Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ በአማራ ክልል ከሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የሚወጡ የንጹሐን ግድያ ሪፖርቶች አሳ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

አሜሪካ በአማራ ክልል ከሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የሚወጡ የንጹሐን ግድያ ሪፖርቶች አሳስበውኛል አለች።

አሜሪካ በአማራ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በሚገኙት ሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የሚወጡ የንጹሐን ግድያ ሪፖርቶቾ አሳስበውኛል ያለችው አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል ነው።

በኢትዮጵያ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በኩል በወጣው መግለጫ ላይ በሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ሰዎች ንጹሐን ላይ ግድያ እና ጉዳት ከመድረሱ በተጨማሪ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተመላክቷል።

የኤምባሲው መግለጫ ውስብስብ ያለውን የኢትዮጵያን የፖለቲካ እና የደህንነት ቀውስ ለመፍታት መፍትሔው ንግግር መሆኑን አፅንኦት ሰጥቶበታል። በአጣዬ ከተማ ሰሞኑን በነበረው ግጭት ወደ ሸዋሮቢት እና ደብረብርሃን ከተማ የተፈናቁ ነዋሪዎች እንዳሉ ታውቋል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed