Get Mystery Box with random crypto!

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ በደቡብ ትግራይና በሌሎች በኃይ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ በደቡብ ትግራይና በሌሎች በኃይል የተያዙ የትግራይ ግዛቶች ባኹኑ ወቅት የተፈጠረው ክስተት በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም በሕወሃት ወይንም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም ሲሉ ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በኤክስ ትስስር ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።

ጌታቸው፣ ክስተቱ ኹለቱ ወገኖች የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እያደረጉት ያለውን አወንታዊ ግንኙነት ለማደናቀፍ የፈለጉ የስምምነቱ ጠላት የኾኑ ኃይሎች የፈጠሩት ነው በማለት ከሰዋል።

ከሩቅም ከቅርብም የግጭት ማቆም ስምምነቱ ጸር የኾኑ ኃይሎች ጦር እየሰበቁ መኾኑን የጠቀሱት ጌታቸው፣ ብቸኛው አዋጭ መንገድ ግን ሰላም ነው ብለዋል።

በአላማጣ አካባቢ ቅዳሜ እለት የጀመረው ተኩስ ትናንት ምሽት ጋፕ ማለቱ ተሰምቷል።
https://t.me/wasulife/28735
https://t.me/wasulife/28737
==========================
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed