2022-10-13 16:58:59
ከጥቂት ዓመታት በፊት በሱዳን የሚኖሩ የአግልግሎት አጋሮቻችን እርዳታን ጠየቁን።በምሥራቅ ሱዳን የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር አጠገብ የምትገኝ አሮማ የምትባል ከተማ በጋሽ ወንዝ ሙላት ምክንያት በጎርፍ ተጠለቅልቃ ነበር።ጎርፉም 7000 ያህል ቤቶችን አውድሞ ነበር።አጋሮቻችንም ገንዘብ አሰባስበን ብንረዳቸው ለአሮማ ሕዝቦች እንደሚያደርሱላቸውና ይህም መልካም ሥራቸው ለወንጌል በርን እንደሚከፍተላቸው ነገሩን።እኛም ይህንን ዜና በገንዘብ ለሚደግፉን አሜሪካውያን አጋሮቻችን አካፈልናቸው።ሁለት ወጣት እጮኛሞች ከተጠየቀው ገንዘብ አብዛኛውን ሰጡንና ለአሮማ ሕዝቦች በችግራቸው ልንደርስላቸው ቻልን።ከጥቂት ጊዜ በኋላ የእነዚህን ለጋስ ጥንዶች ታሪክ ሰማሁና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር መረዳት ቻልኩ።
እነዚህ ሰርገኞች በሱዳን ስለደረሰው የጎርፍ አደጋ የሰጠነውን መግለጫ ሲሰሙ ሊሞሸሩበት ያቀዱትን ድል ያለ ድግስ ቅልብጭ ባለችው ለወጡት።በሆቴል ቤት የመጋባት አሳባቸውንም ቀይረው በአንድ ግለሰብ ጓሮ ቤት አደረጉት።ብሎም ታዳሚ እንግዶቻቸው ለሰርጉ የሚሆነውን ምግብ በየቤታቸው አዘጋጅተው ይዘው እንዲመጡ አደረጉ።ለትልቅ ሰርግ ያሰቡትን ገንዘብ ወደ ሱዳን እንድንልከው ሰጡን።በዚህም ለብዙ የጎርፍ አደጋ ተጠቂዎች በረከት ሆኑ።
እግዚአብሔርን መውደዳችን ሙሉ የሚሆነው እንደዚህ ባልንጀራችንን ስንወድ ነው።...
ማርቆስ ዘመደብርሃን(ዶ/ር) ፤ልኡካን፤ገጽ 26-27
ከመጽሐፍት ማዕድ
66 views13:58