Get Mystery Box with random crypto!

World Peacefully

የቴሌግራም ቻናል አርማ worldpeacefully — World Peacefully W
የቴሌግራም ቻናል አርማ worldpeacefully — World Peacefully
የሰርጥ አድራሻ: @worldpeacefully
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 769
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም ኢስላማዊ ወንድማማችነት በአንድነት እስከ ጀነት።
Peace of Islamic brotherhood together to heaven

━━━━━━━━━━🇪🇹 ━━━━━━━━━━
Selam Islamic Channel
ሰላም ኢስላማዊ ቻናል
https://m.facebook.com/WorldPeacefully
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-10 20:33:17 ቢራን ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ብለህ ብትጽፍበት ማስከሩን እንደማይተወው ሁሉ የወለድም ባንኮችም ስም ኢኽላስ, አሚን, ሲዲቅ, ኑር ብለው በኢስላም ስም ቢሰይሙትም ወለድነቱን አይቀይረውም::
134 views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 17:15:11 ተንኮል ተመልሶ ራስን ይጠልፋል። ለነገ መልካም ሰው ለመሆን በማሰብ ዛሬህን በግፍ አታበላሽ።
ዩሱፍን عليه الصلاة والسلام የስጋ ወንድሞቹ ተጋግዘው ከጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ በመወርወር ዝናውን ሊያከስሙት፣ ተወዳጅነቱን ሊያሳጡት ሞከሩ። በዚህ ድርጊታቸውም አባታችን ዘንድ የበለጠ ተወዳጅነትን እናተርፋለን ብለው አቀዱ። ምንም እንኳ ዩሱፍ ከየእቁብ عليهما الصلاة والسلام እይታ ቢሰወርም ከአእምሮው ግን የበለጠ እየገዘፈ መጣ፣ ደጋግሞ የሚያወሳው ዩሱፍን ሆነ። አብዝቶ የሚያስበውም ስለዩሱፍ መገኛ ጊዜ ሆነ። አባታችን ዘንድ የበለጠ እንወደዳለን ብለው ግን ይባስ ተጠሉ። ከብዙ አመታት በኋላ ዩሱፍም ከጉድጓዱ ወጥቶ እነሱ ደግሞ የዩሱፍን እጅ ከጃዮች ሆነው https://t.me/WorldPeacefully
295 views14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 15:10:57 ዑመር ገነቴ ከዑመር ይማም በምንድነው የሚለየው?
~~~
1- ሁለቱም አሕባሾች ናቸው።

አሕባ - ሽ እዚህ እንዲደርስ ያመቻቸው ከዑመር ይማም ይልቅ ዑመር ገነቴ ነው። አሕባ/ሽ ገና በሁለት እግሩ ሳይቆም በ90ዎቹ ከሊባኖስ በመጡ አሕባ/ሾች የማጥመቅ ስልጠና ሲሰጥ መርቆ የከፈተው ዑመር ገነቴ ነው። አሕ/ባሽ እግሩን በተከለበት ከ1992 እስከ 2000 ድረስ የዑለማእ ምክር ቤት ሊቀመንበር ነበር። ከሚያዚያ 2001 ጀምሮ እስከ 2005 ድረስ ከፌደራል መጅሊስ አመራሮች ውስጥ ነበር። ይሄ ዘመን የአሕባሽ ፈተና የጠነከረበት ጊዜ ነው። ሐምሌ 9 እና 10/2004 ራስ ሆቴል