Get Mystery Box with random crypto!

ፍልስፍና

የቴሌግራም ቻናል አርማ wisdom_wisdom — ፍልስፍና
የቴሌግራም ቻናል አርማ wisdom_wisdom — ፍልስፍና
የሰርጥ አድራሻ: @wisdom_wisdom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 718
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ ቻናል መግቢያም ሆነ አጥር የለውም እንደ ሰው ለሚያስብ ብቻ ተከፍቷል!"
ጲላጦስ

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-19 16:25:41 ከ ፍልስፍና ዓለም
ፍልስፍና እና የፍልስፍና ሀሳቦች ወጎች ተረቶች አባባሎች በዚ ቻናል ላይ አቀርብላቸዋለው

ሀሳብ እና አስተያየት ካላቹ

@Consciousness10 ላይ አድርሱኝ

በፍልስፍና ዙሪያ የተነሱትን ሀሳቦች እስከ ጭብጣቸው እንዳስስሳለን ወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማረግ አብሮነታቹን አሳዩኝ
https://t.me/Philosphyloves
155 views., 13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 20:20:56 የ'በራለት' እና የፍላጎት ክብ ምልልስ(Appetitive Circular Rotation) በፍልስፍና መነፃር?

በህንድ የ"ፍልስፍና" ታሪክ ውስጥ ታዋቂነትን እንዲሁም ቅቡልነትን ካተረፉ ተወዳጅ ዮጊዎች መካከል አንድ ሰው አለ...!የተመስጦ ጥልቀት-ምጥቀት ያሳየ ያ ሰው ቡድሀ!(አንድ የበራለት ሰው ማለት ነው ቀጥተኛ የስሙ ትርጉም!)።በታሪክ ውስጥ ብዙ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችን አልፈዋል...ከኢየሱስ እስከ ሙሐመድ (ረ.ዐ.ሱ)፣ከሶቅራጠስ እስከ ማርክስ፣ከታለስ እስከ ዳርዊን፣ከጋሊሊዮ እስከ አንስታይን፣ከዳቬንቺ እስከ ፓብሎ ፒካሱ.....አለም የስር ነቀል ለውጦችን ተመልክታለች።ሁሉም በነበሩበት ፈርጅ ትልቅ ለውጥ አምጥተዋል።

ይሄንን ስር ነቀል የአስተሳሰብ እና የድርጊት ለውጥ አሜሪካዊው ፈላስፋ ቶማስ ኩን "Paradigm Shift (የፓራዳይም ለውጥ)" ይለዋል ላይመለስ የቀሩ አስተሳሰቦችን...! በ"መንፈሳዊው የፍልስፍና" ታሪክ ውስጥ ለሰው ልጆች የማስተዋል እና ከሁለንተናዊው ማንነት ጋር "እንዲዋሀዱ" የጣሩ ብዙ አሉ...ከነዚህም አንዱ ሲድሀርታ ጉተማ ቡድሀ!

ቡድሀ ስለሰው ልጅ "የስቃይና የመከራ ምንጭ የገዛ ራሱ አለማዊ ምኞትና ጉጉት እንደሆነ" ይነግረናል፤ ሰው ከእውቀት በራቀ ቁጥር ሰነፍ እንዲሁም ለመከራ የተጋለጠ ይሆናል።
"አለማዊው ምኞትና ጉጉቶችን መግራት የቻለ እሱ ከስቃይና ከመከራ የራቀ ነው"።

<<ይህንን ተረዱ! ደረቅ አጥንተን በደም ለውሳችሁ ለውሻ ብትሰጡት ውሻው እስኪ ደክመው ድረስ ከአጥንቱ ጋር ታግሎ ጥሎት ይሄዳል፤እንዲሁም ጉጉት ለሰው ልጅ ለውሻ እንደተሰጠው አጥንት ነው፤ህይወቱን በመከራ እንዲገፋ አድርጎት እንዲሁ ጥሎት እንዲሄድ ያደርጋል!>>ይለናል ቡድሀ። ቡድሀ የሰውልጅ እንዴት ከራሱ ጋር መስማማት እነሠ መዋሀድ እንዳለበት መንገዱን ተመስጦ እንደሆነ ያስረዳናል።ሰው በስሜታዊው ባህሪ ስግብግብ፣ ዝሙት፣ማግበስበስ፣ማጭበርበር... ወ.ዘ.ተ ነገሮች አለማዊውን የተያያዥነት ችግር እና መከራ ፅዋ እንተጎነጨ እንደሆነ እንዲሁም የእነዚህ ሂደቶች መጨረሻ መከራውም ሆነ ውድቀት ወደ ራሳችን እንደሚመጣ እናም ልብ ማለት እንደሚገባን ያሳስበናል።

ብዙ ጊዜ የቡድሀን የ"ምንምነት(nothingness)" ሀሳብ ሳስታውስ አንድ የጃን ዴ ላ ብሩየር አባባል ትውስ ትለያለች እንዲ የምትል፥<<ህይወት ለስሜት አሳዛኝ ታሪክ(ትራጄዲ) ስትሆን ለአሳቢያኑ ደግሞ አስቂኝ ክስተት ናት(𝑙𝑖𝑓𝑒 𝑖𝑠 𝑎 𝑡𝑟𝑎𝑔𝑒𝑑 𝑓𝑜𝑟 𝑡ℎ𝑜𝑠𝑒 𝑤ℎ𝑜 𝑓𝑒𝑒𝑙,𝑎𝑛𝑑 𝑐𝑜𝑚𝑒𝑑𝑦 𝑓𝑜𝑟 𝑡ℎ𝑜𝑠𝑒 𝑤ℎ𝑜 𝑡ℎ𝑖𝑛𝑘)>>በእርግጥ ቡድሀ የሚለን ይሄንን ይሆን?
የሰው ልጅ በምኞት እስር ቤት ውስጥ ሲሆን የማብቂያ ፍላጎት አይታየውም አንዱ ሲሞላ ለሌላው ይሮጣል...ሌላው ሲሞላ ደግሞ ፍላጎት....በክብ ውስጥ እሽክርክሪት(Circular Rotations) ውስጥ ይኳትናል።ቡድሀ እንዲ ይላል<<የሰው ልጅ ምኞት ገደብ የለሽ ነው!የሰው ልጅ የእርካታ ምንጩ ከውስጡ ነው፤በምኞቱ ግን አለመርካት ብቻ ሳይሆን ስቃዩም እየጨመረ ይሄዳል... እናም ለምኞትህ ልጓም አበጅለት! ምኞትህ ከጨመረ ቁጣ ደስታና እርካታህ እየቀነሰ እና እነከፋ ከመሄዱም ባሻገር መጨረሻህ ወደ እብደት መድረስ ብቻ ነው....።>> የሰው ልጅ ከምኞትና ከፍላጎት ባህር ወጥቶ ከተፈጥሮ ጋር መዋሀድ አለበት።

ከዘመናዊው ፈላስፎች መካከል ደግሞ የጀርመኑ ፈላስፋ አርተር ሾፐንሀወር በዚህ የፍላጎት ክብ ዙሪያ(Appetitive Circular Rotation) ከቡድሀ ጋር ተመሳሳይ ሀሳብ ያቀርባል።በእርግጥ አርተር የኒርቫና እሳቤ እና የቡድሀ አስተምሮ በጥቂቱ አድናቂ ነበር።አርተር እንደ ቡድሀ ፍላጎት ማብቂያ እንደሌለው ይስማማል ነገር ግን ለአርተር መጨረሻ ያለው ነገር ስኬት ነው።<< አብዛኛው ሰው በጥቂት እውቀት እና በብዙ ፍላጎት የተሞላ ነው>> ይለናል፤ ታድያ አርተር የፍላጎትን የበላይነት ሲገልፀው ልክ"እውር ጉልበተኛ" አድርጎ ነው እኛ ደግሞ "አይናማ እና ልፍስፍስ" ስለሆን ፍላጎታችንን ተሸክመን በክቡ ዙሪያ እንመላለሳለን። አርተር ከዚህ ለማምለጥ ያስቀመጠው መንገድ በውስጣችን ያለውን እውቀት እና አዋቂነት በማሳደግ ፍላጎትታችንን ማዳከም ከተቻለም (ይቻላል!) መግደል ነው<<ፍላጎቶቻችንን ይበልጥ ባወቅናቸው ቁጥር እኛን የመቆጣጠር ብቃታቸው እንዲሁ ይዳከማል!.....አለምን ማሸነፍ ከውስጣዊ ማንነት ይጀምራል የምንለው ለዚሁ እውነታ ነው።>> ይለናል።

ፍላጎታችን ማብቂያ ይኖረው ይሆን?ፍላጎት በራሱ ምንድነው?...መሰል ጥያቄዎች ማንሳታች እና መመርመራችን ተገቢ ነው።ፍላጎት ብዙ ጊዜ የምንፈልገው ነው ወይስ የሚያስፈልገን ነገር ነው?የምንፈልገው ከሆነ ያልተሟላልን የሚያስፈልገን ነገር ነው ነገርግን የሚያስፈልገን ከሆነ ደግሞ ያንን ነገር ልናገኘው የምንችለው ይሆናል እንደማለት ይሆናል፤ስለዚህ ፍላጎት አንለውም ምክንያቱም ማግኘታች ስለማይቀር ለማናገኛቸው ነገሮችስ ግን?ፍላጎቶቻን ለማይገኙ ነገሮችስ....? እነዚህ ራሳቸው የቻሉ ዘርፍ የሚፈልጉ ጥያቄዎችን ፍልስፍና ታስተናግዳለች።ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እና ለተሰበሰቡ ህዝብ ስለ"መጨነቅ" አላስፈላጊነት ሲያስተምራቸው<<በመጨነቅ ከቁመቱ ላይ አንዲት ስንዝር የሚጨምር እሱ ማነው?>>በማለት የፍላጎቶቻችን የማያበቃ መጨነቅ አላስፈላጊነት ይነግረናል።በሾፐንሀወር አባባል እናብቃ...
<<ብዙውን ጊዜ ከጥበብ የራቁ ሰዎች ምሉዕነት የሚመጣው ከገንዘብ ይመስላቸዋል። ሁሉም ነገር የተሟላለት ሰው ጥበብ ከጎደለችው እንደሱ መከራን የሚቀበል ሰው ያለ አይመስለኝም። የሕይወት መንገድ ሀብት ሳትሆን ጥበብ ነች።>>

ተፃፈ በይሁዳ


ምንጮች;-ጥበብከጲላጦስ
the Teaching of Buddha መፅሀፍት

@Wisdom_Wisdom
208 views., edited  17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 21:55:49 የእለቱ መልእክት

1]ምድራዊ ህይወት ውስጥ ለሚፈጠሩብህ ነገሮች በሙሉ አእምሮህ ዝግጁ አድርግ!

2]ምርጫ አለህ ደስተኛ የመሆን አሊያም በሀዘን መቆየት?

3]ሰው ሁን!

4]አቅምህን ለምታሸንፍበት ነገር በሰፊው አውል ብልህ ከጅማሮ ፍፃሜውን ይረዳልና!

5]ሀብታም ነህ እንግዲያውስ ስለምን እንደደሀ ትኖራለህ?

6]ሰዎችን ለማሸነፍ ሁለት የተመረጡ የብልህነት መንገዶች አሉ አንደኛው ማስመሰል(በብልህነት ማቀድ) ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ፍርሃት በውስጣቸው ትፈጥራለህ! ነገርግን ራስህን ለማሸነፍ አንድ መንገድ ብቻ አለ....ተ.መ.ስ.ጦ!

6]ዋጋህን ከፍ ባለ ቁጥር ተፈላጊነትህ በዛው ልክ የገዘፈ ይሆናል!

7]ስለእነሱ ምን አገባህ?

8]ልብህን በአእምሮዎች ቲያትር ቤት አትፈልጋት!

9]ራስህን ከመዋሸት በላይ አስከፊ ነገር የለም!

10]ብዙ አታውራ በተቻለህ መጠን ቃላቶች የተመጠኑ ግልፅ ይሁኑ!

@Wisdom_Wisdom
245 views., 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 11:58:58
"ህይወት የህይወት ትርጉም እንድትፈጥር እድል ከመሆን የዘለለ በራሷ ትርጉም አልባ ናት!"

ራጅኔሽ ባግዋን

@Wisdom_Wisdom
365 views., 08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 16:53:20 እውነት እና ፍልስፍና?

