Get Mystery Box with random crypto!

ሁል ጊዜ ሕሊናህን በመንፈሳዊ ነገሮች ሙላ !! ይህን የምታደርግ ከሆነ ዲያብሎስ መጥፎ አሳብ ሊያ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

ሁል ጊዜ ሕሊናህን በመንፈሳዊ ነገሮች ሙላ !!

ይህን የምታደርግ ከሆነ ዲያብሎስ መጥፎ አሳብ ሊያስተዋውቅህ ሲመጣ እንኳን ደህና መጣህ የሚለው ሕሊና አያገኝም። እንደ መከላከያ መፍትሔ ይሆንህ ዘንድ ዘወትር ራስህን በሥራ ባተሌ አድርግ። ዲያብሎስ ወደ እርሱ ገብቶ የወደደውን ዘር እንዳይዘራበት ሕሊናህን ባዶ አታድርገው።

መንፈሳዊ ንባብ ሕሊናን በሥራ ለመጥመድና መጥፎ አሳቦችን ለማራቅ ብቻ ሳይሆን ሌላም ታላቅ ጥቅም አለው። ንባብ ሕሊናን በተመስጦ ሊሞላ የሚችል መንፈሳዊ ዘዴ ከመስጠቱም በላይ ተቃዋሚ አሳቦችን የሚያጠፋውንና እግዚአብሔርን መውደድ የሚያስችለውን ስሜት በልብ ውስጥ ያጎናጽፋል።


@wdasemaryam
@wdasemaryam
@wdasemaryam