ውስጥ በተካሄደ የአሕ/ባሽ ኮንፈረንስ ከ100 የሚበልጡ ሱፍዮች ከመላው ሃገሪቱ ተሰብስበው "ወሃ-ቢዮች" የሚሏቸውን ሙስሊሞች ሁሉ ከኢስላም በማስወጣት የክህደት ብይን ሰጥተው መግለጫ አውጥተዋል። ከ 2005 ጀምሮ ደግሞ እስከ 2010 ድረስ የፌደራል መጅሊስ የጠቅላላ ጉባኤው አባል፣ የመስጂድና አውቃፍ ዘርፍ ሀላፊ እንዲሁም የዑለማ ምክር ቤት አባል ሆኖ ሰርቷል። በዚህም ዘመን በአሕ-ባሾች ምን እንደ ደረሰ የምናውቀው ነው።

2- ሁለቱም ሙስሊሞችን ያ - ከ * ፍ - ራ - ሉ።

አዎ ሁለቱም አላህ ከዐርሹ በላይ ነው የሚሉ ሙስሊሞችን በሀሰት "ሙጀሲማ" የሚል ቅፅል ለጥፈው በከሃዲነት የሚፈርጁ ናቸው። የዑመር ይማም አያከራክርም። "ወሃ-ቢዮች ያረዱት አይበላም፣ ኒካሕ የላቸውም" እያለ ባደባባይ የሚናገር ነው። "ዶክተር" አቡበክር የሚባለውም አሕ-ባሽ በቅርቡ ሆሳእና ላይ ተመሳሳይ ነገር ተናግሯል። እነዚህ ሰዎች የ"ሙፍቲው" ጀማዐ እንደሆኑ የሚታወቅ ነው። ዑመር ገነቴ እራሱ "አላህ ከ0ርሽ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን ከኢስላም የሚያስወጣ ፅንፈኛ እንደሆነ የድምፅ ማስረጃ አለ።

3- ሁለቱም ሙስሊሞችን በጠላት ለማስመታት የሚጥሩ ጠላቶች ናቸው።

ዑመር ገነቴ አይደለም እንዴ ክርስቲያኖችን ጭምር ለአመፅ የጠራው? ወደ ደም መፋሰስ የቀሰቀሰው? መስጂድ እያቃጠለ፣ ሙስሊሞችን እየገደለ ያለው ቡድን የሱ ጀማዐ አይደለምን? እስኪ መቼ ነው የሙስሊሞች መሪ፣ የዑለማእ ቁንጮ ነኝ የሚለው ይሄ ሰውዬ በተከታዮቹ የተፈፀመውን ይህንን ፀያፍ ድርጊት የኮነነው? እንዲያውም ቅስቀሳ ሲያደርግ ነው የምናውቀው። እንዲያውም ሙስሊሞችን በጠላት ለማስመታት በግላጭ ሲሰራ የኖረ ሰው ነው። እስኪ ይህንን ጥቅምት 30/2012 በሸገር ሬዲዮ ከቀረበው የዑመር ገነቴ ቃለ ምልልስ የተወሰደ ንግግር መላልሳችሁ አስተውሉ!! ይሄው:–

"ለባለስልጣኖቹም፣ ለእነ አባይ ፀሃዬ – የዚያን ግዜ የደህንነት ኃላፊ ነበሩ –
‘ተው እባካችሁ! ይኼ ችግር (#ሰለፍያን ማለቱ ነው) መንግስት ላይ ይወጣል። እኛ ላይ ብቻ ሳይሆን እናንተም ላይ ይደርሳል’ እላቸው ነበር።
በኋላ እንግዲህ በእነመለስ ግዜ እነርሱ ላይ ሲደርስ መጥፋት አለበት ብሎ ያ ሁሉ ችግር ተፈጠረ። መጀመሪያውኑ ከውጥኑ ማጥፋት ይቻል ነበር።"

ተመልከቱ! መንግስት ሳያስብ በፊት አሕባሽ ያልሆኑ ሙስሊሞችን እንዲያጠፋላቸው ሲወተውት ነበር ማለት ነው። እነዚህ አቅሙ ቢኖራቸው እንደ ዮሐንስ ሙስሊሞችን አጋድመው ያርዱ።

ቀጠለ:—

"መንግስት የዚያን ግዜ በጎናችን አልቆመም። መፈለግ አይፈልገውም። ሙስሊሙ ላይ ብቻ ይቀር መስሎታል እንጂ ወደ መንግስት ያልፋል አልመሰለውም። አሁን ሀገሩ በሙሉ ተዳርሷል። ለማጥፋት አልተቻለም። ወደአንድነት መጥተን ሰላም ቢሆን ይሻላል ሀገሩ ብለን ነው። ወደን አይደለም በአንድነት የምንታየው። ማጥፋት ካልተቻለ አብሮ በሚሆንበት ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል በሚል ነው።"

ምንኛ ልብ የሚያደማ ንግግር ነው?!

