Get Mystery Box with random crypto!

‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለ | የእንጦጦ መ/ስ/ቅ/ሥ/ቤ/ክ ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት

‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡››

#ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት

#ሀምሌ 24/2014 ዓ.ም በእንጦጦ መንበረ ስብሀት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ #በሥርዐተ_ተክሊል ጋብቻህን የፈጸምከው #የሰ/ት/ቤታችን አባል ወንድማችን ዲ/ን ታምራት ስዪም እና እህታችን ራህዋ የማነ ፤ የፈጸማቹሁት ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሣራን፣ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ÷ ያጣምራቹ ÷ ያዋህዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኃላ ይከተላችሁ፡፡

<<ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንደሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡>>

#ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፓሊካርፐስ በላከው መልእክቱ፡፡

<ከተጋባቸሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ፡፡ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፈቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>>
#ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ቅዱስ አጼ ዘርአያዕቆብ፡፡

◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:22)
----------
22፤ ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤

23፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

24፤ ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።

25-26፤ ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤

27፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።

28፤ እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤

29-30፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል።

31፤ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።

32፤ ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።

33፤ ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ።

የመንበረ ስብሐት ቅ/ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን የውሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
#ኦዲዮቪዥዋል ክፍል

ለመቀላቀል ➠
Facebook https://www.facebook.com/1880533115515403/posts/2831103630458342/?app=fbl

Telegram
https://t.me/weludebirhane

YouTube



◈ ገፆቹን #Like , #Follow , #Subscribe እንዲሁም የሚለጠፉትን #Share , #Like ያድርጉ!.