Get Mystery Box with random crypto!

የሰኔ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ግንቦት 28/2015 (ዋልታ) | AddisWalta - AW

የሰኔ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

ግንቦት 28/2015 (ዋልታ) የሁሉም ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከግንቦት 29 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በግንቦት ወር ሲሸጥ በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት ፡-
1. ቤንዚን ………………………………………ብር 69.52 በሊትር
2. ነጭ ናፍጣ………………………………….ብር 71.15 በሊትር
3. ኬሮሲን ……………………………………...ብር 71.15 በሊትር
4. የአውሮፕላን ነዳጅ ………………………ብር 65.35 በሊትር
5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ…………………………ብር 57.97 በሊትር
6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ………………………….ብር 56.63 በሊትር የሚሸጥ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