4- ዑመር ገነቴ ከዑመር ይማም በላይ የተውሒድ ደዕዋን ሲዋጋ የኖረ ነው። እራሱ እንዲህ ሲል ይመስክራል:-
«ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ–ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ትላላችሁ! ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ እና ዐብዱ-ር-ረሕማን ናቸው ወሃቢያን የመሰረቱት፡፡ ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ እንጂ ዑመር አይደለም ወሃቢያን የመሰረተው፡፡
እኔ ብቻዬን ስታገል ነው የኖርኩት፡፡.....
ዐቂዳ ትላላችሁ ...ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ነው ወሃብያን የመሰረተው። ዐብዱ-ር-ረህማን ነው ወሃብያን የመሰረተው፡፡ ... ወደኛ የመጣችሁ እደሆነ የዘከዘኩት እንደሆነ ሌላ ታመጣላችሁ!……
ወሃብያን የመሰረተው ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ እና ዐብዱ-ር-ረህማን ናቸው፡፡ ስንታገል ነው የኖርነው .... ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ናቸው እንዴ ወሃብያን የታገሉት? ማን መሰረተው?"
ዑመር ገነቴ በ 90 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ባህርዳር ላይ በፖሊስ በታጀበ ስብሰባ ታዳሚዎችን ሲያስጨንቅ ነበር።

አንገቱን የደፋበትን ፎቶ እየለጠፋችሁ አጉል አንጀት ለመብላት አትሞክሩ። ሓሪሥ አልሙሓሲቢ ከዑመር ገነቴ በዒልምም፣ በአደብም፣ በአቋምም የተሻለ ነበር። ኧረ ጭራሽ የሚነፃፀሩም አይደሉም። ነገር ግን በያዘው የቢድዐ አቋም የተነሳ ዙህዱም፣ አደቡም፣ ... በነ ኢማሙ አሕመድ ከመወገዝ አላዳነውም። "እርጋታውና ልስላሴው አይሸውድህ። እራሱን በመድፋቱ እንዳትሸወድ" ነበር ያሉት። ይሄኛው ምኑ ነው የሚሸውደን? እብሪትና በባዶ መኮፈስ እንጂ ምን አደብ አለውና! ለማይታዘነው እያዘናችሁ ተሸውዳችሁ ሌሎችን አትሸውዱ። ለእዝነትም ቦታ አለው። ያለ ቦታው እያዋላችሁ አታሪክሱት። ለማይገባው እያለቀሳችሁ ቅጥ አታሳጡት። በጥቅም ተጋሪዎቹ ወይም በመዝሀብ ዘመዶቹ ሙሾ አትሸወዱ። ሁለቱም ዑመሮች በዐቂዳም ሆነ ለሙስሊሞች ባላቸው አደጋ ልዩነት የላቸውም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
273 views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 23:05:19
279 views20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 10:22:43
ለመላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች በሙሉ
እንኳን ለ1443ኛው የኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
281 views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 12:10:57 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ ወበረካትሁ ውድ የኢስላም ልጆችና የሰላም ተከታታዮች በመሉ የአላህ ሰላም በነብዩ መሀመድና የእርሱን ቅን መንገድ ለሚከተሉ ባልደረቦቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ይሁን እያልን ሰላም የሁሉም የሙስሊሙን አመለካከት በአንድ አላህ በሆነው ቃል ቁርዕንና ለሰው ልጆች ሁሉ የጀነት ጎዳና የሆነውን ኢስላማዊ ወንድማማችነት በአንድነት እስከጀነት በሚል መሪ ሀሳብ ተመርኩዞ ተከታታይ ኢስላማዊ ፅሑፎችን ያቀርባል።
ውድ እናቶቻችን አባቶቻችን እንድሁም ወንድሞቻችን እህቶቻችን በሙሉ በሰላምና በአንድነት በልዩነቶቻች ምክንያት ሳንከፋፈል ኢስላማዊ በሆነ መንገድ አብረን የምንጓዝበት ወንድማማችነት ኢስላማዊ ሀቅንና ቅን ሀሳቦችን በማሰብ ለአንድነትና ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት አንድነታችንን እናጠናክር በማለት በአላህ ስም እንጠይቃለን።
ሰላም የቴሌግራም ቻናልና የፌስቡክ ፔጅን በመቀላቀል ለሌሎችም ሼር ላይክ ኮሜንት በመስጠት ወዳጅ ዘመድ ጓደኞች በማስተላለፍ እድቀላቀሉ በማድረግ የበኩላችንን በማድረግ እንተባበር
http://t.me/WorldPeacefully
334 views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 12:08:06
236 views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 14:07:56 የዙልሒጃ ወር መግቢያ ጨረቃ ታይታለች!
