"ሁለቱም ጋር ሃዘን አለ፣ እስካሁን የነበረው ችግር በዚሁ ይብቃ” የኦሮሞ እና የአማራ ማህበረሰብ ተወካዮች—ሸዋሮቢት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በይፋት ቀጣና እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ከቀያቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች "መንግስት ነፃነትን ያውጅልን ወደቀያችን እንገባለን" ሲሉ ጠየቁ። ይህንን የተናገሩት ትናንት ሚያዚያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በኤፍራታና ግድም ወረዳ ጀውሃ ቀበሌ ላይ የአጎራባች ወረዳ ማለትም የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ቀበሌዎች ከከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች እና የዞን አመራሮች እንዲሁም የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች ተገኝተው ባደረጉበት የምክክር መድረክ ነው። ለበርካታ ዘመናት የኦሮሞ እና የአማራ ማህበረሰብ አብሮ ኖሯል ሲሉ ገልጸው “ከስድስት ዓመታት ወዲህ ግን ሰው በብሔሩ ተፈልጎ ሞቷል፤ ሃብት ንብረቱ ወድሟል፤ "ሁለቱም ጋር ሃዘን አለ እስካሁን የነበረውን ችግር በዚሁ ይብቃ ለአብሮነታችን በጋራ እንስራ የወደፊቱ ይበልጣ እና" በማለትም ተናግረዋል። “አማራ ጠል አልያም ኦሮሞ ጠል የሆነ ከጭንቅላቱ ያውጣ፣ ወንድማማችነን ጎረቤት ነን በየቀያችን ሰርተን መለወጥ እንፈልጋለን” ብለዋል የሁለቱም ብሔረሰብ ተሳታፊዎች። ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ https://t.me/wasumohammed 12.9K viewsWasu Mohammed, 09:49