሄን እንድሰጥህ ነው የላከችኝ።" ፖስታውን አውጥቼ ሰጠሁት። ከፍቶ ካየው በኋላ የሚሰጠን ምላሽ ግራ የገባው ይመስላል፤ ሃያዕ የሚይዘው አይነት ሰው ነው። መመለሱም መቀበሉም እኩል የከበደው መሆኑ ያስታውቃል። "ውስጡ የፅሁፍ መልዕክት አለው..." ሳይመልስልኝ በፊት ከሃሳብ ከገላገለው ብዬ አከልኩበት። ወደ ፖስታው መለስ ብሎ ካርዱን ካገኘው በኋላ ለደቂቀዎች በዝምታ ሲያነብ ቆየ።
"እምም... መርሃባ እሺ ኢንሻአላህ በላት። ጀዛኩሙለህ፤ በኸይር እጥፉን ይመልስላቹ። ደግሞ አብሽሪ በሰላም ተገለግላለች በላት፤ ገና ስላልተሰናዳን ለማንም አልደወለችም ሆና እንጂ ረስታት አታውቅም።"
"ኸይር እሺ ኢንሻአላህ። ካላስቸገርኩህ አንዴ ካርዱን..."
"ኦ ትችላለህ አብሽር..." የማመንታት ጥያቄዬን ሳምጨርስ ፈጠን ብሎ አቀበለኝ። በዝምታ ለራሴ ብቻ ማንበብ ጀመርኩ...
.
<<አሰላሙ ዐለይክ ሪድዋን.... ራቢያ ነኝ የፋጢማ ልጅ። ሃጃዎች ይዘውኝ ለሰሙ ሳልደውልላት ብዙ ቆየሁ ይመስለኛል፤ አፉታሽን በልልኝ። ማሻአላህ ቤታቹ በቅርቡ በልጅ ድምፅ ይበልጥ ሊሞቅ ነው፤ አላህ በሰላም ይገላግላት። ገንዘቡ ለልጃቹ ከአክስቱ የተላከለት ትንሽ ስጦታ ነው.... ስለዚህ ያለመቀበል መብቱ የናንተ አይደለም። መጪው የራህማ ወር ዱንያ ሳትይዛቹ አብራቹ ለዒባዳ ደፋ ቀና የምትሉበት ያድርግላቹ፤ መቼስ ላንተ ስለ ረመዳን ልቅና አማና አልሰጥህም። ግን አደራህን ሰሙን ከአባቷ ጋር ሰላም እንድታወርድ ገፋፋት። አውቃለሁ በጣም እልኸኛ እንደሆነች.... ግን እርግጠኛ ነኝ አሁን ልጅ ሊኖራቹ ስለሆነ አይጨክኑም። ነቢና {ሰ.ዐ.ወ}:- <ስራዎች ዘወትር ሰኞና ሀሙስ ይቀርባሉ። አላህ በርሱ ላላሻረኩ ሰዎች ሁሉ ምህረትን ይለግሳል። በርሱና በወንድሙ መሃከል ጥልና መቀያየም ያለበት ሰው ሲቀር። 'እነዚህን ሁለቱንስ እስኪታረቁ ድረስ ተዋቸው' ይላል> አይደል ያሉን? ያንተንም የሷንም የቤተሰቦቿንም መልካም ስራ አየር ላይ አታስቀሩት። ዝምድናን ቀጥሉ እየተባለ አመት በድርቅና ስትቆይ ዝም አትበላት.... <ልጅ ነሽ ለአፉታ ቅደሚ> ብለህ ተቆጣት። ካንተ ትሰማለች ኢንሻአላህ.... እሷም ካላደረገችው አንተ ወደነሱ ሄደህ አፉታ በመጠየቁ ቅደም። በምትወልድ ጊዜ ስራ እየቆየህ ብቻህን አትሸፍነውም፤ እሷም መጉደላቸው የሚታወቃት ያኔ ነው። አደራ እሺ በራህማን? በቅርቡ በአካል እስክዘይራቹ ለኔና ለሙስዐብም ጭምር ዱዐ አድርጉልን። ወሰላሙ አለይክ ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።>> የመልዕክቱ ማብቂያ ነበር። አንብቤ መለስኩለት.... ስላነበብኩት ቅር የተሰኘ አይመስልም።
.