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ሐምሌ 2 ዕለተ ቅዳሜ እንደሚከበር ተገለፀ!!
የዙልሒጃ ወር ዛሬ ሐሙስ አንድ ብሎ ይጀምራል
አቡ ዳውድ ኡስማን
በሳዑዲ አረቢያ አዲስ የዙልሂጃ ወር መግቢያ ጨረቃ
በመታየቷ የዙልሂጃ ወር ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 23/2014 / June 30/2022 አንድ ብሎ
እንደሚጀመር ታውቋል::
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልም ቅዳሜ ሐምሌ 2-2014/ July 09/2022 እለተ ቅዳሜ
እንደሚውል ታውቋል፡፡
ከዛሬ ሐሙስ ሰኔ 23 ጀምሮ ያሉትን 10 ቀናት በኢባዳ ልናሳልፋቸው ይገባል፡፡
የዙልሂጃን ዘጠኙንም ቀናት ለመፆም ፍላጎት ያለው ከዛ ሐሙስ June 30 /2022 ጀምሮ
መፆም ይችላል፡፡
ታላቅ ምንዳ የሚያስገኘውን የዙልሒጃ 9 (የአረፋን ቀንን) ለመፆም የሚፈልግም ሐምሌ
1እለት ጁምዓ መፆም ይችላል::
ከሐሙስ ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ አስር ቀናቶች በኢባዳ እናሳልፋቸው!
አላህ ይርዳን!
https://t.me/WorldPeacefully
292 views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 15:58:57 ካስገረሙኝ ንግግሮች
=================

* كلام اعجبني ........



عندما تولد لا تعلم
من الذي أخرجك من بطن أمك
ስትወለድ ከእናትህ ሆድ ያወጣህን ፈፅሞ አታውቅም።

وعندما تموت لا تعلم
من الذي أدخلك إلى قبرك
ስትሞት ማን ወደ ቀብርህ እንዳስገባህ ፈፅሞ አታውቅም።

* عجبا لك ياابن آدم*
* የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ።*

عندما ولدت تغسل وتنظف
ስትወለድ ትታጠባለህ፣ ትፀዳለህ።

وعندما تموت تغسل وتنظف
ስትሞት ትታጠባለህ፣ ትፀዳለህ።
* عجبا لك ياابن آدم*
* የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ።*

عندما تولد لاتعلم من فرح واستبشر بك
ስትወለድ ማን በልደትህ እንደተደሰተ አታውቅም።

وعندما تموت لاتعلم من بكى عليك وحزن
ስትሞት ማን እንዳዘነና እንዳለቀሰ አታውቅም።

* عجبا لك ياابن آدم*
* የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ*

في بطن أمك كنت في مكان ضيق ومظلم
በእናትህ ሆድ ውስጥ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ነበርክ።

وعندما تموت تكون في مكان ضيق ومظلم
ስትሞት ጊዜ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ትሆናለህ።

* عجبا لك ياابن آدم*
* የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ*

عندما ولدت تغطى بالقماش ليستروك
ስትወለድ በጨርቅ ትጠቀለላህ ሊሸፍኑህ!

وعندما تموت تكفن بالقماش ليستروك
ስትሞት በከፈን ይጠቀልሉሃል ሊሸፍኑህ!

عجبا لك ياابن آدم
የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ

عندما ولدت وكبرت يسألك الناس
عن شهادتك وخبراتك
በተወለድክና በአደግክ ጊዜ ሰዎች ምስክር ወረቀት ስለሙያህ ይጠይቁሃል።

وعندما تموت تسألك الملائكة عن عملك الصالح
በሞትክም ጊዜ መልዐኮች ስለመልካም ስራህ ይጠይቁሃል።

* فماذا أعددت لآخرتك ؟*
* ለመጨረሻው ሃገርህ ምን አዘጋጀህ?*

جرب تقولها من قلب :
آشهد آن لآ آله آلآ آلله
واشهد آن محمد رسول آلله
ከልብህ ይህችን (ቃል) ለመናገር ሞክር! ከአላህ ሌላ በፍፁም የሚመለክ አምላክ እንደሌለ መስክር። እንዲሁም ሙሃመድ የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መስክር።

مستحيل تقرآها بدون ما ترسلها
ይህችን መልእክት ፍፁም ሳታነባት እንዳትልካት!

& & &
‏ بسم الله الرحمن الرحیم
*{ قل هو الله أحد * الله الصمد * لم يلد ولم يولد * ولم يكن له كفواً أحد }*

*ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ*
*{ በል! እርሱ አላህ አንድ ነው። አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። አልወለደም፤ አልተወለደምም። ለእርሱ አንድም ብጤ የለውም።}*

إرسل وتخيل في هالساعه
መልዕክቱን ላክ! ሰአትህን አስተውል

كم شخص يقرأ ثلث القرآن بسببك لاتحرم نفسك مٍن الاجر
በአንተ ሰበብ የቁርኣን አንድ ሶስተኛን ይቀራሉ (ያነባሉ)


(منقول)
@WorldPeacefully
750 viewsedited  12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 21:14:11 እውቀትን አሰራጭ


➲ዳኢ ሆነህ ሰዎችን መጥራት ባትችል፦ የዱአቶችን ዳእዋ ለሌሎች አድርስ።

➲ኡለማ ሆነህ ሌሎችን መጥቀም ባይሆንልህ፦ የኡለማዎችን ጠቃሚ ምክር ለሌሎች አሰራጭ።

➲ሙፍቲ ሆነህ ፈትዋ መስጠት ቢያቅትህ፦ የሙፍቲዎችን ፈትዋ ላልሰሙት አስተላልፍ።

በዚህ ፊትና በበዛበት፣ ሰዎች የሚይዙትና የሚጨብጡት ባጡበትና የጥመት ሰዎች በተበራከቱበት በዚህ ከባድ ዘመን፦ የሱና ኡለማዎች፣ መሻይኾችና ዱአቶች ዳእዋ፣ ምክር፣ ፈትዋና ፅሁፍ በቻልከው መጠን ማሰራጨትህ እንደ ቀላል አትመልከተው። ይህ ኢኽላስ ከታከለበት ትልቅ ስራ መሆኑን ተገንዝብ።

ይህ ማድረግህ ተውሂድና ሱና እየረዳህ፣ ቢድአና ሽርክን እያወደምክ፣ የሱና ሰዎች የበላይ እያደረክ መሆኑን አትዘንጋ። በዚህ ላይ የቢድአና የስሜት ተከታዮች ሊበልጡህ በፍፁም አይገባም።

ኢብኑ ረጀብ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አለ።

ከሞተ በኋላ ስራው እንዳይቋረጥ የፈለገ ሰው ኢልም በማሰራጨት ላይ ይጠንክር።
{ التذكرة (55)}

ኢብኑ ባዝ አላህ ይማራቸውና እንዲህ ብለዋል።

ሙስሊሙ ወንድሜ ሆይ ኢልም ለሰዎች በማሰራጨት ላይ ልትጓጓ እንዲሁም ጥሩ ነሻጣና አቅም ሊኖርህ ይገባል። የባጢል ሰዎች ባጢልን በማሰራጨት ካንተ ሊበልጡ አይገባም። ሙስሊሞችን በዲናቸውና በዱንያቸው ጉዳይ ላይ አቅምህ በቻለው ልክ ለመጥቀም ሞክር።
[مجموع الفتاوى (67/6)]

የአላህ መልእክተኛም እንዲህ ብለዋል
【بلغوا عني ولو آية】
{ከኔ አንዲትም አንቀፅ ቢሆን አስተላልፋ}
http://t.me/WorldPeacefully
416 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