Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በራሳቸው መመራት ያለበትን ሃላፊነት ከህግ ውጭ አሳልፈው ለሌላ ሰጡ ከሳምንት በ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በራሳቸው መመራት ያለበትን ሃላፊነት ከህግ ውጭ አሳልፈው ለሌላ ሰጡ

ከሳምንት በፊት በተጻፈ የሹመት ደብዳቤ በቅርቡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒትርነት የተሸሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን በቦርድ ሰብሳቢነት እንዲመሩ ተሹመዋል።

ሆኖም ከሁለት አመት በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ የወጣው የኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 487/2014 አንቀጽ 11 ንኡስ አንቀጽ አንድ እንደሚያትተው የቦርድ ሰብሳቢ የሚሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው፡፡

ደንቢ ሰብሳቢው ሌሎች ስድስት የቦርድ አባላትን ይሾማል ይላል፡፡ ሆኖም ህጉ ሳይሻሻል የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሾም እያነጋገረ ነው፡፡

አቶ ተመስገን ሹመታቸውን ተከትሎ የኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና መስሪያ ቤት ትላንት መጋቢት 19 ቀን የጎበኙ መሆኑን ድርጅቱ በማህበራዊ ገፁ አጋርቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በስሩ ወደ 27 የሚጠጉ ግዙፍ እና ስትራቴጂካዊ የመንግስት ኩባንያዎች የሚያስተዳድር ተቋም መሆኑ ይታወሳል ሲል ካፒታል ጋዜጣ በዘገባው አመልክቷል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed