Get Mystery Box with random crypto!

የህወሓት መግለጫ ዓላማው ምንድነው በሴራ ሠላምን ማደናቀፍም ይሁን ኢትዮጵያን ማሸነፍ ከቶም አይ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የህወሓት መግለጫ ዓላማው ምንድነው

በሴራ ሠላምን ማደናቀፍም ይሁን ኢትዮጵያን ማሸነፍ ከቶም አይቻልም ህወሓት የናይሮቢው የፊርማ ሥነ ሥርዓት እንደተከናወነ በማህበራዊ ትስስር ገፆቹ "ስምምነቱን አልፈረምኩም" የሚል መግለጫ አውጥቷል። በዚህም "የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በደቡብ አፍሪካው ስምምነት ህወሓትን ወክሎ የሄደ አካል የለም፤ ስምምነቱ ላይ የህወሓት ታጣቂ ትጥቅ ይፈታሉ ተብሎ የተገለፀውም ህወሓት ጦር የሌለው መሆኑን ለዓለም ህዝብና ለአጋሮቻችን እንገልፃለን፤ በአጠቃላይ ሰላም መምጣቱን ግን እንደግፋለን" ይላል። አስቂኝ የጅል ቀልድ የሚመስል፣ ግን ህወሓትን መሰሪነት የሚያንፀባርቅ ተረክ ይመስለኛል

ህወሓት በአንድ በኩል የሠላም ስምምነቱን ተቃውሞ "እኔ አልፈረምኩም" እያለ፤ በሌላ በኩል ደግሞ "ሠላምን እንደግፋለን" የሚል የለበጣ ዲስኩር አስነብቧል። እዚህ ላይ የሚመለከታቸው አካላት ጥንቃቄ ማድረግ ያለባቸው ይመስለኛል። ያም ሆኖ፣ በበኩሌ የዚህ መግለጫ ዓላማ ሶስት ጉዳዩችን ለማሳካት ያለመ  ይመስለኛል። እነርሱም፦

1ኛ) የሠላም ስምምነቱን የማይፈልጉ ወገኖች እንዳሉ አስመስሎ በማቅረብ፤ በስምምነቱ መሠረት ወደፊት የሚከናወኑ ጉዳዩች ላይ ተፅዕኖ በማሳረፍ እንቅፋት የመፍጠር ፍላጎት፤

2ኛ) የስምምነቱ ፈራሚዎች የፓርቲያችን አባልላት ስላልሆኑ ስምምነቱ አይመለከተንም የሚል ጥርጊያ መንገድ የመክፈት ፍላጎት፤

3ኛ) በህወሓት በኩል ጦርነቱን የመቀጠል ፍላጎት እንዳለ በማስመሰል የሚፈልጉትን ነገር ለማስፈፀም ውስጣዊ ሸፍጥ መኖሩን የሚያሳይ ነው

በርግጥ እንዲህ ዓይነቱ መግለጫ፤ የሠላም ስምምነቱ ጥቅማቸውን ሊነካባቸው የሚችሉ አካላት ሊያቀናብሩት ይችላሉ። ሆኖም ፈራሚዎቹ እነ ጌታቸው ረዳ እጃቸው እንደሌለበት ርግጠኛ መሆን አይቻልም። ምክንያቱም በትናንትናው ዕለት ክንደያ ገ/ሕይወት የሚባለውና የመግለጫውን ዓይነት ሐሳብ የሚያራምደው የህወሓት ከፍተኛ አመራርን ትዊት፤ ጌታቸው የሠላም ስምምነቱን ትቶ ሼር አድርጎ በትዊተር ገፁ ሲያሰራጭ ነበር። ለማንኛውም መንግሥት ከዜጎች የተሻለ መረጃ ቢኖረውም፤ እኔም ከዚህ በኋላ ሊኖሩ የሚችሉ ሸፍጦችን በጥንቃቄ መመልከት እንደሚገባ እንደዜጋ ሐሳቤን ለመግለፅ እወዳለሁ። ያም ሆኖ፣ የቱንም ያህል የተቀነባበረ ሸፍጥና ሴራ ቢኖር፤ የተፈረመውን የሠላም ስምምነት ማደናቀፍም ይሁን ኢትዮጵያን ማሸነፍ ከቶም እንደማይቻል ህወሓትም ሆነ የትኛውም ቡድን ወይም አካል ማወቅ አለበት

የኢትዮጵያ ሠላም፣ ሉዐላዊነትና የግዛት አንድነት በልጆቿ ፈርጣማ ክንድ ፀንቶ ይኖራል
ሠላም ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ይሁን

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej