#SamaraUniversity በ2014 ዓ.ም ወደ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ግንቦት 13 እና 14/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 15 እስከ 17/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ • የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው • የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው • ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው • 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (8) • ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ • የስፖርት ትጥቅ ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል። ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ፦ www.su.edu.et መጎብኘት ትችላላችሁ፡፡ 4.4K views¶Well CR7 G, 17:20