Get Mystery Box with random crypto!

የልባችን እድሜ ከእኛ ቀደሞ እያረጀ ይሆን፤ እንዴትስ ማወቅ እንችላለን? ጤናማ አመጋገብን መከተል | Wasu Mohammed-ዋሱ መሀመድ

የልባችን እድሜ ከእኛ ቀደሞ እያረጀ ይሆን፤ እንዴትስ ማወቅ እንችላለን?

ጤናማ አመጋገብን መከተል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ከአጉል ሱሶች መራቅ ልባችን ቀድሞን እንዳያረጅ ያደርጋሉ ተብሏል
ልባችን ከእድሜያችን በላይ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ?
የልባችን እድሜ ለልብ ህመም እና ስትሮክ የመጋለጥ እድላችን ይጠቁማል ይላሉ ባለሙያዎች።
ልባችን ከእኛ ቀድሞ የሚያረጀው በተለያዩ ምክንያቶች ቢሆንም ጾታ፣ ክብደት እና የደም ግፊት መጠንን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቤታችን ውስጥ የምናውቅበት የልብ እድሜ ማስያ (ካልኩሌተር) አለ።

የልብ እድሜ ማስያው የሚሰጠን ጠቅለል ያለ መረጃ መሆኑ ግን አጠራጣሪ ነገሮችን ስንመለከት የህክምና ባለሙያዎችን ማማከር ያስገድዳል።
ከዚህ በታች የተዘዘዘሩት ጉዳዮችም ልባችን ከእና ቀድመው እንዲያረጁ የሚያደርጉ ናቸውና አስቀድመን ጥንቃቄ ማድረግ ይበጃል።

1. ጭንቀት

ልብን በፍጥነት ከሚያስረጁ ምክንያቶች ቀዳሚው ጭንቀት መሆኑን ጆን ሆፕኪንስ ያወጣው ጥናት ያሳያል። ጭቅጭቅ የበዛበት ትዳር ውስጥ ያሉ እና ፍቺ የተደጋገመባቸው ሰዎች ለልብ ህመም የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ መሆኑንም ነው ጥናቱ ያመላከተው። በጭንቀት ጊዜ ሰውነታችን የሚለቃቸው ኬሚካሎች የደም ግፊት እና የመጥፎ ኮሊስትሮል መጠን እንዲጨምር ማድረጉም የልብ ጤናን እንዲያውክ ያደርገዋል።

2. ጨውና ስኳር የበዛባቸው ምግቦች

የተቀነባበሩ፣ ጨውና ስኳር የበዛባቸውን ምግቦች ማዘውተርም የደም ግፊትን ጨምሮ ለልባችንም እርጅናን ያስከትላል ነው የተባለው። በመሆኑም አትክልትና ፍራፍሬዎችን፣ እንደ አሳ ያሉ የፕሮቲንን ይዘታቸው ከፍ ያሉ ምግቦችን ከማዕዳችን እንዳይጠፉ ማድረግን ባለሙያዎች ይመክራሉ።

3. የእንቅልፍ እጦት

በቂ የእንቅልፍ ጊዜ ማጣትም የደም ዝውውርን በማፍጠን በልብ ላይ ከፍተኛ ጫናን ያሳድራል። ይህም የልብ ጤናን በረጅም ጊዜ ክፉኛ የሚጎዳው ሲሆን ልባችን ያለጊዜው ያስረጀዋል ይላል የሲ ዲ ሲ ጥናት።

4. የደም ግፊት

የአሜሪካው የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (ሲ ዲ ሲ) የልብ እርጅና እና የደም ግፊት ጥብቅ ትስስር አላቸው ይላል። የአንዲት እድሜዋ 53 የሆነች እንስት የልብ እድሜ ሲለካ 75 አመት መድረሱን እንደአብነት በማንሳትም የሴትዮዋ የደም ግፊት ከፍተኛ መሆኑ ለልቧ ቀድሟት ማርጀት ዋናው ምክንያት መሆኑን ይጠቅሳል። ወጣቶች የደም ግፊታቸው ንባብ ከ120/80 እንዳይበልጥ የአኗኗር ዘይቤያቸውን ካስተካከሉ ከልብ ጋር የተያያዙ ችግሮችን በብዙ እጥፍ መቀነስ እንደሚችሉም ሲ ዲ ሲ ገልጿል።

5. አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ

ማዮ ክሊኒክ በ2019 ባደረገው ጥናት የልብ እርጅናን ለመቀነስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ትልቅ ድርሻ እንዳለው አመላክቷል። በወር ውስጥ ለ150 ደቂቃዎች የአካል እንቅስቃሴ ማድረግንም የልብ ጤናን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው በሚል ይመክራል።

6. ሲጋራ ማጨስ

“ሲጋራ ማጨስ ሳንባን ብቻ ይጎዳል ብላችሁ የምታስቡ ተሳስታችኋል” ሲ ዲ ሲ፥ ማጨስ የልብ ጤና ጸር መሆኑን ይገልጻል። በሲጋራ ውስጥ የሚገኙ ኪሚካሎች የደም መርጋትን በማስከተል በልብ ላይ ጫና እንደሚፈጥሩ በጥናት ተረጋግጧል። እናም ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ልባቸው ከእድሜያቸው በፊት ከማርጀቱ በፊት ማጨስ ያቁሙ ሲልም ያሳስባል ሲ ዲ ሲ።

7. ከፍተኛ ኮሌስትሮል

የመጥፎ ኮሌስትሮል ክምችትም የልብ ጤናንም ሆነ እድሜ ከሚወስኑ ነገሮች አንዱ ነው። በመሆኑም ከፍተኛ የስብ ክምችት ያላቸውን ምግቦች አለማዘውተር ተገቢ ነው ይላሉ ባለሙያዎች።
በአጠቃላይ ጤናማ አመጋገብን መከተል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ከአጉል ሱሶች መራቅ ልባችን ቀድሞን እንዳያረጅ ያደርጋሉ ተብሏል።
====≡=============≡=====
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለገደብ ለማግኘት ፈጥነው ከታች ያለውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፣ አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር ያድርጉ መረጃ ህይወት ነው።

http://t.me/wassulife
http://t.me/wassulife