Get Mystery Box with random crypto!

… የ56 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባና በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

… የ56 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባና በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች የ 56 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የገለፀ ሲሆን በጊዜ ማዕቀፉ 39 ሰዎችን ከእሳት አደጋ፤ 85 ሰዎችን ደግሞ ከሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች በድምሩ 124 ሰዎችን በሕይወት መታደግ መቻሉን ገልጿል፡፡

ከእዚህ በተጨማሪ በመዲናዋ ለተከሰቱ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት 11.5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ከውድመት ማዳኑንም ኮሚሽኑ ተናግሯል፡፡

በዘጠኝ ወራቱ 392 አደጋዎች ያጋጠሙ ሲሆን 670 ሚልዮን ብር ሚገመት ንብረት ደግሞ መውደሙን ከኮሚሽኑ በተገኘ መረጃ ተመልክቷል፡፡

በአዲስ አበባ የእሳት ቃጠሎ፣ በግንባታ ወቅት የሚከሰት አደጋ፣ ጎርፍ በተደጋጋሚ ከሚከሰቱ አደጋዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በዘጠኝ ወራት የደረሱ አደጋዎች ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የንብረት ውድመት መጠን በ37 ሚሊዮን ብር ቀንሷል።
(አሐዱ ራድዮ)
========================
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed