Get Mystery Box with random crypto!

የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተገኙ ድሎችና ውጤቶች አጠናክረን እናስቀጥላለን - በብልፅግና ፓር | AddisWalta - AW

የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተገኙ ድሎችና ውጤቶች አጠናክረን እናስቀጥላለን - በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተገኙ ድሎችንና ውጤቶች አጠናክረን እናስቀጥላለን ሲሉ በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ ገለጹ።

ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክልል ድረስ በየደረጃው ያሉ ከ2 ሺሕ 58 በላይ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የሚሳተፉበት መድረክ ከነገ ጀምሮ በአዳማ ከተማ ይካሄዳል።

በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ የመድረኩን አጠቃላይ ይዘት በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እየተጠናቀቀ ባለው የበጀት ዓመት ህዝቡን በማስተባበርና በንቃት በማሳተፍ በርካታ ድሎችና ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል።

በተለይም የተጀመሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶችን ከማስቀጠል፣ ሰላምና ደህንነትን ከማረጋገጥ አንፃር መላው የክልሉ ህዝብ የነበረው ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0zr6s1BoK9ymwFDAyKuTa8VdTZJBRHTv83W4t7Rctuxvg76fhprzLZqcQZgqMmchKl