Get Mystery Box with random crypto!

'ኮንሶዎች ከሚታወቁበት የእርከን ስራ ባሻገር የአትክልትና ፍራፍሬ ተክሎችን፤ በመትከል፣ በመንከባከ | AddisWalta - AW

"ኮንሶዎች ከሚታወቁበት የእርከን ስራ ባሻገር የአትክልትና ፍራፍሬ ተክሎችን፤ በመትከል፣ በመንከባከብና በመጠበቅ ለሌሎች አርዓያዎች ናቸው" ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 27/2015(ዋልታ) "ኮንሶዎች ከሚታወቁበት የእርከን ስራ ባሻገር፤ ለምግብነት የሚውል የአትክልትና ፍራፍሬ ተክሎችን፤ በመትከል፣ በመንከባከብና በመጠበቅ ለሌሎች አርዓያዎች ናቸው" ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ገለጸዋል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮንሶ ዞን ካራት ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን ባኖሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት:- ወቅትን ጠብቆ አካባቢን ማልማት የተለመደ ቢሆንም፤ ኮንሶዎች ተፈጥሮን መጠበቅና መንከባከብ የተለመደ ስራቸው በመሆኑ ልዩ ያደርጋቸዋል ብለዋል።

በእርከን ሥራ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በውኃ ማቆር እና በጥንታዊ የእጅ መሣሪያዎች በታወቀው የኮንሶ ሕዝብ መካከል በመገኘቴ እጅግ ደስ ብሎኛል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የኮንሶ ህዝብ ተራራን በእርከን፤ መንገድኑ በእጁ የሰራ መሆኑን ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አሁንም ይህንን ተሞክሮ በማስፋት በአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ዝናብ አጠር በሚል የሚታወቀውን አካባቢ ስም መቀየር ይጠበቃል ነው ያሉት

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮንሶ ህዝብ ጥንታዊነትን በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ የኮንሶ ሽማግሌዎች ግጭትን በማረቅም ይታወቃሉ በማለት ገልፀዋል።

ኮንሶዎች ቀልብን የሚስበው ስራ ወዳድነታቸውን የአፈርና ውሃ እቀባ እርከን ስራዎቻቸው ምስክር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ደግሞ ለምግብነት የሚውሉ ተክሎችን በመትከል አካባቢያችሁን በአረንጓዴ እንድታለብሱ ያስፈልጋል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በደረሰ አማረ