Get Mystery Box with random crypto!

ይህ የእሱ ቦታ ነበር...ካፖርቱም በርጩማውም ግርማውን ሚለብሰው እሱ ሲነካው ነበር። ሰርክ በጠዋ | ወግ ብቻ

ይህ የእሱ ቦታ ነበር...ካፖርቱም በርጩማውም ግርማውን ሚለብሰው እሱ ሲነካው ነበር።

ሰርክ በጠዋት ተነስቶ እዚህ ይሰየማል። አላፊ አግዳሚውን ሰላም ማለት ሲ ወ ድ!

ፈገግታውስ ደግሞ..

አሁን ይህ ከርካሳ ወንበር ከነካፖርቱ ሳየው ያናድደኛል።

አንስቼ እሳት ልጨምረው እቃጣለው።

እሱን አጥቶ ወንበር ማትረፍ ምን ይሉታል።

አሁን ጠዋት ጠዋት ማን ሰላም እንዲለኝ ነው ?

በማን ፈገግታ ተደግፌ ልፈግግ ነው?

አይ እድሌ....አይ እ ድ ሌ

...................................

Ribka Sisay
Jan 3,2022
Addis Ababa, Ethiopia

..................................
@ribkiphoto
@wegoch
@wegoch