እውነት ምንድነው?እውነት ማነው?እውነት የት ነው?ፍፁም ወይስ አንፃራዊ ወይስ የለም?እውነት ምንድነው ብሎ መጠየቅ በእርግጥ አስፈላጊ ነው?ለምን እንጠይቃለን ግን?¿......እነዚህን መሰል ጥያቄዎች ፈላስፎችም ሆኖ ተመራማሪዎች የሚጠይቁት ነው ይዘቱ ይቀያይር እንጂ! ከዘመን ዘመን እየተጠየቀ 'መልስ' ተብለው የተሰጡትን ሀሳቦች ችግሩን እየነቀፈ እና እያረቀቀ ያለንበት የእውነት 'ጥያቄ መልስ' ላይ ደርሰናል።ከዚህ በኋላስ ግን..?

በሰዎች የየለተለት እንቅስቃሴ ውስጥ እውነት እንደብርቅ እየተቆጠረች እና እየደበዘዘች ጉዞዋን በዝግመት እየቀጠለች ላለችው እውነት ትጠፋ ይሆን? ማለት ተገቢ ጥያቄ ነው! ለምን እውነት መናገሩ ሆነ ማሰቡ ከበደን?እነዚህን የማህበረሰብ የእውነት 'ቀውስ' ለመፈተሽ መጀመሪያ <<እውነት ምንድነው?>> የሚለው የጲላጦስ ጥያቄ በፈላስፎቹ ሀሳብ ማወቅ እና ማሸት ያስፈልጋል።ሌላውስ?

ከፍልስፍና መንደር ስንዘልቅ "የመጀመሪያዎቹን" የግሪክ ጠበብቶች እናገኛለን።ብዙዎቻንን እውነት ምን እንደሆነ በፍልስፍና ለማወቅ የተነሳን ጊዜ የጥንት እሳቦቶቹን ሰምተን ወይም አንብበን ስለሆነ እውነትን ከዘመናዊው ፍልስፍና አንፃር መቃኘቱ የተገባ እንደሆነ እሙን ይመስለኛል።

እውነት ከዘመናዊነት ፍልስፍና ማለትም ከፈረንሳዊው ሬኔ ዴካርት ፍልስፍናዊ አቅጣጫዎች በፊት በመካከለኛው ዘመን በእግዚአብሔር መኖር ጋር የተገናኘ ባህሪ ተሰጥቶት ፍፁማዊነትን የተላበሰ የእውነት ትርጓሜ ነበር ከእሱ በፊት በጥንቱ ደግሞ አንፃራዊ እና ፍፁማዊነትንም የያዘ የነበረው እውነት በጥንቱ በእነፊሮ፣በመካከለኛው በቶማስ አኳይነስ እንዲሁም በዘመናዊው ደግሞ በሦስት ታላላቅ ፈላስፎች የስህተት ችግርን በመተቸት እየረቀቀ መጥቶል።

እውነት ከድህረ ሶቅራጠስ እስከ ድህረ ዘመናዊነት(Post-modernism) ዘመን ድረስ በፈላስፎቹ የህይወት ምልከታ ጉዞ የተቃኘ ነበር(ነውም!)። በዘመናዊው ፍልስፍና እውነት የመፈተሽ ጉዞ በእነኒቼ፣በርትናንድ ረስል፣ ኢማኑኤል ካንት፣ እንዲሁም ሌሎች ታላላቅ አሳቢያን አስተሳሰቦቹ ስያሜዎች እየተሰጣቸው እና እየረቀቁ ያደጉት በዘመናዊ(Modern Philosophy) ዘመን ነበር።በእርግጥም በቀደሙት ጊዜያት ስያሜ ቢኖረው እንደዘመነኛው የእውነት መልስም ሆነ ጥያቄ ረቀቀ ያለ አልነበረም።

በዋናነት በ3ት ፅንሰሀሳቦች ይመደባል፦

1)Correspondens(ህገ-መጣጣም)

፦ይህም እውነት የእውነት ፅንሰሀሳብ ዘረፍ የሚለው ነገር ነገሩ በገሀዱ አለም ካለው ነገር ጋር ሲመሳሳል ነው ማለትም አንድ ነገር እውነት ነው የምንለው ከነገሩ ጋር የሚገናኝ ሌላ እውነት የሆነ ነገር ሲኖር ነው።ለምሳሌ"ወተት ነጭ ነው"መሆኑን እውነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ወተት በራሱ ቀለሙ ምን እንደሆነ "ነጭ ነው" ያልነው ሀሳብ ይደግፍልና እንደማለት ነው።በህገ-መጣጣም ውስጥ ቃሉ በሌላ ቃል ስለተደገፈ ወይም ስለተገናኘ ብቻ እውነት ነው ማለት አይቻልም(correspondence is not a word by word connecting of a sentence to its reference.)።
በዚህ የእውነት ዘርፍ ተጠቃሽ ፈላስፎች ጆን ሎክ፣ በርትናልድ ራስል ጉልህ አስተዋፅኦ አድርገዋል።

2)Coherence Theories(ህገ-መስማማት)

:-ይሄኛው ከህገ-መጣጣም(Correspondence) ጋር ተመሳሳይነት ቢኖራቸው ልዮነታቸው የጎላ ነው።በህገ-መስማማትእውነት ነው ብለን የምናምነው ነገር በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ካለው ነገር ጋር ሲጣጣም ነው።ለምሳሌ Elephants are gray (ዝሆን ግራጫ ነው!)

3)Pragmatism(ተግባራዊነት)
፦ በ19 እና 20ኛ ክፍለዘመን የተጀመረ የአሜሪካ ፍልስፍና እሳቦት ነው።ከስነ-ምግባር ፍልስፍና ስናየው እንደውጤት ተኮር ስነ-ምግባር አስተምህሮ(Consequence Ethics theory) ነገሩን በውጤቱ ላይ ተመርኩዘን እውነት መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን የሚለው ነው።

ሌሎችም አሉ ለምሳሌ..
1]Deflationary Theories
2]Semantic Theory

አሁን ያለንበት ድህረ-ዘመናዊነት (Post-Modernism) ስለእውነት ያለው እሳቤም "የጋራ የሆነ የእውነት መለኪያ ከለሌ እውነት አንፃራዊ ነው" አንድ መነሻ እና መፈረጃ መንገድ እስከሌለ እውነት የግል ምልከታ ነው'።ታዋቂ ድህረ ዘመናዊው ፈላስፎች መካከል አንዱ ሊዪታርድም እንዲህ "የራሳችን እውነት የምንለው ነገር በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲሆን መጠበቅ የለብን!"ይለናል።በድህረ ዘመናዊው አለም ያንተ/ያንቺ እውነት ለሌላው እውነት ላይሆን ይችላል።

ከፓለቲከኛ ፈላስፎች መካከል አንዱ ፋኮ ነው!ፋኮም እውነትን እንዲህ ይገልፀዋል<<እውነት ሁሌም ሀይል ባለው ዘንድ ተሰርቶ ይቀርባል>> በእርግጥ ይሄ ሀሳብ በጀርመናዊው ፍሬድሪክ ኒቼ "power of well" ጋር ተመሳሳይነት ይታይበታል ኒቼ እውነትን በThe spake of Zarathustra መፅሀፉ በኩል እንዲህ ይለዋል<<እውነት ባለበት ሀይልን አገኘሁት፣ሀይል ባለበት ሁሉ እውነት አገኘው!>>ቀጥሎም<<ሁሉን የሚያስማማ አንድ እውነት የለም>>አለ።ይሄ በእርግጥ ለዘመናዊው የእውነት ጥያቄ ርዮት ራሱን የቻለ ደጋፊ ሀሳብ ነበር።

<<.....እውነት ምንድነው?.....>>
ጲላጦስ

ተፅፈ በይሁዳ

@Wisdom_Wisdom
@Wisdom_Wisdom
466 viewsʙ-Ʀᴀʙʙɪᴛ, edited  13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 16:53:09
355 viewsʙ-Ʀᴀʙʙɪᴛ, 13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 14:09:27 አራቱ ልዕልናዎች (The Four Cardinal Virues)
***
ልዕልናዎች (Virtues) አመክንዮ ላይ የተመሰረቱ የአእምሮ ባህርያት ሲሆኑ እነዚህም ልዕልናዎች የሰውን ልጅ ደስታ እንደሚያጎናፅፉ ይታመናል፡፡ በታላቁ ፈላስፋ ፕሌቶ መሠረት ደስታን የሚያጎናፅፉ የህይወት ልዕልናዎች አራት ናቸው፤ እነሱም፣
1) Ann (Wisdom/Prudence) - ለትክክለኛ ድርጊት ትክክለኛ ጊዜና ትክክለኛ ቦታ ማወቅ፣ ‹‹ምን?እንዴት? መቼ? የት? ማን?›› የሚሉትን ጥያቄዎች የማቀናጀት ችሎታ፤ ይሄ እሴት በተለይ ህዝብን ለሚመሩ ሰዎች እጅግ የሚያስፈልግ እሴት ነው እንደሆነ ይታመናል፤
***
2) ታጋሽነት (Temperance/Moderation) | ስሜትን የመቆጣጠርና የመግራት ችሎታ፤ ይህ ልዕልና ለሁሉም የህብተሰብ ክፍል አስፈላጊ ቢሆንም፣ በተለይ ግን ለአምራቹ የህብረተሰብ ክፍል ይበልጥ ጠቃሚ የሆነ ነው፤
***
3) ጉብዝና/ደፋርነት (Courage) ፍርሃትን ማሸነፍ፣ በአስቸጋሪ ጊዜ መፅናት፣ አቋም ያለው፣ በወቅታዊ ማዕበል በቀላሉ አለመናወፅ፤ ይሄ ደግሞ ለወታደሮች እጅግ ጠቃሚ የሆነ እሴት ነው፡፡

4) ፍትሐዊነት (Justice) ፍትሐዊነት ለአንድ የህብረተሰብ ክፍል ተለይቶ የሚሰጥ እሴት ሳይሆን፣ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚመለከት ነው፡፡
***
አሪስቶትል እነዚህን የፕሌቶ አራት ልዕልናዎች ይቀበልና እንደ "ጓደኝነት" ያሉ ሌሎች ልዕልናዎችንም ይጨምርበታል፡፡ ቶማስ አኳይነስ ግን እነዚህን የፕሌቶና አሪስቶትል ልዕልናዎች ‹‹የዚህ ምድር ልዕልናዎች ናቸው›› ይላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን፣ ያሉን ልዕልናዎች እነዚህ ምድራዊ ልዕልናዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ሦስት የሰማያዊው ዓለም ልዕልናዎችም እንዳሉነ ቅዱስ ጳውሎስን በ1ቆሮ 13:13 ይጠቅሳል፡፡
በዚህም እምነት፣ ተስፋና ፍቅር – faith hope and love በአኳይነስ አመለካከት ዘላለማዊ ህይወትና ደስታን ለመጎናፀፍ እነዚህን ሦስት ሰማያዊ ልዕልናዎች የግድ ማሟላት እንዳለብነ ይነግረናል፡፡

@Wisdom_wisdom
456 viewsPeter, 11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:44:01
ለእስልምና እምነት ተከታዮች ቤተሰቦቻችን መልካም ኢድ አልሃ(አረፋ)



መልካም
በዓል!



እንኳን
አደረሳችሁ


@Wisdom_Wisdom
440 viewsʙ-Ʀᴀʙʙɪᴛ, 11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 12:34:28 https://t.me/codewithas
ይሄን ቻናል ስለ #CODEING & #PROGRAMMING- *DATA SINCE, *JAVA SCRIPT, *RUBY, *PYTHON,......etc, የመሳሰሉትን ትምህርቶች የሚሰጥበት CHANNEL ሲሆን

ማንኛውም ሰው ሊማርበት የሚችል እና የዚህ channel አላማም ሰዎችን አስተምሮ ለስራ ማብቃት እንዲሁም ትልቅ ደረጃ ላይ ማድረስ ነው

ይህን channel Share በማድረግ ይተባበሩ

#በተጨማሪ ይህን channel share ላደረገ 10 ሰው ነፃ የ online course አንሰጣለን
460 viewsʙ-Ʀᴀʙʙɪᴛ, 09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 12:17:50
421 viewsʙ-Ʀᴀʙʙɪᴛ, 09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