Get Mystery Box with random crypto!

ስለ #እረኛዬ ድራማ በጥቂቱ... በደንብ አንብቡት! እረኛው ወንድ ነው እርሱም:- #ኢየሱስ ነ | Virtuous women💃💃let's learn

ስለ #እረኛዬ ድራማ በጥቂቱ... በደንብ አንብቡት!

እረኛው ወንድ ነው እርሱም:- #ኢየሱስ ነው!

በእረኛዋ ውስጥ እረኛችሁን ኢየሱስን እዩት!!!

#እረኛዬ ድራማ ድንቅ አገርኛ ፊልም ነው! ድራማው 4 ምዕራፎች 48 ክፍሎች ነበሩት! "እናናን" ገድሎ ይጨርሳል ብዬ አላሰብኩም! እረኛዬ ድራማ በእረኛዋ ሞት መደምደሙ ከለመድነው መንገድ ወጣ ይላል!

ደራሲዎቹ እናናን እና ዳዊትን፣ መንግሥቱን እና የጌጤን እናት አጋብተው፣ ወግዬን እና ሽፈራውን አዋደው፣ የሰፈሩን ሰው አያይዘው ... ቢጨርሱ ማናችንም አንቀየማቸውም! እነርሱ ግን ሌላ እይታ ሰጥተውን ተሰናበቱን!

ይህኛው እይታ ድራማውን የበለጠ ትክክል ያደርገዋል! እረኛዬ ተብሎ እረኛዋ ሰብሳቢ ብቻ ብትሆን አይገርምም! የቱንም ያህል ቢያስለቅሰን የእረኛዋ መሞት ትክክለኛ ነው! የተሟላ ትርጉም የሰጠው መሞቷ ነው!

እረኛችን ኢየሱስ ያደረገው ይህን ነበረ! የቱንም ያህል ብናዝንለት መሞቱ ነበረ ትክክል! ደራሲዎቹ የእናና ሞት ላይ እንደ ፈረዱ አብም ኢየሱስ ላይ ፈርዷል! ትክክለኛ ፍርድ ነበረ!

እረኛዋ በሞቷ ተስማምታ ነበረ! እረኛችን ኢየሱስም ለእኛ ለመሞት ፈቃዱ ነበረ!

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።” — ዮሐንስ 10፥11

ደግሞ ተዘራን እዩት ሞያተኛ እረኛ ነው፤ በጎቹን ለጥቅም ለመሸጥ አልከበደውም ነበረ!

“ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።” — ዮሐንስ 10፥13

እረኛዋ ከበጎቿ እንዲታረድ አትፈቅድም ነበረ! ትንሿን በግ ተዘራ ገደል እንዳይጥል እንዴት እንደለመነችው አስታወሳችሁ? ሲጥላት ገደል መግባቷስ? ጥጋቡ ያለችውን በግ አጋልጣ ላለመስጠት ምክንያቷ ምን ነበረ? ያርዱታል! ኢየሱስ እንዲህ ነው!

እረኛዋ በሞቷ አንድ እንዳደረገቻቸው ኢየሱስም በሞቱ አንድ አድርጎናል!

“ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።” — ዮሐንስ 10፥16

የአባባ በቃሉ ቤተሰብ አይሁዳውያን ይወክላል!
ጌጤ ከዚህ በረት አልነበረችም፥ እኛን አሕዛብን ትወክላለች! መጥታ አሮጊቷን መሪ ነው የሆነችው! አሁን የእግዚአብሔር ምስጢር በቤተክርስቲያን በኩል ነው እየተገለጠ ያለው!

ለእናና የተቀኙት ሙሾ፦

"ያንቺ ደም ዝም አይበል ከቶ እንዳይቀር ባክኖ፣
ይጠበው መንደሩን አስታራቂ ሆኖ"

እስኪ ግጥሙን በወንድ ጾታ አስቡት!?

ያንተ ደም ዝም አይበል ከቶ እንዳይቀር ባክኖ፣
ይጠበው መንደሩን አስታራቂ ሆኖ

የኢየሱስ ደም ነው ማጠብ የሚችለው!

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።” — 1ኛ ዮሐንስ 1፥7

የኢየሱስ ደም ነው የእርቅ መሠረት የሆነን! ከእግዚአብሔርም ጋር፥ እርስበርሳችንም!

“ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።” — ሮሜ 5፥9

“አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።” — ኤፌሶን 2፥13

በአንድ ወቅት ኢየሱስ በጾታ ሴት ሆኖ መጥቶ ቢሆን? በቀላሉ እንቀበለው ይሆን? ብለን አስበን እናውቃለን! አያችሁ የጌታ እናት ማርያምን የወደድናት በእናት በኩል ስለሰበኩን ነው! እናቶቻችንን ስለምንወድ!

እስኪ #በእረኛዋ #ውስጥ #እረኛችሁን ኢየሱስን #እዩት!!!

መልካም ቀን

--ፀሃፊ #በርናባስ #ዘመነ Barnabas Zemene
@womensletlearn