Get Mystery Box with random crypto!

የዙል ሒጃ 10ሩ ቀናቶች በእነዚህ ቀናቶች የሚሰሩ ዒባዳዎች በአመቱ ውስጥ ካሉ ቀናቶች | WEDE_HAK_TUBE

የዙል ሒጃ 10ሩ ቀናቶች

በእነዚህ ቀናቶች የሚሰሩ ዒባዳዎች በአመቱ ውስጥ ካሉ ቀናቶች ከሚሰሩ ዒባዳዎች ሁሉ የበለጠ ምንዳ አላቸው ። አንድ ሙእሚን በእነዚህ ቀናቶች ራሱን ከመልካም ስራ እርም ሊያደርግ አይገባም ። ሁሉም በገራለት አይነት ዒባዳ መበርታት አለበት ። ሶላት የሚገራለት በሶላት ፣ ሶደቃ የሚገራለት በሶደቃ ፣ ቁርኣን የሚገራለት በቁርኣን ፣ ዚያራ የሚገራለት በዚያራ ፣ ፆም የሚገራለት በፆም ፣ ····· አቅም ያለው ኡድሒያ ነይቶ እስከ 10ኛው ቀን ፀጉሩንና ጥፋሩን ከመቁረጥ ተቆጥቦ እድሒያውን ካረደ በኋላ መቁረጥ ።
በተቻለ መጠን እነዚህን ቀናቶች አላህን በመገዛትና ትእዛዙን በመፈፀም ለአኼራ ስንቅ መሰነቅ ያስፈልጋል ።
እነዚህ ቀናቶች አስመልክ ኑሱሶች መጥተዋ ። ከእነዚህ ውስጥ ቀናቶቹ አላህ ዘንድ ያላቸውን ቦታ ለማመልከት አላህ የማለባቸው መሆኑን የሚገልፁ የሚከተሉት አንቀፆች ይገኙበታል : –
وَالْفَجْرِ
በጎህ እምላለሁ ፡፡
وَلَيَالٍ عَشْرٍ
በዐሥር ሌሊቶችም ፡፡
በሌላ አንቀፅ ላይም የሐጅ ስራ ላይ ያሉ ሰዎች በእነዚህ ቀናቶች ውስጥ የሚሰሩትን ሲነግረን የታወቁ ቀናቶች ብሎ አውስቷቸዋል ።

« لِّيَشْهَدُوا مَنَافِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۖ فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ »
الحج ( 28 )
" ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ይመጡሃል) ፡፡ ከርሷም ብሉ ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ "፡፡
የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – በእነዚ ቀናቶች የሚሰሩ ዒባዳዎች ደረጃ ሲነግሩን እንዲህ ይላሉ : –

وروى ابن عباس – رضي الله عنهما – قال :
قال رسول الله – صلى الله عليه وآله وسلم – :
"مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهَا أَحَبُّ إِلَى اللهِ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ" يَعْنِي أَيَّامَ الْعَشْرِ، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللهِ؟ قَالَ: "وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللهِ، إِلَّا رَجُلٌ خَرَجَ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ، فَلَمْ يَرْجِعْ مِنْ ذَلِكَ بِشَيْءٍ"،
أخرجه أبو داود وابن ماجه وغيرهما

" ምንም ቀን የለም መልካም ስራ አላህ ዘንድ የበለጠ ተወዳጅ የሆነበት ከእነዚህ ቀናቶች ውጪ ( የዙል ሒጃ አስሩ ቀናቶች) የአላህ መልእክተኛ ሆይ ጂሃድም ቢሆን ? ጂሃድም ቢሆን ምናልባት አንድ ሰው ነፍሱና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ከዛ በምንም ካልተመለሰ እንጂ " ።
በመሆኑም ነገ ሳንል ዛሬውኑ በምንችለው መልካም ስራ መሰነቁን እንጀምር ።
https://t.me/Wede_Hak_Tube

https://t.me/Wede_Hak_Tube