Get Mystery Box with random crypto!

ገና አስፓልቱን ተሻግሬ ሳልጨርስ ድርድር ብለው የቆሙት መኪኖች ተለቀቁ.. ዘጭ ዘጭ እያልኩ ቂጤን | ወግ ብቻ

ገና አስፓልቱን ተሻግሬ ሳልጨርስ ድርድር ብለው የቆሙት መኪኖች ተለቀቁ.. ዘጭ ዘጭ እያልኩ ቂጤን እያናጋሁ ተሻገርኩ። እዛና እዚህ አራርቄያቸው የምተኛቸው እግሮቼ ብቸኝነት
ተመችቷቸው ዳሌያቸው እያደር ይሰፋል። ጎንበስ ብዬ ከሁለት ወር በፊት ይሰፋኝ የነበረ አሁን አጣብቆ የያዘኝን ሱሪ አየሁ ለንፋስ ቦታ የለውም። አፍ ቢኖረው ድረሱልኝ የሚል ያህል ከአካሌ ጋር ተዋድዷል። ምናልባት ሳወልቀው በሌሊት ተምበርክኮ ለጅንስ አምላክ ስቃዩን ያስረዳ ይሆናል። እንጃ... <<ምን እያየሽ ነው?>> አለኝ ካቀረቀርኩበት ጥቁር ከፋይ ጫማው ብቻ የሚታየኝ ሰው ... መንገድ ላይ የሚያዋራኝ አይደለም የሚያየኝን <<ምናገባህ>> ብለው ከእብድ ይቆጠርብኛል ብዬ እንጂ ደስታዬ ነው። ለጥያቄው ምላሽ የሚሆን በነገር አካሄድ ትከሻውን በሀይል ገፍቼው አለፍኩ። ውስጤ እጁን የሰቀሰቀ ወጠምሻ ፤ከልስልስ ገላዬ ስር ጉንጩን በፀብ የጫረ ነገረኛ ወንድ ያለ ይመስለኛል...ሁሌም። <<ኧረ ተይ እንተዋወቃለን >>አለኝ ያው ድምፅ ሮም የተሰራችበትን ግዜ ያህል ፈጅቼ ላየው ዞርኩ ... እሱ ነው። ረጅም፣ የቀይ ዳማ ፣ ትናንሽ አይኖች፣ የፊት ጎልማሳ የሌላቸው ልጅ እግር የጥርስ ቤተሰቦች፣ ኪንኪ ፀጉር፤ ጥቁር ኮት ያጠለቀ ሰፊ ትከሻ፣ ጥቁር ሰአት ያጠለቀ ደብዳቤ የፃፈልኝ እጅ፣ ለስላሳ ሽቶ የሚያተን ኩሩ ገላ ሁልጊዜም ከሚንደኝ ሳቁ ጋር ... እራሱ ነው።
-
አስታውሳለሁ ግቢ እያለሁ ከድርድር ሴት ጓደኞቼ መሀል በሚያማምሩ ትንንሽ አይኖቹ ይፈልገኝ ነበር። ሳያምረኝ ቀርቶ ሳይሆን እንደሁሉም ሴቶች እንዳልወደው እየፈራሁ <<መጣ መጣ>> ሲሉ ገና አይኔን በሌላ አቅጣጫ እጥል ነበር። እንደማላየው ሲያውቅ ይሆን ወይ የእውነት ደስ ብዬው አንድ እለት ግቢ በር ላይ ቆሜ ከቦርሳዬ መታወቂያ ፍለጋ ሳምስ<<የኔ ባሪያ>> ብሎኝ ገባ። ያን ለት በቤተስኪያን ደጆች ሳልፍ ሸብረክ የማይለው ጉልበቴ ሙሉ ቀን ከዳኝ። ብዙ የውበት አድናቂ አልነበርኩም ስኖር እንደሰማሁት ወንድ ልጅ ከጉማሬ መለስ ካለ የሚል ድግግሞሼን ያነገብኩ ነብርኩ። አንዱ ነገር ሲያምረኝ ሌላ የምጥልለት ብዙ መልክ አውቃለሁ። እንደእሱ ግን ምንም የማላወጣለት ሰው ማንንም አላውቅም። ቆንጆ ሲባል፤እንኳን ወንዱን ሴቷንም በእሱ ውበት ማንፀር ጀመርኩ። OCR ፊት ለፊት ፀሀይ ያጋለው ድንጋይ ላይ ከጓደኞቼ ጋር ስኮለኮል የሚሉትን መሳት፤ከአጀንዳቸው መራቅ ጀመርኩ። ስለእሱ አስባለሁ .... አንዳንዴም ስለሁለታችን፤ ስንተቃቀፍ፣ የምወደውን ቀለም ሲጠይቀኝ፣ አልጄሪያን ጥብስ ፍርፍር ሲያጎርሰኝ ሂሂ.. ከምናቤ ስባንን ግን በቀኝ ሲመጣ በቀኝ invisible gawn ለብሼ የምጠፋ ነበርኩ።
he was like a movie... a quantin tarentino movie .. that uma thurman and jhon travolta dancing scene ..He was that guy from adele's song "when we were young" and every actor in the movie that blows up a car and walks away in slow motion. . Every A- list celebrity from the
cover of vog megazine, He is that guy in every movie every women leaves her lawfull husband for, a hybrid of idris elba and michael ealy. He is a trap, a test, a temptation , you will never pass. And i fall for him over and over and over and over again.
-
It was at a party
ሳቅ፣ ስካር፣ ነፃነት ፣ ሀላፊነት የሌለው ደስታ፣ እና ጅምር ወጣትነት የሞላው ፓርቲ ...የሲጋራ ጢስ ያፈነው እዚህም እዛም የሚተዋወቁ ከዚህ ሲወጡ unprotected sex ሊደራረጉ የሚፈልጉ ፊቶች። በጆኒ አበሻዊ የሚወዘወዙ ጠያይም ፊቶች፣በጀንትልማን it is happening again ዳሌያቸውን የሚያዘልሉ ውብ ሴቶች ... አረንጓዴ ሜንት ጂን፣ የጓደኛዬ ሽኔል ሽቶ እና የእሱ stare የሞላበት ምሽት...<<አሁን ቢመጣ ምንድነው የምለው?፣ ምንድነው የምለው?፣ ምንድን ነው የምለው?፣ ምንድነው የምለው?፣ ምንድን ነው የምለው?፣ ምንድን ነው የምለው>>.. እያልኩ መልሱን ሳላገኝ መጥቶ በረጅም ቁመቱ የቤቱን ጭላንጭል ብርሃን ጋርዶ እጁን ለዳንስ ዘረጋልኝ...እየተርበተበትኩ በጓደኞቼ የድጋፍ ሳቅ ተነሳሁ... የትግስት በቀለ ና የኔ ገላ ጀመረ... እጆቹን ወገቤ ላይ አድርጎ ወደእሱ አስጠጋኝ፣ ከቁመቱ ቀንሶ ሸብረክ ስላለልኝ ለሚያምር ፊቱ
ቀረብ ብያለሁ። አይምሮዬ ውስጥ ከማውቃቸው ፊቶች ጋር አነፃፅሬ ይበልጥ የመሰለኝን አንስቼ በቀስታ <<ሲያምረኝን ትመስላለህ>> አልኩት
ወደጆሮዬ ተጠግቶ ሶስት ፊደሎችን በማይገባቸው ከባድ ትንፋሽ ጠቅልሎ ተነፈሰልኝ
<<ታድሎ!>>ሊያጨስ እጅ ለእጅ ተያይዘን ደጅ ወጣን... መንገዱ ያምር ነበር ... ጭር ያለ ...የመንገድ መብራቶቹ ብርቱካንማ ደብዛዛ ብርሃን እየተፉ ቆመው ኑ አንዳች ታሪክ ስሩብን በሚል ጭንቅላታቸውን ያዘነበሉ ይመስላሉ። ወገቤን ይዞ ወደ ራሱ አስጠጋኝ በሁለቱ እጆቹ ፊቴን አቅፎ በሚያምሩት ግን ሰስቼ ባልነገርኳችሁ ከንፈሮቹ ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ጉርስ ሳም
አደረገኝ። ሰፊ ትከሻው ውስጥ ሰረግኩ ሰመጥኩ።
-
እንዴት አለቀ? እኔንጃ.. it was a slip,not a walk... it was one step back not break up , it was never good bye, It was i ll see you.
-
<<ራስሽ ላይ መመሰጥ ጀመርሽ?>> ያችን ፈገግታውን ከርጋታ እና ከበላይነት ስሜት ጋር ብልጭ እያደረጋት ...መኪናዎቹን እንደተሻገርኳቸው አይነት አሯሯጥ ሮጬ ላመልጠው ፈለግኩ...He is that ሽቦ that says ዴንጀር የሀብታም አጥር ላይ... he was a caution for a wet floor፣ he was that ጦር in a heart but not from cubid. He is a story that has to begin with <> run baby girl, run፨

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Bez brown