ካርዱን ወደ ፖስታው እያስገባው እያለ የህፃን ልጅ ለቅሶ ከውጥ ተሰማ.... ይቅርታ ጠይቆን ወደ ውስጥ ገባ። ትንሽ ቆይቶ በእጆቹ መሃል ትንሽዬ በማቀፊያ የተጠቀለለ ልጅ ይዞ ተመለሰ.... ገና ሲያዩት ያጓጓል። የልጆች ነገር ሞቴ ነው፤ እንዳቅፈው ጠየኩት.... አቀበለኝ።
"ማነው ስሙ?" ጠየኩት...
"አላወጣሁለትም፤ ገና እያሰብንበት ነበር..." በፈገግታ እየተመለከተው። ከጥቂት ዝምታ በኋላ አንድ ሃሳብ ብልጭ አለብኝ...
"አህመድ!.... ቅር ካላለህ አህመድ በለው።"
"ማሻአላህ አህመድ.... በጣም ጥሩ ስም ነው። መርሃባ.... አህመድ ተብሏል፤ ሰሙም ቅር የሚላት አይመስለኝም።" በደስታ መለሰልኝ። ስልኬን አውጥቼ ለራቢ ለመላክ ፎቶ ካነሳሁት በኋላ መለስኩለት። "ሰማህ ሃሙዲ? አጎትህ ሙስዐብ አህመድ አለህ እኮ?.... አሚን ውለታ መላሽ አመስጋኝ ያርገኝ... ሹክለን አትለውም? ሃሃህ..." ከልጁ ጋር እያወራ ሳቅ አለ፤ እኛም አብረነው ሳቅን።
ያነሳሁትን ፎቶ፤ 'መብሩክ.... የሸይኽ አህመድ ምትክ.... ሌላ አህመድ ተወልዷል...' ከሚል caption ጋር አያይዤ ለራቢ ላኩላት፤ የባለፈውን ዜና የካስኳት ያህል ደስ አለኝ።
"ኸይር በቃ እንሂድ... በዱዐ አትርሱን።" የሃሙዲን ትንሽዬ እጅ ስሜ ለመሄድ ተነሳን፤ ሰሚራን ብቻዋን ትተህ ባንክ እንሂድ ማለቱ ትክክል ስላልመሰለኝ አላነሳሁም። ሊሸኘን ቢፈልግም አራስ ልጅ ስለያዘ አይሆንም ብለን ተሰናብተነው ወደ መኪናችን አመራን።
.
.
ይቀጥላል...

@wub_Tarikoch
@wub_Tarikoch
603 views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 09:04:10 ይቅርታ እስከዛሬ ባለመለቀቁ
530 viewsedited  06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 09:03:58 ውብ ታሪኮች pinned «ፈዳኢል... (በTeam Huda) (ክፍል ሀያ ሁለት) . . ከነጋሽ ቃሲም ቤት ስንመለስ ቁርዐኖቹን ገዝተን ወደ ሳባ መስጂድ አመራን። ቁርዐኖቹን ከሰጠናቸው በኋላ ዱዐቸውን ተቀብለን ዙህርን እዛው በጀመዐ ሰገድን፤ የተቀራረቡ ሰፈሮችን በማገናኘቴ ሰዐታችንን ቆጥበናል። ከዙህር በኋላ ወጥተን ምሳችንን ተመገብን..... ቀጣዩ ቤት ጋር እንሂድ ወይስ እስከ መግሪብ እዚሁ እንጠብቅ የሚለውን ለመወሰን ትንሽ ተወዛግቤአለሁ፤…»
06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 09:03:47 ፈዳኢል...
(በTeam Huda)
(ክፍል ሀያ አራት)
.
ከእህቴ ጋር በስልክ እያወራን ወደ ክፍሌ ደረስኩ። ከቤተሰቦቼ ይልቅ ራቢ ጋር ብቻ መደዋወል መብዛቴን እያነሳች ስታሾፍብኝ ቆየች። ተሰነባብተን ስልኩን ከዘጋሁት በኋላ ከሷ ንዝንዞች ጋር የተፈጠረብኝን ሃሳብ ማመላለስ ጀመርኩ። ከመስጂድ ከወጣን ጀምሮም ጭንቅላቴ ላይ ሲመላለስ ነበር የቆየው። በጎበኘኋቸው ሰዎች ፊት ላይ ያየሁት ደስታ፣ በሚዋደዱት ባለትዳሮች ላይ ያየሁት ፍቅር፣ በዒባዳ ላይ ያየሁትን ታታሪነት ወደ ተግባር የመቀየር ምኞት.... ሁሉም የተቀሩኝን 3 ቀናት 3 አመታት የሆኑ ያህል አርዝመውብኛል። ለመመለስ ያለኝ ናፍቆት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል! ማስታወሻ ደብተርና እስክርቢቶ አውጥቼ የቀሩኝን ሰዎችና መስጂዶች ማስላት ጀመርኩ።
"15 ቤቶችንና 7 መሳጂዶችን አዳርሻለሁ። ስለዚህ 5 ቤቶችና 3 መስጂዶች..." ወረቀቱ ላይ እያሰፈርኩ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ። "የተሰጠኝ የረፍት ጊዜ ሊያልቅ 6 ቀናቶች ይቀሩታል.... እነዚህን በ2 ቀናት ብጨርስ ትኬት ቆርጬ ለመመለስ እችላለሁ።" ትናንት ያገናኘኋቸውን አድራሻዎች አየኋቸው.... ሁለቱ አንድ ሰፈር ናቸው፣ ሁለቱ ደግሞ የተለያዩ ሰፈሮች ላይ ናቸው፤ 5ኛው ደግሞ.... "ስለዚህ እደርሳለሁ!" በደስታ እስክርቢቶውን ማስታወሻው ላይ ወረወርኩት። ኢላሂ ባቀድኩት መሰረት ያሳካው።
*
በቀጣዩ ንጋት በጠዋት ወደ ቤተል አቀናን፤ በአንድ ሰፈር ላይ ካሉት 2 ቤቶች አንዱ ነበር። ወደ አድራሻው ስንደርስ ቤቱ ደጅ ላይ ሁለት በእድሜ የገፉ እናቶች ፀሃይ ላይ ተቀምጠዋል። ራቅ ብሎ 2 ሴቶች ልብስ እያጠቡ ያወራሉ፣ በሌላኛው ጥግ ሬድዮ ከያዙ አንድ አባት አጠገብ ሌላ ሴት እሳት ታቀጣጥላለች። ማንኛቸውን መጠየቅ እንዳለብኝ ግራ እየተጋባሁ እያለ አንድ ወጣት ከዛው ቤት ወቶ አልፎኝ ወደ ውጪ ሲያመራ ተመለከትኩት።
"አፍወን ወንድም.... የአቶ ሰዒድ ቤት ይሄ ነው?"
"አዎ ፈልገኸው ነው?"
"ካለ ብትጠራልኝ አዎ..."
"ሃናን!..... አባን ጥሪው ሰው ይፈልገዋል! አፍጥኚው!..." ጮክ ብሎ እየተጣራ። ሲያጥቡ ከነበሩት ሴቶች አንዷ እጇን አራግፋ ወደ ውስጥ ገባች፤ ሃናን እሷ ሳትሆን አትቀርም። "አብሽር ጠብቀው ይመጣል..." በቆምኩበት ትቶኝ ወደ ውጪ ወጣ። ትንሽ ቆይቶ ጋሼ መጡ፤ መንደሩ መኪናቸውን ለማስገባት ስካልተመቻቸው የሚያቆሙበት እስኪፈልጉ ነበር የቀደምኳቸው። ብዙም ሳይቆዩ ነጭ ኮፍያቸውን የደረቡ ጎልማሳ ሰው ከቤቱ ወተው ወደኛ አመሩ።
"እንዴ ጋሽ አብደላ.... አንተን ነው እንዴ ሰው ይፈልጎታል ምናምን የሚሉኝ? ሃሃሃ" ደስታቸው ከፊታቸው ላይ እየተንፀባረቀ ጋሼንና እኔን ዘየሩን። እንደሁሌው ጋሼ እስኪያስተዋውቁኝ ስለራሴ ምንም አላልኩም። ከሰላምታቸውና ከንግግራቸው የተረዳሁት ግን አንድ ነገር በጣም ደንቆኛል.... ይሄ ሁሉ ደጅ ላይ ያለው ሰው የሳቸው ቤተሰብ ነው! ኧረ እንደውም 5 ልጆቻቸው ት/ት ቤት ስለሆኑ እንጂ ቤተሰቡ ከዚም በላይ ትልቅ ነው.... አጂብ!
"እና ምን እግር ጣለህ? ወደዚ ሰፈር ቤት ቀየርክ እንዴ?" አቶ ሰዒድ ጋሼን ጠየቋቸው።
"ኧረ አይደለም ራቢያ ናት የላከችን የሱልጣን ልጅ ትንሿ አስታወስካት? እሱ ሙስዐብ ይባላል.... ባለቤቷ ነው።"
"ኧረ? ማሻአላህ..... አማቻችን ነዋ! እና እስካሁን አትናገርም በር ላይ እንደገተርነው.... ፋይዛ ሻይ አፊማ ቶሎ በይ!" ዞር ብለው መጣራት ጀመሩ። እቃዎችን እሳት ለምታቀጣጥለው ሴት ስታቀብል የነበረች ሌላ 4ኛ ሴት እየተቻኮለች ወደ ውስጥ ገባች.... ወይ ቤተሰብ።
"ኧረ.... ወላህ አያስፈልግም፤ ብዙ አንቆይም።"
"አይሆንማ! ራቢያ እኮ ልጄ ናት.... ሄጄ አባትሽ ከደጅ መለሰኝ ልትላት ነው... ሃሃሃ"
"ሃሃህ ኧረ ምንም አትልም ወላህ። አንድ መልዕክት ልካኝ ነው የመጣሁት።" ፖስታውን አውጥቼ ሰጠኋቸው። ገንዘቡን ካዩት በኋላ እንደሌሎቹ ከመደንገጥ ይልቅ ኮስተር ሲሉ አየኋቸው።
"ኧረ አይሆንም እረፊ በላት! እኔ እሷን ደግሼ መዳር ሲኖርብኝ ጨራሽ..." ፖስታውን ወደኔው መለሱት።
"አይ እንደሱ ብላ አይደለም..." ላስረዳቸው ብሞክርም ተቃወሙኝ። ቅርርባቸውን ባላውቅም ለመጀመሪያ ጊዜ አባቷ ፊት የቆምኩ ያህል እኔም ልጫናቸው ከበደኝ።
"ሰዒዴ.... ሱልጣን ቢኖር አትልክለትም ነበር? እሱም እምቢ አይላትም አይደል? አታስቀይማታ...." ጋሼ ጣልቃ ገብተው አሳረፉኝ።
"ሳህ.... ውስጡ ያስቀመጠችልህን የፅሁፍ መልዕክትም ጭምር እንዲደርስህ ስለፈለገች ነው አጎቴ" መልሼ ፖስታውን ዘረጋሁላቸው። በአንደበታቸው መስማማታቸውን ባይገልፁም ቀዩን ካርድ አውጥተው ማንበብ ጀመሩ። አይኖቻቸው ከመስመሩ ጋር አብረው ሲንቀሳቀሱ በመኮሳተር የተሸበሸበው ግምባራቸውም አብሮ ፈታ ሲል ይታይ ነበር።
"ህህም.... እሺ ይሁን፤ ደስ ይበላት ኸይር። ምን አስቀይመሽኝ በላት.... ደግሞ መች ከዱዐዬ ረስቻት ያመውቀውን። አብሽሩ አላህ ሰፊውን ሪዝቅ ይክፈትላቹ..." እየመረቁን ወረቀቷን ወደ ፖስታው መለሷት። አሚን ከማለቴ ጋር የዛሬውን ወረቀት ማንበብ እንደማልችል በማወቄ እንደጎደለብኝ ተሰማኝ።
"ሰዒዴ.... ካርዱን ባነበው ቅር ይልሃል?" ጋሼ ነበሩ። ያልጠበቅኩት እድል ነበር።
"ሃሃህ.... መቼስ ከኔ ለይታ ምን አለችው የሚለው አሳስቦህ ነው አይደል?..." ወረቀቱን አውጥተው ሰጡት። ጋሼ ጥቂት ካነበቡት በኋላ ለኔ አቀብለውኝ ከአቶ ሰዒድ ጋር ማውራታቸውን ቀጠሉ። አቶ ሰዒድ አይተው ስላልተቃወሙ እንደተፈቀደልኝ ቆጥሬው ማንበብ ቀጠልኩ...
