Get Mystery Box with random crypto!

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል ካለው የውሃ አቅርቦት በተጨማሪ  የተሻለ የውሃ አቅርቦት እንዲኖር በ | Wachemo University students' union

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል ካለው የውሃ አቅርቦት በተጨማሪ  የተሻለ የውሃ አቅርቦት እንዲኖር በማቀድ ታስቦ የተጀመረው የውሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ ስራ መጀመሩ ተገለፀ።

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

የዩኒቨርስቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ ጨምሮ ጥቂት የሴኔት አባላት በተገኙበት የውይይት መድረክ ከተማሪዎች  ህብረት ፣ ከሰላም ፎረም እንዲሁም ከሀይማኖት ተወካዮች ጋር ውይይት ተካሄዷል።

በውይይቱ ወቅት መደበኛ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ዙሪያ በርካታ ሀሳቦች የተሰነዘረ ሲሆን በጥቅሉ ተማሪዎች በፈተና ወቅት ሊተገበሩ የሚገቡ ጥብቅ መመሪያዎች ማክበርና መተግበር እንደሚገባቸው በጥብቅ አሳስበዋል።

በተዘጋጀው መድረክ  የዩኒቨርስቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ በንግግራቸው በግቢው ካለው የውሃ አቅርቦት በተጨማሪ  የተሻለ የውሃ አቅርቦት እንዲኖር በማቀድ ታስቦ የተጀመረው የውሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ ስራ መጀመሩን አብስረዋል።

ተማሪዎች በእውቀት እንዲጎለብቱ እንዳሻቸው የሚጠቀሙበትን ምቹ ግቢ መፍጠር፣ commercial complex ህንፃዎች ግንባታ ተጠናቆ ስራ ሲጀምር በርካታ ተማሪ ተኮር አገልግሎቶች እንደሚሰጥ ማስቻል፣ Wi-Fi አገልግሎት ማስፋት፣ በተማሪዎች አደረጃጀት በቀጣይ የሚታቀዱ እቅዶች ከተቋሙ እቅድ ውስጥ ተካተው ወደ ክንውን እንዲገባ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

በዚህም አጋጣሚ ስርዓት አልበኝነት ፣ በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የማይፈቀዱ ሀይማኖታዊም ይሁን ወጣ ያሉ አለባበቦች እና በሀይማኖት ስም ግጭት የሚቀሰቅሱ እንቅስቃሴዎች ላይ በተገኙ ተማሪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድባቸው  ዶ/ር ሀብታሙ በአንክሮ አስጠንቅቀዋል።

ነሀሴ 13/2014 ዓ.ም

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት


ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት  ይከታተሉን
Facebook Wachemo University Students' Union
Telegram @WCUSU

ጥያቄና አስተያየት ካላችሁ
@WCUSUbot