Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራም ይፋ ሆነ ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) ለሚቀጥሉት አምስት | AddisWalta - AW

የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራም ይፋ ሆነ

ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በግጭት በተጎዱ ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራም የክልል ፕሬዝዳንቶች፣ ሚኒስትሮችና የልማት አጋሮች በተገኙበት ይፋ ሆነ፡፡

የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራም ይፋ ሲደረግ በግጭቱ 28.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመትና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን ውድመቱን መልሶ ለመገንባት 20 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራሙ ይፋ በተደረገበት ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ መንግስት ለፕሮግራሙ ውጤታማነት ከሚያደርገው ሰብአዊ ድጋፍ በተጨማሪ በጀት መድቦ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ተግባር በመንግስት አቅም ብቻ የሚከናወን ተግባር ባለመሆኑ ባለድርሻ አካላትና የልማት አጋሮች ለፕሮግራሙ ስኬታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፕሮግራሙ አተገባበር ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው የፌዴራል መስሪያ ቤቶች፣ ሚኒስትሮችና በግጭት የተጎዱ ክልሎች ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተጠሪዎችና የልማት አጋሮች ኃላፊዎች በፕሮግራሙ አተገባበር ላይ ሰፊ ውይይት አድረገው የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