.
<<አሰላሙ ዐለይክ አጎቴ ሰዒድ... ራቢያ ነኝ። ሁኔታዎች እስኪስተካከሉልኝ ነው የጠፋሁት እንጂ ውለታቢስ ሆኜ አይደለም፤ ሁላችንም ደህና ነን። ከአባ ለቅሶ በኋላ ያሳዩንን ድጋፍ መቼም አልመልሰውም። አባዬ ለምን አንተንና ጋሼን በጣም ይተማመንባቹ እንደነበር አሳይታቹኛል። ያን ሁሉ ቤተሰብ ተሸክመህም ለመጣው ለሄደው ሁሉ ቤትህ ክፈት ነው.... እናንተ ጋር ያየሁትን የእንግዳ ተቀባይነት ማንም ጋር አላየሁም። በመጪው የራህማ ወር ሙሳፊሮችን ማብላቱን፤ የመጣ የሄደውን መሸኘቱን በጉጉት እንደምትጠብቁት አውቃለሁ። <ፆመኛ ሰው ከርሱ ዘንድ ሌሎች ሰዎች በሚመገቡ ጊዜ ምግባቸውን እስኪያጠናቅቁ (ወይም እስኪጠግቡ) ድረስ መላኢኮች ከአላህ ምህረት ለዚያ ሰው ይለምኑለታል> የሚለውን የነቢናን ንግግር ሳስታውስ ቀድሜ የማስበው እናንተን ነው። አንቺም ልጄ ነሽ ትል አልነበር አጎቴ? ስለዚ ይሄን ወጪ እንድጋራህ ፍቀድልኝ። ለዛ ሁሉ ቤተሰብ ለመትረፍ ከፍ ዝቅ ከማለት አረፍ ብለህ ዒባዳ ላይ የምትበረታበት ይሁን። ነቢዩ {ሰ.ዐ.ወ} ሰዕድ ኢብኑ ዐብደላህ (ረ.ዐ) ዘንድ በተመገቡ ጊዜ <ፆመኞች እናንተ ዘንድ አፈጠሩ። ምግባችሁን በጎ ሰዎች ተመገቡት። መላኢኮች ምህረትን ለመኑላችሁ።> ብለው ያደረጉላቸው ዱዐ ለናንተም የሚደርስበት ይሁን። አሳዝኜህ የማውቅ ከሆነ አፉው በለኝ አጎቴ.... እኔና ሙስዐብን በዱዐህ አትርሳን። ሁላቹም ናፍቃቹኛል፤ በቅርቡ በአካል እስክዘይራቹ የራህማኑ ሰላምና እዝነት በናንተ ላይ ይሁን።>>
.
....አንብቤ ስጨርስ አጎቴ ራቢ ዘንድ ያላቸው ቦታ ይበልጥ ገዘፈብኝ። ካርዱን መለስኩላቸው፤ በጨዋታ መሃል ሆነው ተቀብለውኝ ወደ ፖስታው ከተቱት። ትንሽ ካወሩ በኋላ ለመሄድ ፍቃዳቸውን ጠየቅን፤ ሻዩ ስለደረሰ አትሄዱም ብለው ተቃወሙን። ልናስቀይማቸው ስላልፈለግን ተስተናግደን ለመሄድ ተስማምተን ወደ ውስጥ ገባን።
.
.
ይቀጥላል...

@wub_Tarikoch
@wub_Tarikoch
517 views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 09:03:17 ፈዳኢል...
(በTeam Huda)
(ክፍል ሀያ ሶስት)
.
.
ተመልሰን ወደ ሳባ መስጂድ ስንደርስ የዐስር ጀመዐ ሰላት ተሰግዶ አብቅቶ ነበር። ከጋሼና ከሌሎች ጥቂት ሰዎች ጋር በጀመዐ ሰገድን። ለዛሬ የያዝኳቸውን ፖስታዎችም፤ የያዝኩትን የገንዘብ መጠንም ጭምር ጨርሻለሁ.... ስለዚህ መግሪብ እስኪደርስ እዛው ተቀምጠን ቁርዐን ለመቅራት ወሰንን።
*
መግሪብ በጀመዐ ተሰግዶ ካበቃ በኋላ አስተባባሪዎቹ ቀን እንድንታደመው የጋበዙን ዳዕዋ ጀመረ.... ቀናት ስለቀሩት የራህማ ወር የተሰናዳ ማንቂያ ነበር። ሸይኹ በራቢ መልዕክቶች ላይ ያነበብኳቸውን ሃዲሶች እያፈራረቁ ስለ ረመዳን ታላቅነት ሲያብራሩልን ቆዩ... በልቤ ውስጥ ከእያንዳንዱ ሃዲስ ጋር በተግባራቸው የቀረፅኳቸውን ግለሰቦች እየከለስኩ ነበር። ሸይኹ ቀጥለውም ረመዳን ላይ ሊኖረን ስለሚገባው አመጋገብ መተንተን ጀመሩ... ሃሳቤን ወደሳቸው ብቻ ሰብስቤ መከታተሌን ቀጠልኩ።
.
"....ስለዚህ ሱፍራ ስለሞላ ብቻ እኛም ለዒባዳ መነሳት እስኪያቅተን መመገብ የለብንም። ልክ ይኑረው.... ራህማኑን የምናመሰግንበት ፋታ ይኑረን። አንዳንዶቻችን ለመመገብ ከመጣደፋችን የተነሳ 'ዘሃበ ዘመዑ ወብተልለቲል ዑሩቁ፣ ወሠበተል አጅሩ ኢንሻአላህ' (ጥማችን ተቆርጧል። የደም ስሮቻችን ረጥበዋል። የአላህ ፈቃድ ከሆነ ምንዳም ተረጋግጦልናል።) የሚለውን ዱዐዕ እንኳን አናስታውሰውም። ከፊሎቻችን በፊጥራ ሰዐት ለሚጀምረው የረመዳን ዝግጅት ልባችን ተሰቅሎ ነው የምናፈጥረው። ከፊሎቻችን ደግሞ ሆዳችን ሞልቶ መነሳት እስኪያቅተን የመግሪብ ሰላት ትዝ አይለንም። ይሄ ልክ አይደለም አህባብ.... አጿጿማችንን አሳምረን መቋጫውን አናበላሸው። ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ)... 'በጤንነትህ ወቅት ለበሽታህ ጊዜ የሚሆን፥ በሕይወት እያለህ ደግሞ ለሞትህ የሚየገለግልህን መሰናዶ አድርግ።' ይሉ ነበር። ዛሬ ላይ ሞልቶ የምናየው ሱፍራ አያታለን.... ረመዳን ላይ ዋና አላማችን ለአኼራ የሚሆነንን ስንቅ መሰብሰብ ነው። ሲመቸን ሲመቸን አይደለም ዒባዳችን፤ አጿጿማችን፤ አፈጣጠራችን ማማር ያለበት.... ከመጀመሪያውም እንዲያምር መመቻቸት ነው ያለብን። ከቻልን ለመግሪብ አዛን 10 ደቂቃ ሲቀረው ዝግጅታችንን እንጨርስ.... አዛን ስትሰሙ ለማፍጠር ተጣደፉ እንጂ ለማቅረብ ተቸገሩ አልተባልንም አይደል? አዛን ስንሰማ አንዳችን አንዳችንን ቴምር የሚያስዪዝበት.... ከቻልን ተጎራርሰን በመሃባ አጅራችንን እያበዛን የምናፈጥርበት እናድርገው። 'አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ቢራህመቲከ አልለቲ ወሲዐት ኩልለ ሸይኢን አንተግፊረሊ' (አላህ ሆይ! ምህረትን ትለግሰኝ ዘንድ ሁሉንም ነገር ባዳረሰችው እዝነትህ እማፀንሃለሁ) እንበለው። የሱናውን 3፤ 5 ወይ 7 ፍሬ ቴምሮችን ከቀመስን፤ ውሃችንን ከጠጣን ተነስተን መግሪብን ለመስገድ በቂ ነው። መስጂድ ከሆንን በሰፊ ጀመዐ.... ሰፈራችን መስጂድ ከሌለም ቤታችን ባለ ጀመዐ የተዋበ ሰላትን እንስገድ። ከዛ ተመልሰን ለመብላቱ እንደርሳለን ኢንሻአላህ..." ረጋ ባለው አነጋገራቸው የሚስሉልንን የፊጥራ ድባብ በምናባችን እየቀረፅን ተመስጠን መከታተላችንን ቀጥለናል።
.
"ኸይር ከፊጥራ ውጪ ደግሞ ሱሁርን እንደ ቀላል አይተነው የምንዘናጋበት ብዙዎች ነን። የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ} <ሱሁርን ተመገቡ። ሱሁርን መመገብ በረከት አለውና> ብለውናል። በተቻለን አቅም አላርም ሞልተን ለሱሁር እንነሳ። ቤተሰቦቻችን ይሄን በረካ እንዲያገኙ እነሱንም እንቀስቅሳቸው። በጊዜ በልቶ ከመተኛቱ ይልቅ፥ ሳይታወቀን ፈጅር እንዳይደርስ እስካልፈራን ድረስ፥ ዘግይተን ሱሁር መመገባችን ይወደዳል። ዘይድ ኢብኑ ሳቢት {ረ.ዐ} ባስተላለፉት ሀዲስ። <ከአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ} ጋር ሱሁር ተመገብን። ከዚያም ወደ ሰላት ሄድን።> አሉ። <በመሃከላቸው ምን ያህል ጊዜ ቆያችሁ?> ተብለው ተጠይቀውም። <ሃምሳ አንቀፆችን (ለማንበብ የሚያስችል) ያህል ጊዜ> በማለት ዘይድ መልሰዋል። 50 አንቀፅ ትንሽ ነው አይደል? ለፈጅር ሰላት ያን ያህል ክፍተት ብቻ እስኪቀር አዘግይተው ሱሁር ይመገቡ ነበር። በዛውም ግን የሚጠቀሙትን የጊዜ አገላለፅ ማራኪነት ልብ አላቹ? እኛ በዚ ጊዜ ሰዐታችንን ያላየን ሆነን ስለ ጊዜ ብንጠየቅ ምንድነው ቀድሞ ትዝ የሚለን?.... 'የእከሌ ፊልም ማስታወቂያ እስኪሆን...' አይደል?" ሸይኹ ከሰጡት ምሳሌ ጋር ሁላችንም ሳቅን።
.
