Get Mystery Box with random crypto!

የህፃኗን ህይወት እናድን እኔ የምችለውን ተወጥቻለሁ እናንተስ? ህፃን ሰበነማርያም ትባላለ | ወሸባ

የህፃኗን ህይወት እናድን እኔ የምችለውን ተወጥቻለሁ እናንተስ?

ህፃን ሰበነማርያም ትባላለች ገና የ1 አመት ከስድስት ወር ህፃን ስትሆን በዚህ ዕድሜዋ በልብ ህመም እየተሰቃየች ትገኛለች።

የተለያዩ ህክምና ተከታትላለች ነገር ግን ዉጭ ሀገር ሂዳ ካልታከመች ህይወቷ አደጋ ላይ እንደሆነ በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል ተገልጿል።

ስለሆነም እያንዳንዳችን ቢያንስ ተርፎን ለአንደ ቀን መዝናኛ የምናወጣውን ወጭ ለዚች ታዳጊ ህይወት ብንረዳ ከፈጣሪ በረከትን የምናገኝ ይሆናል።

የህፃኗ አባት ማስተር አበራ ለብዙ የጎንደር ታዳጊ ህፃናት እና ወጣቶች ከሱስ የፀዳ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ የሚገኝ ወጣት ነው ።

መልካም ስራ አልፎ ይጠብቃልና እኛም የዚህን ወጣት ልጅ ህይወት ለማዳን በተቻለ መጠን የምንችለውን እንደግፍ መርዳት ለምትፈልጉ፦

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ➺1000450728946
አቢሲኒያ ባንክ➺41993995
አዋሽ ባንክ➺01347564797700
እናት ባንክ➺0371122231034001 ድጋፍ እናድርግ።

መርዳትና አቅም የሌላችሁ ወገኖቸ ደግሞ ሌሎች እንዲረዷት ሼር በማድረግ ፈጣሪ ይማርሽ እንበላት።