Get Mystery Box with random crypto!

#Tigray ትግራይ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ቀደመው የመማር ማስተማር ስራቸው ለመመለስ ከፍተኛ ር | Students News & Well laptop®

#Tigray

ትግራይ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ቀደመው የመማር ማስተማር ስራቸው ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከነዚህም ውስጥ የኣክሱም እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው መማር ያልቻሉ ተማሪዎች በአጭር ቀናት ውስጥ በስልክ እየደወሉ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለማስታወሻ ፦ https://t.me/welllaptops

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ለሁሉም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ላልተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች ቀጥሎ የተቀመጡትን መረጃዎች ከሚያዝያ 16-20/2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ሰዓታት ብቻ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመጠቀም መረጃዎች እንዲያቀብሉ ጠይቋል።

ተፈላጊ መረጃዎቹ ምንድናቸው ?

ሙሉ ስም
የመታወቅያ ቁጥር
ትምህርት ክፍል
የስንተኛ ኣመት ተማሪ መሆንዎ፡

እነዚህን መረጃዎች የመላኪያ ስልክ ቁጥሮች ፦

1. EiTM - 0984026089 / 0984026059
2. MIT - 0984026727
3. CHS - 0984023986
4. CVS - 0984024072
5. CLG - 0984023987
6. CSSL - 0984023985
7. CBE - 0984024069
8. IPHC - 0984025512
9. CDAaNR - 0984025593
10. CNCS - 0984025582
11. Other Universities - 0984025589

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፅሁፍ መልእክቱን ሲልኩ #በእንግሊዘኛ እንዲልኩ አሳስቧል።

ዩኒቨርሲቲው በሌሎች የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩና በጦርነቱ ምክንያት ያቋረጡ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ከላት የተጠየቁትን መረጃዎች ፤ከዛ በተጨማሪ ሲማሩበት የነበረውን የዩኒቨርሲቲ ስም በማከል መረጃ እንዲያሳውቁ ጥሪውን አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፥ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎቹን በቅርብ ጊዜ እንደሚጠራ ገልጿል።

https://t.me/welllaptops