Get Mystery Box with random crypto!

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ለመጀመርያ አመት ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የድጋፍ ትምህርት | Wolkite University Students' Union

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ለመጀመርያ አመት ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የድጋፍ ትምህርት ተጠናቀቀ፡፡
****************************************************

በ2014 የትምህርት ዘመን አዲስ ለገቡ የ1ኛ አመት ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የመጀመርያው ወሰነ-ትምህርት የተማሪዎች ለተማሪዎች ድጋፍ ትምህርት መጠናቀቁን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት አካዳሚክስ ዘርፍ ገለፀ። በዚህ የድጋፍ ትምህርት የተሰጡ የትምህር አይነቶች English, Psychology, General Physics, Logic, Mathematics እና Economics መሆናቸውን፤ ዘወትር ከምሽቱ 1፡00-3፡00 እያንዳንዳቸው ከ14 ሰዓታት በላይ በተሳለጠ መልኩ እንደተሰጠና ከትምህርቱ በተጨማሪ የተለያዩ ስልጠናዎች እና ተማሪዎች ጊዜያቸውን እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው እንዲሁም በስነ-ልቦናም ሆነ በተግባር ለፈተና በምን መልኩ መዘጋጀት እንዳለባቸው ጭምር ምክክሮች እንደተደረጉ የድጋፍ ትምህርቱን በበላይነት ሲያስተባብሩ የነበሩት የወ/የ/ተ/ህ/አካዳሚክ ዘርፍ ተወካይ ተማሪ ሀይማኖት ገድፍ የተናገሩ ሲሆን የድጋፍ ትምህርቱ ተማሪዎቹ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ከሚያገኙት ትምህርት በተጨማሪ የሚሰጥ እንደመሆኑ እንደልብ እንዲሳተፉበትና እንዲከታተሉ ካለምንም የጊዜ ገደብ ሲሰጥ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡

አክለውም የድጋፍ ትምህርቱን በአግባቡ ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ከተከታታይ ምዘና አንዱ የሆነውን የአጋማሽ ፈተና ውጤት ክትትል መደረጉን አውስተው ተማሪዎቹ በጣም ጥሩ የሚባል ውጤት ማስመዝገባቸውን እና የድጋፍ ትምህርቱን በተከታተሉባቸው ጊዜያቶች ተማሪዎቹን ከተለያዩ አልባሌ ቦታዎች ከመዋል በመጠበቅ ጊዜያቸውን እንዲጠቀሙ ያገዘ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን የድጋፍ ትምህርቱ በቀጣይ የትምህርት ጊዜያትም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አሳውቀው የሚመለከታቸው አካላትም ለትምህርት አሰጣጡ የሚያስፈልጉ ግብአቶችንም ሆነ የማስተማርያ ቦታዎችን በይበልጥ በማመቻቸት እንዲተባበሩ በማሳሰብ ካለምንም ቅድመ-ሁኔታ የድጋፍ ትምህርቱን ሲሰጡ እና ሲያስተባብሩ ለነበሩ አባላት አድናቆታቸውን በመግለፅ ምስጋና አቅርበዋል።

በመጨረሻም ተማሪ ሀይማኖት ለሁሉም የመጀመርያ አመት ተማሪዎች ለማጠቃለያ ፈተናው መልካም እድል በመመኘት ሁሉም ተማሪዎች ራሳቸውን የሚፈትሹበትና ካለምንም መጨናነቅ በመረጋጋት የየራሳቸውን ብቻ እንዲሰሩና በመፈተኛ ቦታዎችም ቢሆን የፈተናን ህግና ስርአትን በመጠበቅ እንዲፈተኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የወ/ዩ/ተ/ህ/ የመረጃ እና ግንኙነት ዘርፍ ያነጋገራቸው የድጋፍ ትምህርቱን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች እንደገለፁት የድጋፍ ትምህርቱ በጣም እንደጠቀማቸው እና የወ/ተ/ህ/አካዳሚክ ዘርፍም ቢሆን በመማር ማስተማር ዙርያ ከገቡበት ቀን ጀምሮ ከጎናቸው ሆኖ እየረዳቸው በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበው አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የመርሃ-ግብር መዛባቶች በቀጣይ ላይ ይስተካከሉ በማለት ዩኒቨርሲቲውም እያደረገላቸው ላለው ነገር ሁሉ ያመሰገኑ ሲሆን የድጋፍ ትምህርቱን ያገኙት በተማሪዎች ህብረት አካዳሚክ ዘርፍ አስተባባሪነት ቢሆንም የግል ጊዜያቸውን ሰውተው እና በእረፍትም ጭምር ወደ ቤታቸው ሳይሄዱ ላስተማሯቸው ተማሪዎች በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።


#ዘገባው የወ/ዩ/ተ/ህ/ የመረጃና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ነው





የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት
"OUR REWARD IS STUDENT'S HAPPINESS!!!"


የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook
Wolkite University Students Union
Telegram @WkUSU
Website https://wkusu.com

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
EMAIL
student.union@wku.edu.et
ለአብሮነቶ ከልብ እናመሰግናለን