Get Mystery Box with random crypto!

መንገድና እውነት

የቴሌግራም ቻናል አርማ wayandtruth — መንገድና እውነት
የቴሌግራም ቻናል አርማ wayandtruth — መንገድና እውነት
የሰርጥ አድራሻ: @wayandtruth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 119
የሰርጥ መግለጫ

“ኢየሱስም፦ እኔ #መንገድና #እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
— ዮሐንስ 14፥6
For any comment and Questions
👇👇👇👇👇
@Davebright1

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-08 11:26:50
94 viewsSon of the mighty!!!, 08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-21 17:05:50 Hey! Come watch funny videos with me on ClipClaps! There is a $1 sign up reward.
https://h5.cc.lerjin.com/propaganda/#/community?clapcode=9906562848
138 viewsDave, 14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-14 14:24:09 sign up to get a 10 US Dollar newcomer bonus! I made more than 200 US Dollars by watching the video here, so you can try it. https://hp-video.xyz/8613537177768774/
152 viewsDave, 11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-30 07:28:51 Watch " እውነት - new gospel rap song / ፍየል Gang fyel gang" on YouTube


540 viewsBerni, 04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-20 17:40:33 #የዘላለም_ሕይወት_ዋስትና (አለመጥፋት) ክፍል ሁለት
#The_doctrine_of_eternal_security part two
========(#Small sized audio)
#በወንድም_ሀብታሙ_አዲሱ

ዋነኛው የአዲስ ኪዳን ትምህርት መሠረት የአንድ አማኝ ደኀንነት የሚያገለግለው ለዘለዓለም መሆኑን ማብሰር ነው።#ዮሐ3:15-18,36፣5:24

ይህ ደኀንነት በአማኙ መልካምነት እና ብርታት ላይ የተመሰረተ አይደለም። ኤፌ 2፡8-9

ማንም አማኝ ዳግመኛ የተወለደው
ኃጢአትን ላለማድረግና በጽድቅ ለመኖር ቢሆንም በዚህ ምድራዊ ተፈጥሮ ኃጢያትን ባለማድረ መቀጠል የሚችል አይሆንም ፣
ይህም ሲባል እውነተኛ ክርስቲያን በፀጋ የዳነ ከሆነ በሐጥያት የመቀጠል መብት አለው ማለት አይደለም ይልቅስ የእግዚአብሔር ፀጋ ሃጢያተኝነትን እና አለማዊ ምኞትን ያስክዳል። #ቲቶ 2፡11-14

ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ ኀጢአት በመሞት የሰጠን የዘላለም ህይወት እኛ #በድካማችን #ተሣሥተንም ሆነ #አውቀን ስንበድል ከእኛ የሚወሰድና እኛን ለዘላለም ሞት የሚዳርገን አይደለም፡፡#1ኛጴጥ1:23.

1 ጴጥሮስ 1 :23፤
ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።

የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ
Gospel Truth Ministry Jimma.
@DawitFassilMinistry
181 viewsDave, 14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-08 18:48:27 https://youtube.be/3Esb7lZl5X4
153 viewsDave, 15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-07 19:18:56 Watch "ማሪያም ባትኖር እግዚአብሔር አይኖርም እንዴ? " on YouTube


162 viewsDave, 16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 17:19:47 #የሥላሴ_አስተምህሮ
#The_Doctrine_of_Trinity
==============================
#ክፍል_አራት (4)

#ሥላሴ_በብሉይ_ኪዳን
=================================
የሥላሴ አስተምህሮ በብሉይ የማይታወቅ በአዲስ ኪዳን የመጣ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው። በብሉይ ኪዳን ያልነበረ እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን እንዴት ሊገለጥ ይችላል?
በአዲሱ ኪዳን የተገለጠው እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን የነበረው ከሆነ እንኪያስ የሥላሴ አስተምህሮ የሚጀምረው በአዲስ ኪዳን ሳይሆን በብሉይ ኪዳን መሆን አለበት።

መጽሐፍ ቅዱስን በስርዓት ስናጠና ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን የተፃፉ እውነታዎችን ስንመረምር መሸሽ በማንችል ሁኔታ ሶስት አካላት ያሉት አንድ አምላክ (ሥላሴ) እንዳለ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተፅፎ እናገኛለን ።

ቅዱሳን ሊያስተውሉት የሚገባ ነገር፦
================================
እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድ አይደለም እግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አይደለም ሶስቱም የተለያዩ አካላት ናቸው ደግሞም አንድ አምላክ ነው።

ዘዳግም 6 (Deuteronomy)
4፤ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤

መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል!!!

ሥላሴ በብሉይ ኪዳን
===================
#በብሉይ ኪዳን የሚገኙ በርካታ ጥቅሶችን ስንመለከት ሶስት የተለያዩ አካላት ያሉት አንድ አምላክ እንዳለ በግልፅ ይናገራሉ።

በዘፍጥረት መፅሐፍ እግዚአብሔር የሚለው ኤሎሂም (Elohim )የሚል የዕብራይስጥ ቃል ይጠቀማል።
ኤል== ኃያል አምላክ (ነጠላ ቁጥር) ሲሆን
ኤሎሂም== ኃያላን አምላኮች ( ብዙ ቁጥር) ይጠቀማል።

1) ዘፍጥረት 1፡1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰማይንና ምድርን #ፈጠረ።
እግዚአብሔር (ኤሎሂም) = ብዙ ቁጥር
ፈጠረ = ነጠላ ቁጥር

2) ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም( ኤሎሂም) #አለ፡— ሰውን #በመልካችን እንደ #ምሳሌአችን #እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።
አለ= ነጠላ ቁጥር
በመልካችን,ምሳሌአችን,እንፍጠር = ብዙ ቁጥር

3) ዘፍጥረት 3፡22 እግዚአብሔር አምላክም #አለ፡— እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ #ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ..
አለ= ነጠላ ቁጥር
ከእኛ እንደ አንዱ = ብዙ ቁጥር

4) ዘፍጥረት 11፡6-7 እግዚአብሔርም #አለ፡— ......
#ኑ፥ #እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።
አለ = ነጠላ ቁጥር
ኑ ፣ እንውረድ = ብዙ ቁጥር

5) ኢሳይያስ 6፡8 የጌታንም ድምፅ፡— ማንን #እልካለሁ? ማንስ #ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ።
እልካለሁ? = ነጠላ ቁጥር
ይሄድልናል?= ብዙ ቁጥር

6) ኢሳይያስ 48 ፡15 -16፤ እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ እኔ ጠርቼዋለሁ፤ አምጥቼዋለሁ፥ መንገዱም ትከናወንለታለች።
፤ ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥ አሁንም #ጌታ እግዚአብሔርና #መንፈሱ_ልከውኛል። ( ዩሐ ወንጌል 8:23-25)
ጌታ እግዚአብሔር = አብ
መንፈሱ= መንፈስ ቅዱስ=
ልከውኛል መሲሁ (ወልድ)
7) ኢሳይያስ 61 (Isaiah)
1፤ #የጌታ የእግዚአብሔር #መንፈስ #በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
የጌታ እግዚአብሔር = አባት
መንፈስ = መንፈስ ቅዱስ
በእኔ ላይ ነው= መሲሁ (ወልድ)

8)መዝሙር 45፡6-7 በዕብራውያን 1፡8-12
እግዚአብሔር አባት እግዚአብሔር ወልድን በግልፅ የተናገረበት ቦታ ነው

ዕብራውያን 1፡8-10 ስለ ልጁ ግን፡— #አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።
ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር #አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ፥ ይላል።
10፤ ደግሞ፡— #ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤
ዕብ 1:8-10
እግዚአብሔር አባት እግዚአብሔር ወልድን በግልፅ የተናገረበት ቦታ ነው
አምላክ ሆይ == የወልድ አምላክነት
ጌታ ሆይ== የወልድ ጌትነት
እግዚአብሔር #አምላክህ= የኢየሱስ ሰውነት

9) መዝሙር 110፡1#እግዚአብሔር #ጌታዬን፡— ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፡ አለው።(ማቴዎስ 22፡43-44፤ )
እግዚአብሔር አባት ጌታ ኢየሱስን
ጌታ ጌታየን=
ያህዌ=አዶኒን
ኩርዮስ=ኩርዮስን

ዘዳግም 6 (Deuteronomy)
4፤ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤

ሮሜ 11፡33,36 የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።.......
ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

###ይቀጥላል........

የወንጌል እውነት አገልግሎት ጂማ
Gospel Truth Ministry
@wayandtruth
@wayandtruth
@wayandtruth
173 viewsDave, 14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 17:17:12 የአሸናፊነት መርህ

ፍጥረታዊ ሰው አሸናፊነትን የሚተረጉመው ማንነቱ ላይ ተመስርቶ ሳይሆን በትግሉ ጥንካሬ ላይ ተንተርሶ ነው።

ምክንያቱም መንፈሳዊ ዓለም የራሱ የሆነ የውጊያ ስልት እንዳለው እንዲሁም የሚታየውም ዓለም የራሱ የሆነ የውጊያ ስልት አለውና። ይህም ስልት ድል በትጊል ይባላል።

የሁለቱም ዓለማቶች የውጊያ ስልታቸው የተለያዩ እና ፈጽሞ የማይገናኙ መሆናቸውን ቃሉ ውስጥ የምናገኘው እውነት ነው።

የምንኖረው በዚህች ዓለም ቢሆንም የምንዋጋው በዚህ ዓለም ስልት አይደለም። "፤ በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤"
-2ኛ ቆሮ 10፥3

ጥቅት የማይባሉ ቅዱሳኖች ከእግዚአብሔር ዳግም በመወለድ የአሸናፊነትን ህይወት ተካፍለው ነገር ግን እንዳልተካፈሉ ለወደቀው ዓለም ተገዝተዋል!

እንዲሁም እጅ ሰጥተው በተሸናፊነት የሚመላለሱት ድል ነሺውን የአባታቸውን ህይወት መኖር ስለማይፈልጉ ሳይሆን የፍጥረታዊውን ዓለም የውጊያ ስልት ለመንፈሳዊው ዓለም ውጊያ ስለሚጠቀሙ ነው።

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ በማንነት አሸንፎ አርፎ መኖር እንጂ ለማሸነፍ መታገል የምል መርህ የለም። ምክንያቱም አሸናፊነት ለእግዚአብሔር የትግሉ ውጤት ሳይሆን ዘላለማዊ የሆነ የማንነቱ መገለጫ ነው።

ስለዚህ ድል በትግል የሚለው የውጊያ ስልት የምሰራው ለፍጥረታዊው እንጂ ለመንፈሳዊው ዓለም አይደለም። የመንፈሳዊው ዓለም የውጊያ ስልት ድል በማንነት ይባላል።

@wayandtruth
@wayandtruth
124 viewsDave, 14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-10 23:50:28      @wayandtruth

                   የእምነታችን መሰረት
እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 : 4-5

መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ የተሰበከ ወንጌልና የሚሰበክ ወንጌል ተፅዕኖው ከፍ ያለና እውነተኛ ነው። ወንጌል ንግግር ሳይሆን የክርስቶስ የማዳኑና የሃይሉ እንዲሁም የትንሳኤው ብስራት ነው።
ብዙ ሰዎች እምነታቸውን ተረት ተረት ላይ፣የታዋቂ ሰዎች ንግግርና ሃይል አልባ በሆነ አባባል ላይ ሲመሰርቱ ማየት የተለመደ ነው።ብዙ ሰዎች ወንጌልን ከንግግር የዘለለ መልዕክት እንደሆነ አይረዱም።

እንደ ክርስትያን እምነታችን በክርስቶስ የትንሳኤ ኃይል መመስረቱን መገንዘብ ይገባል።የተመሰረታችሁበት መሰረት ወይም የተሰበከላችሁ ወንጌል ኃይል አልባ ከሆነ ቆም ብላችሁ እምነታችሁን መርምሩ።

ወንጌል በሙሉ ሃይልና ስልጣን የሚሰበክ የእግዚአብሔር አጀንዳ ነው። ክርስትና ደግሞ በትንሳኤው ኃይል የምትኖሩበት ድል አድራጊ ህይወት ነው።

ክርስትና በሞት ላይ፣በእርግማን ላይ በበሽታ ላይ እና በየትኛውም የሲኦል መሳሪያ ሁሉ ላይ የበላይነት መቀዳጀት ነው።እውነተኛ ክርስትያናዊ እምነት የትንሳኤን ኃይል አምኖ መዳን ነው። የዳናችሁት በሚያባብል በጥበብ ቃል እንዳልሆነ ተረዱ።
በክርስቶስ ስታምኑ ወደ አስደናቂ መንግስት ተጠርታችኋል።ጌታ ላይ ያላችሁ እምነታችሁ ዘላለማዊ ታሪካችሁን የለወጠ ነው።

መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ የሰማችሁት ወንጌልና የሚያባብለው ወንጌል ልዩነት አላቸው።የሚያባብለው ወንጌል ብታምኑትም ባታምኑትም ለውጥ የማያመጣ የሰው ጥበብ ውጤት ነው።ይህ ማባበያ ኃይል አልባ ነው።ምንም ተአምራታዊና መለኮታዊ ይዘት የለውም።ይህ አባባይ ወንጌል የሃይማኖት መልክ ያለው ነው። ነገር ግን ኃይሉን የካደ ነው።አያድንም፣
አይፈውስም፣አያስመልጥም፣አያሻግርም። ይህ አባባይ ወንጌል በጥሩ ቋንቋ ብቻ ያሸበረቀ ነው።

በዚህም ዘመን ሁለት አይነት ሰዎች አሉ።
1ኛ በኃይል የተሞላውን ወንጌል የተቀበሉና የሚሰብኩ 
2ኛ የሚያባብል ወንጌል የተቀበሉና የሚሰብኩ ሰዎች ናቸው።
ወንጌል ከተሰበከ በኋላ የሃይልና የመንፈስ መገለጥ ከሌለ የተሰበከው ወንጌል መፈተሽ አለበት።

በሀይልና መንፈስን በመግለጥ ያልተሰበከ ወንጌል በኃይል የተሞላ ትውልድ አያፈራም።ይህ ማለት በፈውስ ላይ፣በአጋንንት ላይ እና በሌሎች የህይወት ጉዳዮች ላይ ኃይል የለሽ ትውልድ ያፈራል ማለት ነው።

ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1 : 20-28
@wayandtruth
@wayandtruth
@wayandtruth
200 viewsDave, 20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