Get Mystery Box with random crypto!

የሰላም ሚኒስቴር ከዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለአራተኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰ | Wachemo University students' union

የሰላም ሚኒስቴር ከዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለአራተኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ሲሰለጥኑ የቆዩ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን አስመርቋል። የምረቃ ስነ ስርዓቱ በሐይማኖት አባቶች እና በሐገር ሽማግሌዎች ምርቃት ተጀምሯል ።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ለተመራቂ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መልዕክት ያስተላፋት በሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኋላፊ ወ/ሮ ሂሩት ዴሌቦ የሰላም ሚኒስቴር ዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም የዚሁ አንድ አካል ነው ብለዋል ።

በጎ ፈቃድ አገልጋዮች ለበጎነት የበጎነት ልብ ሊኖረን ይገባል ያሉት ወ/ሮ ሂሩት በቀጣይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በማህበረሰቡ ውስጥ በሚኖራችሁ ቆይታ ኢትዮጵያዊ ስሜትን ከፍ የሚያደርጉ ስራዎችን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል ።

የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ በበኩላቸው ዩኒቨርስቲው ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ለዘላቂ ሰላም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል ።

ዩኒቨርስቲው ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ለአራት ተከታታይ ዙር በማሰልጠን ሀገራዊ ኋላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል ።


በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና አስተባባሪዎች ፣ የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ አመራሮችና የግቢው ማህበረሰቦች ፣ የሀዲያ ዞን የሐይማኖት አባቶችና የሐገር ሽማግሌዎች ፣የሀዲያ ዞን አመራሮች ፣ የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም የክልል አስተባባሪዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።