"ሃሃህ.... አላህ ይመልሰን። አላህ የቀደምቶቹን መንገድ የምንከተል ያድርገን። እና ምን ለማለት ነው ማዘግየቱ ይወደዳል። ከዛ ውጪ ለሱብሂ ሁለት ጥሪ የሚያደርጉ ሰዎች ቢኖሩና አንደኛው በሚያደርገው ጥሪ ሙስሊሙ ለሰላት እንዲዘጋጅ.... ሱሁሩን ተመግቦ ያልጨረሰም እንዲያጠናቅቅ መደረጉ የተወደደ መሆኑንም በነቢና ጊዜ ከነበረው ሁኔታ እንማራለን። የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ} ሁለት አዛን አድራጊዎች ነበሯቸው። ቢላል እና ኢብኑ ኡሙ መክቱም ይባላሉ። የአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ}፦ <ቢላል አዛን የሚያደርገው በሌሊት በመሆኑ ኢብኑ ኡሙ መክቱም አዛን እስኪያሰማ ድረስ ብሉ፤ ጠጡ።> ይሉ ነበር። ኢብኑ ዑመር እንዳሉት፦ <በሁለቱ ሰዎች አዛን መካከል የነበረው የጊዜ ልዩነት አንደኛው ወርዶ ሌላኛው እስኪወጣ ድረስ ያለው የጊዜ መጠን ነው።>.... ስለዚህ ሁለት አዛን አድራጊዎች ካሉ የመጀመሪያውን ስትሰሙ ተዘጋጁ፤ ሁለተኛውን ስትሰሙ ሙሉ በሙሉ መመገብ አይቻልም... ታቆማላችሁ ማለት ነው። ኢንሻአላህ በመጪው ረመዳን 6 ሰዐት አካባቢ በሱሁርና በራት መካከል ያለ ነገር ተመግበን፤ እንቅልፍ ጥሎን ፈጅር በተኛንበት የሚያልፈን መሆን የለበትም። ሱሁርን ወደነው የምንነሳበት፤ ተመግበን ወደ ሰላት የምናመራበት.... ነቃ ብለን ፆመን የምንውልበት እናድርገው። ሱሁር መነሳት ሸክም ሊሆንብን አይገባም... <በእኛና በመፅሃፉ ሰዎች ፆሞች መካከል ያለው ልዩነት እኛ ሱሁር መመገባችን ነው።> አይደል እንዴ ሸፊዑና {ሰ.ዐ.ወ} ያሉን? የኛ ዲን የሚለይበት ነው.... ፆማችን እንዳይከብደን የተሰጠን ኒዕማ ነው፤ በረካ ያለበት ነው! ስለዚህ ከቤተሰቦቻችን ጋር ነቃ ብለን እንመገብ። ተስማማን ኢንሻአላህ?" ሁላችንም በጋራ በሚተራመስ ድምፅ መስማማታችንን በ 'ኢንሻአላህ' ገለፅን።
"ባረከላሁ ፊኩም። መጀመሪያ ላይ ያነሳናቸው የረመዳን ልቅናዎች፤ የፊጥራ አደብም ጭምር እንዳይረሱ። ኸይር የተቀረውን ደግሞ ነገ ከደርስ በኋላ ጊዜ ካለን ይቀጥላል ኢንሻአላህ። ለዛሬ ይብቃን.... ወሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።" ተሰናብተውን ንግግራቸውን አጠቃለሉ። ለመጀመሪያ ጊዜ ከራቢ ጋር ለሚኖረኝ የረመዳን ቆይታ ይበልጥ እንድጓጓ አደረጉኝ.... ኢንሻአላህ እሳቸው በገለፁት መልኩ የተዋበ ላደርገው እጥራለሁ። ትንሽ ከቆየን በኋላ ወደ ሆቴል ለመመለስ ከጋሼ ጋር ከመስጂዱ ወጣን።
.
.
ይቀጥላል...

@wub_Tarikoch
418 views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 09:02:40 ፈዳኢል... (በTeam Huda) (ክፍል ሀያ አንድ) . . ከባንክ ቤት መልስ ወ/ሮ ሁስኒያን ወደ መስሪያቤቷ የሚያደርሳትን ታክሲ ካስያዝናት በኋላ ወደ ቀጣዩ አድራሻ መንገዳችንን ቀጥለናል... "ጋሼ.... የባለፈው ጡሩ ሲና መስጂድ ስንሰግድ የተደረገውን ዳዕዋ ልብ ብለዋል?.... ያሉብንን ጥሩ ያልሆኑ ልማዶች በመልካም ስለመቀየር.... የፊታችን የበረካ ወርም የተሻለ እድል ስለመሆኑ..." እንዲያሳዩ…
490 views06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