Get Mystery Box with random crypto!

እንዴት አረፈዳችሁ በአንድ ወቅት አንዲት ሴት ልጅ ህይወቷ የተመሰቃቀለ እንደሆነ እና አንዱን ችግ | Wisdom Club🇪🇹

እንዴት አረፈዳችሁ

በአንድ ወቅት አንዲት ሴት ልጅ ህይወቷ የተመሰቃቀለ እንደሆነ እና
አንዱን ችግር ስትፈታ ሌላ ችግር እንደሚገጥማት፤ መኖር እንደከበዳታ እና
ከዚህ በላይ ችግሮቿን መቋቋም እንደማትችል አቤቱታዋን ለአባቷ
አቀረበች፡፡
አባቷ የምግብ ሰራተኛ ነው፤ እናም ወደ ማብሰያ ክፍል ይዟት ሄደ፡፡
ሶስት ድስቶችን ውሃ ሞልቶ እሳት ላይ ጣዳቸው፡፡
በድስቶቹ ውስጥ ያለው ውሃ መፍላት ሲጀምር በአንዱ ድስት ውስጥ
ድንች፤ በሌላኛው ውስጥ እንቁላል፤ በሶስተኛው ውስጥ ደሞ ቡና
ጨመረባቸው እና ከደነው፡፡ እናም ምንም ሳይናገር መጠበቅ ጀመረ፡፡ ልጁ
መነጫነጭና ትዕግስት በጎደለው መልኩ ምን ሊያረግ እንደሆነ ለማየት
መጠበቅ ጀመረች፡፡
ከ20 ደቂቃ በኀላ እሳቱን አጥፍቶ ድንቹን፣ እንቁላሉን አውጥቶ በአንድ
ሰሃን አስቀመጠ፡፡ ቡናውን በሲኒ ቀድቶ አስቀመጠ፡፡
"ልጄ አሁን ምን ይታይሻል? በማለት ጠየቃት፡፡ ልጅ "በቁጣ ስሜት
ሁና ድንች፣ እንቁላል፣ ቡና" አለች፡፡
"በደንብ ተመልከች፤ ድንቹን ንኪው" አላት፡፡ እንዳላት አድርጋ ድንቹ
ጥንካሬውን እንዳጣ ተገነዘበች፡፡
"እንቁላሉንም ስበሪው" አላት፡፡ ሰበረችው ነገር ግን አስኳሉ ሌላ
ጠንካራ እና የሚያቃጥል አካል ሰርቷል፡፡
በስተመጨረሻ ከቡናው ፉት እንድትል አዘዛት፡፡ እሷም ቀምሳ ደስ
የሚለው ጣዕሙ የፊቷን ፈገግታ ሲቀይረው ታወቃት፡፡
"አባቴ ይህ ምንድን ነው?" አለች፡፡
አባት ማብራራት ጀመረ፡፡ "ድንቹ፣ እንቁላሉ እንዱሁም የቡናው ዱቄት
ሁሉም እኩል የፈላ ውሃ ውስጥ ነው የገቡት፡፡ ነገር ግን ሁሉም ለፈላው
ውሃ የሰጡት ምላሽ የተለያየ ነበር፡፡
ድንቹ በፊት ጠንካራ ነበር፤ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ጥንካሬውን
አጥቶ ልፍስፍስ ሆነ፡፡
እንቁላሉ በፊት በቀላሉ ከተሰበረ ሜዳ ላይ የሚፈስ ልፍስፍስ አስኳል
ነበር፡፡ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ውስጡን አጠንክሮ መጣ፡፡
ከሁሉም የሚገርመው ግን የቡና ዱቄቱ ነው፡፡ በፈላ ውሃ ሲፈተን
እራሱ ውሃውን ወደ ጣፋጭን መልካም ጠረን ቀይሮ አዲስ ነገር ፈጠረ፡፡
አንቺ የትኛው ነሽ?"
ችግር ሲገጥማችሁ የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው ?
እንደ ድንቹ መልፈስፈስ ? ወይስ እንደ እንቁላሉ ውስጥን ማጠንከር ? ወይስ እንደ ቡናው በፈተና ውስጥ ድንቅ ማንነትን ለሌሎች የሚያበራ ማንነትን ይዞ መገኘት ?
ከወደዳቹህት ላይክ እና ሸር አድርጉት
መልካም ቀን